ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 2

2
ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት
1ስለ ይሁ​ዳና ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አሞፅ ልጅ ወደ ኢሳ​ይ​ያስ የመጣ ቃል።
2በኋላ ዘመን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በተ​ራ​ሮች ራስ ላይ ይታ​ያል፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ የተ​ከ​በረ ይሆ​ናል ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በተ​ራ​ሮች ራስ ላይ ይሆ​ናል ፤” ይላል። ከኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አሕ​ዛ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ይመ​ጣሉ። 3ሕግ ከጽ​ዮን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይወ​ጣ​ልና ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ መጥ​ተው፥ “ኑ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ፥ ወደ ያዕ​ቆብ አም​ላክ ቤት እን​ውጣ፤ እር​ሱም መን​ገ​ዱን ያስ​ተ​ም​ረ​ናል፤ በጎ​ዳ​ና​ውም እን​ሄ​ዳ​ለን” ይላሉ። 4በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ይፈ​ር​ዳል፤ ብዙ አሕ​ዛ​ብ​ንም ይዘ​ል​ፋ​ቸ​ዋል፤ ሰይ​ፋ​ቸ​ው​ንም ማረሻ፥ ጦራ​ቸ​ው​ንም ማጭድ ለማ​ድ​ረግ ይቀ​ጠ​ቅ​ጣሉ፤ ሕዝ​ብም በሕ​ዝብ ላይ ሰይ​ፍን አያ​ነ​ሣም፤ ሰል​ፍ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ማ​ሩም።
5አሁ​ንም የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ፥ ኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብር​ሃን እን​መ​ላ​ለስ። 6ሕዝ​ቡን የያ​ዕ​ቆ​ብን ቤት ትቶ​አ​ልና፤ ምድ​ራ​ቸው እንደ ቀድ​ሞው እንደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ምድር በሟ​ርት ተሞ​ል​ቶ​አ​ልና፤ እንደ ባዕድ ልጆ​ችም ሆነ​ዋ​ልና፤ ብዙ እን​ግ​ዶች ልጆ​ችም ተወ​ል​ደ​ው​ላ​ቸ​ዋ​ልና። 7ምድ​ራ​ቸ​ውም በብ​ርና በወ​ርቅ ተሞ​ል​ታ​ለች፤ ለመ​ዛ​ግ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቍጥር የለ​ውም፤ ምድ​ራ​ቸ​ውም ደግሞ በፈ​ረ​ሶች ተሞ​ል​ታ​ለች፤ ለሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ቍጥር የለ​ውም። 8ምድ​ራ​ቸ​ውም በእ​ጆ​ቻ​ቸው በሠ​ሩ​አ​ቸው ጣዖ​ታት ተሞ​ል​ታ​ለች፤ በጣ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ለሠ​ሩ​አ​ቸው ይሰ​ግ​ዳሉ። 9ታና​ሹም ሰው ዝቅ ብሎ​አል፤ ታላ​ቁም ሰው ተዋ​ር​ዶ​አል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይቅር አል​ላ​ቸ​ውም።
10አሁ​ንም ምድ​ርን ያነ​ዋ​ው​ጣት ዘንድ በተ​ነሣ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ፍ​ራ​ትና ከግ​ር​ማው ክብር የተ​ነሣ ወደ ድን​ጋይ ዋሻ ግቡ፤ በመ​ሬት ውስ​ጥም ተሸ​ሸጉ። 11የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞች ሰዎች ዐይ​ኖች ይዋ​ረ​ዳሉ፤#ግሪኩ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች ከፍ ከፍ ይላሉ” ይላል። የሰ​ዎ​ችም ኵራት ትወ​ድ​ቃ​ለች፥ በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።
12የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በት​ዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውና በኵ​ራ​ተ​ኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለ​ውም ላይ ይሆ​ናል፤ እነ​ር​ሱም ይዋ​ረ​ዳሉ፤ 13ደግ​ሞም በረ​ጅሙ ከፍ ባለ​ውም በሊ​ባ​ኖስ ዝግባ ሁሉ ላይ፥ በባ​ሳ​ንም ዛፍ ሁሉ ላይ፥ 14በረ​ጅ​ሙም ተራራ ሁሉ ላይ፥ ከፍ ባለ​ውም ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፥ 15በረ​ጅ​ሙም ግንብ ሁሉ ላይ፥ በተ​መ​ሸ​ገ​ውም ቅጥር ሁሉ ላይ፥ 16በባ​ሕ​ሩም መር​ከብ ሁሉ ላይ፥ በተ​ጌጡ ጣዖ​ታ​ትም ምስል#ጊርክ ሰባ. ሊ. “በተ​ደ​ረ​ደሩ መር​ከ​ቦ​ችም” ይላል። ሁሉ ላይ ይሆ​ናል። 17ሰውም ሁሉ ይዋ​ረ​ዳል፤ የሰ​ውም ኵራት ይወ​ድ​ቃል፤ በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል። 18በእጅ የተ​ሠሩ ጣዖ​ታ​ትን ሁሉ ይሰ​ው​ራሉ፤ 19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ርን ያና​ውጥ ዘንድ በተ​ነሣ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ፍ​ራ​ትና ከግ​ር​ማው ክብር የተ​ነሣ ወደ ድን​ጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃ​ቃት ውስጥ ያገ​ቡ​አ​ቸ​ዋል። 20በዚ​ያም ቀን ሰው ይሰ​ግ​ድ​ላ​ቸው ዘንድ ያበ​ጁ​አ​ቸ​ውን የብ​ሩ​ንና የወ​ር​ቁን ጣዖ​ቶ​ቹን ለፍ​ል​ፈ​ልና ለሌ​ሊት ወፍ ይጥ​ላል። 21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ርን ያና​ውጥ ዘንድ በተ​ነሣ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ፍ​ራ​ትና ከግ​ር​ማው ክብር የተ​ነሣ ወደ ድን​ጋይ ዋሻና ወደ ተሰ​ነ​ጠቁ ዓለ​ቶች ውስጥ ያገ​ባሉ። 22እስ​ት​ን​ፋሱ በአ​ፍ​ን​ጫው ያለ​በ​ትን ሰው ተዉት፤ እርሱ ስለ ምን ይቈ​ጠ​ራል?#ምዕ . 2 ቍ. 22 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ