የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 44

44
የተ​ዘ​ጋ​ችው የም​ሥ​ራቅ በር
1ወደ ምሥ​ራ​ቅም ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው በስተ ውጭ ወደ አለው ወደ መቅ​ደሱ በር መለ​ሰኝ፤ ተዘ​ግ​ቶም ነበር። 2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ይህች በር ተዘ​ግታ ትኖ​ራ​ለች እንጂ አት​ከ​ፈ​ትም፤ ሰውም አይ​ገ​ባ​ባ​ትም፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገብ​ቶ​ባ​ታ​ልና ተዘ​ግታ ትኖ​ራ​ለች። 3አለ​ቃው ግን እርሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ጀራ ይበላ ዘንድ ይቀ​መ​ጥ​ባ​ታል፤ በበሩ ይገ​ባል፤ በዚ​ያም መን​ገድ ይወ​ጣል።”
4በሰ​ሜ​ኑም በር መን​ገድ በቤቱ ፊት አገ​ባኝ፤ እኔም አየሁ እነ​ሆም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መል​ቶት ነበር፤ እኔም በግ​ም​ባሬ ተደ​ፋሁ። 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ልብ አድ​ርግ፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ሥር​ዐ​ትና ሕግ ሁሉ የም​ነ​ግ​ር​ህን ሁሉ በዐ​ይ​ንህ ተመ​ል​ከት፤ በጆ​ሮ​ህም ስማ፤ የቤ​ቱ​ንም መግ​ቢያ፥ የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንም መውጫ ሁሉ ልብ አድ​ርግ። 6ለዐ​መ​ፀ​ኛው ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ርኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ይብ​ቃ​ችሁ። 7እን​ጀ​ራ​ዬን፥ ስብ​ንና ደምን በም​ታ​ቀ​ር​ቡ​በት ጊዜ በመ​ቅ​ደሴ ውስጥ ይሆኑ ዘንድ ቤቴ​ንም ያረ​ክሱ ዘንድ፥ በል​ባ​ቸ​ውና በሥ​ጋ​ቸው ያል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትን እን​ግ​ዶ​ችን ሰዎች አግ​ብ​ታ​ች​ኋ​ልና፥ በር​ኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ሁሉ ቃል ኪዳ​ኔን አፍ​ር​ሳ​ች​ኋ​ልና። 8የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት አል​ጠ​በ​ቃ​ች​ሁም፤ ነገር ግን የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት የሚ​ጠ​ብቁ ሌሎ​ችን ለራ​ሳ​ችሁ ሾማ​ችሁ።”
9ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ከአ​ሉት ሁሉ በል​ቡና በሥ​ጋው ያል​ተ​ገ​ረዘ የባ​ዕድ ልጅ እን​ግዳ ሁሉ ወደ መቅ​ደሴ አይ​ግባ። 10ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም በሳቱ ጊዜ ጣዖ​ታ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለው ከእኔ ዘንድ የሳቱ ሌዋ​ው​ያን ሳይ​ቀር ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ። 11ነገር ግን በመ​ቅ​ደሴ ውስጥ አገ​ል​ጋ​ዮች ይሆ​ናሉ፤ በቤ​ቱም በሮች በረ​ኞች ይሆ​ናሉ፤ በቤ​ቱም ውስጥ ያገ​ለ​ግ​ላሉ፤ ለሕ​ዝ​ቡም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ሌላ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ይሠ​ዋሉ፤ ያገ​ለ​ግ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ በፊ​ታ​ቸው ይቆ​ማሉ። 12በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ፊት አገ​ል​ግ​ለ​ዋ​ቸው ነበ​ሩና፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት የኀ​ጢ​አት እን​ቅ​ፋት ሆነ​ዋ​ልና ስለ​ዚህ እጄን በላ​ያ​ቸው አን​ሥ​ቻ​ለሁ፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይሸ​ከ​ማሉ፥#“ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይሸ​ከ​ማሉ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 13እኔ​ንም በክ​ህ​ነት ለማ​ገ​ል​ገል ወደ እኔ አይ​ቀ​ር​ቡም፤ ወደ ተቀ​ደ​ሰ​ውም ነገ​ሬና ወደ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን ነገር አይ​ቀ​ር​ቡም፤ እፍ​ረ​ታ​ቸ​ው​ንና የሠ​ሩ​ት​ንም ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ። 14ነገር ግን ለአ​ገ​ል​ግ​ሎቱ ሁሉና በእ​ርሱ ውስጥ ለሚ​ደ​ረ​ገው ሁሉ የቤ​ቱን ሥር​ዐት ጠባ​ቂ​ዎች አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።
15“ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከእኔ ዘንድ በሳቱ ጊዜ የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት የጠ​በቁ የሳ​ዶቅ ልጆች ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀ​ር​ባሉ፤ ስቡ​ንና ደሙ​ንም ወደ እኔ ያቀ​ርቡ ዘንድ በፊቴ ይቆ​ማሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 16ወደ መቅ​ደ​ሴም ይገ​ባሉ፤ ያገ​ለ​ግ​ሉ​ኝም ዘንድ ወደ ገበ​ታዬ ይቀ​ር​ባሉ፤ ሥር​ዐ​ቴ​ንም ይጠ​ብ​ቃሉ። 17ወደ ውስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በር በገቡ ጊዜ የተ​ልባ እግር ልብስ ይል​በሱ፤ በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በርና በቤቱ ውስጥ በአ​ገ​ለ​ገሉ ጊዜ ከበግ ጠጕር አን​ዳች ነገር በላ​ያ​ቸው አይ​ሁን። 18በራ​ሳ​ቸው ላይ የተ​ልባ እግር መጠ​ም​ጠ​ሚያ ይሁን፤ በወ​ገ​ባ​ቸ​ውም ላይ የተ​ልባ እግር ሱሪ ይሁን፤ የሚ​ያ​ልብ ነገር አይ​ታ​ጠቁ። 19ወደ ውጭ​ውም አደ​ባ​ባይ ወደ ሕዝብ በወጡ ጊዜ ያገ​ለ​ገ​ሉ​በ​ትን ልብ​ሳ​ቸ​ውን ያው​ልቁ፤ በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ዕቃ ቤት ውስጥ ያኑ​ሩት፤ ሕዝ​ቡ​ንም በል​ብ​ሳ​ቸው እን​ዳ​ይ​ቀ​ድሱ ሌላ​ውን ልብስ ይል​በሱ። 20ራሳ​ቸ​ው​ንም አይ​ላጩ፥ የራ​ሳ​ቸ​ው​ንም ጠጕር ይከ​ር​ከሙ እንጂ ጠጕ​ራ​ቸ​ውን አያ​ሳ​ድጉ። 21ካህ​ና​ቱም ሁሉ በው​ስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ሲገቡ የወ​ይን ጠጅ አይ​ጠጡ። 22መበ​ለ​ቲ​ቱ​ንና የተ​ፈ​ታ​ች​ይ​ቱን አያ​ግቡ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ዘር ግን ድን​ግ​ሊ​ቱን ወይም የካ​ህን ሚስት የነ​በ​ረ​ች​ይ​ቱን መበ​ለት ያግቡ። 23በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውና ባል​ተ​ቀ​ደ​ሰው መካ​ከል ይለዩ ዘንድ ሕዝ​ቤን ያስ​ተ​ምሩ፤ ንጹ​ሕና ንጹሕ ባል​ሆ​ነው መካ​ከል ይለዩ ዘንድ ያሳ​ዩ​አ​ቸው። 24ክር​ክ​ርም በሆነ ጊዜ ለመ​ፍ​ረድ ይቁሙ፤ እንደ ፍርዴ ይፍ​ረዱ፤ በበ​ዓ​ላቴ ሁሉ ሕጌ​ንና ሥር​ዐ​ቴን ይጠ​ብቁ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ይቀ​ድሱ። 25እን​ዳ​ይ​ረ​ክ​ሱም ወደ ሞተ ሰው አይ​ግቡ፤ ነገር ግን ለአ​ባት፥ ወይም ለእ​ናት፥ ወይም ለወ​ንድ ልጅ፥ ወይም ለሴት ልጅ፥ ወይም ለወ​ን​ድም፥ ወይም ላል​ተ​ዳ​ረች እኅት ይር​ከሱ። 26ከነ​ጻም በኋላ ሰባት ቀን ይቍ​ጠ​ሩ​ለት። 27በመ​ቅ​ደ​ስም ውስጥ ያገ​ለ​ግል ዘንድ ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ወደ መቅ​ደሱ በሚ​ገ​ባ​በት ቀን የኀ​ጢ​አ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ያቅ​ርብ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
28“ርስት አይ​ሆ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ እኔ ርስ​ታ​ቸው ነኝ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘንድ ርስት አት​ስ​ጡ​አ​ቸው፤ እኔ ርስ​ታ​ቸው ነኝ፤ 29የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና የኀ​ጢ​አ​ትን መሥ​ዋ​ዕት የን​ስ​ሓ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ይበ​ላሉ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ እርም የሆ​ነው ነገር ሁሉ ለእ​ነ​ርሱ ይሆ​ናል። 30የበ​ኵ​ራቱ ሁሉ መጀ​መ​ሪያ ከየ​ዓ​ይ​ነቱ፥ ከቍ​ር​ባ​ና​ች​ሁም ሁሉ የማ​ን​ሣት ቍር​ባን ሁሉ ለካ​ህ​ናት ይሆ​ናል፤ በቤ​ታ​ች​ሁም ውስጥ በረ​ከት ያድር ዘንድ የአ​ዝ​መ​ራ​ች​ሁን ቀዳ​ም​ያት ለካ​ህ​ናቱ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ። 31ከዎ​ፍም ሆነ ከእ​ን​ስሳ የበ​ከ​ተ​ው​ንና አውሬ የሰ​በ​ረ​ውን ካህ​ናት አይ​ብ​ሉት።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ