የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 43

43
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የክ​ብሩ ብር​ሃን
1ወደ ምሥ​ራ​ቅም ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አመ​ጣኝ። 2እነ​ሆም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ክብር ከም​ሥ​ራቅ መን​ገድ መጣ፤ ድም​ፁም እንደ ብዙ ውኆች ይተ​ምም ነበር፤ ከክ​ብ​ሩም የተ​ነሣ ምድር ታበራ ነበር። 3ያየ​ሁ​ትም ራእይ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለማ​ጥ​ፋት በመ​ጣሁ ጊዜ እንደ አየ​ሁት ራእይ ነበረ፤ ራእ​ዩም በኮ​ቦር ወንዝ እን​ደ​አ​የ​ሁት ራእይ ነበረ፤ እኔም በግ​ም​ባሬ ተደ​ፋሁ። 4የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ወደ ምሥ​ራቅ በሚ​መ​ለ​ከት በር ወደ መቅ​ደሱ ገባ። 5መን​ፈ​ስም አነ​ሣኝ፤ ወደ ውስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር መቅ​ደ​ሱን መል​ቶት ነበር።
6በመ​ቅ​ደ​ሱም ሆኖ የሚ​ና​ገ​ረ​ኝን ሰማሁ፤ በአ​ጠ​ገ​ቤም ሰው ቆሞ ነበር።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እኔም ቆሜ ነበር” ይላል። 7እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለዘ​ለ​ዓ​ለም የም​ቀ​መ​ጥ​በት የዙ​ፋኔ ስፍ​ራና የእ​ግሬ ጫማ መረ​ገጫ ይህ ነው። ዳግ​መ​ኛም የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸው በዝ​ሙ​ታ​ቸ​ውና በከ​ፍ​ታ​ዎ​ቻ​ቸው በአ​ለው በነ​ገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸው ሬሳ ቅዱስ ስሜን አያ​ረ​ክ​ሱም። 8መድ​ረ​ካ​ቸ​ውን በመ​ድ​ረኬ አጠ​ገብ፥ መቃ​ና​ቸ​ው​ንም በመ​ቃኔ አጠ​ገብ አድ​ር​ገ​ዋ​ልና። በእ​ኔና በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ግንብ ብቻ ነበረ፤ በሠ​ሩ​ትም ርኵ​ሰት ቅዱስ ስሜን አረ​ከሱ፤ ስለ​ዚህ በቍ​ጣዬ አጠ​ፋ​ኋ​ቸው። 9አሁ​ንም ዝሙ​ታ​ቸ​ው​ንና የነ​ገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሬሳ ከእኔ ዘንድ ያርቁ፤ እኔም ለዘ​ለ​ዓ​ለም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አድ​ራ​ለሁ።
10“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ሥራ​ቸ​ው​ንና ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይተዉ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ይህን ቤት አሳ​ያ​ቸው፤ አም​ሳ​ያ​ው​ንም ይለኩ። 11እነ​ር​ሱም ስለ ሠሩት ሥራ ሁሉ መቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸ​ውን ያገ​ኛሉ፤ አን​ተም የቤ​ቱን መል​ክና ምሳ​ሌ​ውን፥ መው​ጫ​ው​ንም፥ መግ​ቢ​ያ​ው​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም፥ ሕጉ​ንም ሁሉ አስ​ታ​ው​ቃ​ቸው፤ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ሕጉን ሁሉ ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ ያደ​ር​ጉ​ትም ዘንድ በፊ​ታ​ቸው ጻፈው። 12በተ​ራ​ራው ራስ ላይ ያለ​ውን ቤቱ​ንና የቤ​ቱን ሥር​ዐት ሣል፤ የዙ​ሪ​ያ​ውም ዳርቻ ሁሉ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው። እነሆ የቤቱ ሕግ ይህ ነው።”
የመ​ሠ​ውያ አሠ​ራር
13የመ​ሠ​ዊ​ያው ልክ በክ​ንድ ይህ ነው፤ ክን​ዱም ክንድ ተጋት ነው። የመ​ሠ​ረ​ቱም ቁመቱ አንድ ክንድ፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ነው፤ አንድ ስን​ዝ​ርም ክፈፍ ዳር ዳሩን በዙ​ሪ​ያው አለ፤ የመ​ሠ​ዊ​ያው ቁመት እን​ዲሁ ነው። 14በመ​ሬ​ቱም ላይ ከአ​ለው መሠ​ረት ጀምሮ እስከ ታች​ኛው እር​ከን ድረስ ሁለት ክንድ፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ነው፤ ከት​ን​ሹም እር​ከን ጀምሮ እስከ ትልቁ እር​ከን ድረስ አራት ክንድ፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ነው። 15ምድ​ጃ​ውም አራት ክንድ ነው፤ በም​ድ​ጃ​ውም ላይ አንድ ክንድ ወደ ላይ ከፍ የሚሉ አራት ቀን​ዶች አሉ​በት። 16የም​ድ​ጃ​ውም ርዝ​መት ዐሥራ ሁለት ክንድ፥ ወር​ዱም ዐሥራ ሁለት ክንድ ነው፥ አራ​ቱም ማዕ​ዘን ትክ​ክል ነው። 17የእ​ር​ከ​ኑም ርዝ​መት ዐሥራ አራት ክንድ፥ ወር​ዱም ዐሥራ አራት ክንድ ነው፤ አራ​ቱም መዐ​ዝን ትክ​ክል ነው፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያለው ክፈፍ የክ​ንድ እኩ​ሌታ ነው፤ መሠ​ረ​ቱም በዙ​ሪ​ያው አንድ ክንድ ነው፤ ደረ​ጃ​ዎ​ቹም ወደ ምሥ​ራቅ ይመ​ለ​ከ​ታሉ።”
18እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡ​በት ዘንድ፥ ደሙ​ንም ይረ​ጩ​በት ዘንድ በሚ​ሠ​ሩ​በት ቀን የመ​ሠ​ዊ​ያው ሕግ ይህ ነው። 19ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ለሚ​ቀ​ርቡ ከሳ​ዶቅ ዘር ለሚ​ሆኑ ለሌ​ዋ​ው​ያኑ ካህ​ናት ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን ከመ​ን​ጋው አንድ ወይ​ፈን ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 20ከደ​ሙም ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ በአ​ራቱ የመ​ሠ​ዊያ ቀን​ዶ​ቹም፥ በእ​ር​ከ​ኑም በአ​ራቱ ማዕ​ዘን ላይ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም በአ​ለው ክፈፍ ላይ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ እን​ዲሁ ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ታስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ት​ማ​ለህ። 21ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን ወይ​ፈን ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ በመ​ቅ​ደ​ሱም ውጭ በቤቱ በተ​ለ​የው ስፍራ ይቃ​ጠ​ላል። 22በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን ነውር የሌ​ለ​በ​ትን አውራ ፍየል#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሁለት የፍ​የል ጠቦ​ቶ​ችን” ይላል። ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ በወ​ይ​ፈ​ኑም እን​ዳ​ነ​ጹት እን​ዲሁ መሠ​ዊ​ያ​ውን ያነ​ጹ​በ​ታል። 23ማን​ጻ​ቱ​ንም ከፈ​ጸ​ምህ በኋላ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ወይ​ፈን፥ ከበ​ጎ​ችም ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ጠቦት በግ ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ 24በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ካህ​ና​ቱም ጨው ይጨ​ም​ሩ​ባ​ቸ​ዋል፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ቡ​አ​ቸ​ዋል። 25ሰባት ቀንም በየ​ዕ​ለቱ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ ነው​ርም የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን አንድ ወይ​ፈ​ንና ከበ​ጎ​ችም አንድ ጠቦት በግ ያቀ​ር​ባሉ። 26ሰባት ቀን ለመ​ሠ​ዊ​ያው ያስ​ተ​ሠ​ር​ያሉ፤ ያነ​ጹ​ታል፤ ይቀ​ድ​ሱ​ት​ማል። 27ቀኖ​ቹ​ንም በፈ​ጸሙ ጊዜ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ከዚ​ያም በኋላ ካህ​ናቱ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያደ​ር​ጋሉ፤ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ