ትንቢተ ሕዝቅኤል 9
9
የኢየሩሳሌም መቀጣት
1እርሱም፥ “እያንዳንዳቸው የሚያጠፉባት መሣሪያን በእጃቸው ይዘው ከተማዪቱን የሚቀሥፉ ይቅረቡ” ብሎ በታላቅ ድምፅ በጆሮዬ ጮኸ። 2እነሆም እያንዳንዳቸው ገጀሞ መሣሪያ በእጃቸው ይዘው ስድስት ሰዎች ወደ ሰሜን ከሚመለከተው ከላይኛው በር መንገድ መጡ፤ በመካከላቸውም የበፍታ ልብስ የለበሰና የሰንፔር መታጠቂያ በወገቡ የታጠቀ#ዕብ. “የጸሓፊ ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘ ...” ይላል። አንድ ሰው ነበረ። እነርሱም ገብተው በናሱ መሠዊያ አጠገብ ቆሙ።
3የእስራኤልም አምላክ ክብር በበላዩ ከነበረበት ኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መድረክ ሄዶ ነበር፤ በፍታም የለበሰውን፥ የሰንፔር መታጠቂያም በወገቡ የታጠቀውን ሰው ጠራ። 4እግዚአብሔርም፥ “በከተማዪቱ በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ኀጢአት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግንባር ላይ ምልክት ጻፍ አለው። 5እኔም እየሰማሁ ለሌሎቹ፦ በስተኋላው ወደ ከተማው ግቡ፤ ግደሉም፤ ዐይናችሁ አይራራ፤ ይቅርም አትበሉ፤ 6ሽማግሌውንና ጎበዙን፥ ድንግሊቱንም፥ ሕፃናቱንና ሴቶቹን፥ ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወደ አለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ” አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ። 7እርሱም፥ “ቤቱን አርክሱ፤ ወጥታችሁ ግደሉ፤ በሙታንም መንገዶችን ሙሉ” አላቸው። 8ሲገድሉም እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ#“ሲገድሉም እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ” የሚለው በዕብ. ብቻ። በግንባሬ ተደፍቼ፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ቅሬታ ሁሉ ታጠፋለህን?” ብዬ ጮኽሁ።
9እርሱም፥ “የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ኀጢአት እጅግ በዝቶአል፤ ምድሪቱም በብዙ አሕዛብ#ዕብ. “በደም” ይላል። እንደ ተመላች ከተማዪቱም እንዲሁ ዓመፅንና ርኵሰትን ተሞልታለች፤ እነርሱም፦ እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል፤ እግዚአብሔርም አያይም” ብለዋል። 10“እኔም ደግሞ በዐይኔ አልራራም፤ ይቅርታም አላደርግም፤ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ” አለኝ። 11እነሆም በፍታ የለበሰው፥ የሰንፔር መታጠቂያም በወገቡ የታጠቀው ሰው መጣ፥ “ያዘዝኸኝንም አድርጌአለሁ” ብሎ በቃሉ መለሰ።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 9: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ