ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 5

5
ስለ ወይን ቦታ የተ​ነ​ገረ መዝ​ሙር
1አሁን የወ​ይ​ኔን ቦታ በተ​መ​ለ​ከተ የወ​ዳ​ጄን መዝ​ሙር ለወ​ዳጄ እዘ​ም​ራ​ለሁ። ለወ​ዳጄ በፍ​ሬ​ያ​ማው ቦታ ላይ የወ​ይን ቦታ ነበ​ረው። 2አጥር አጠ​ርሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ቈፈ​ርሁ፤ ድን​ጋ​ዮ​ች​ንም ለቅሜ አወ​ጣሁ፤#በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በግ​እዝ የለም። ምርጥ የሆ​ነ​ው​ንም ወይን ተከ​ልሁ፤ በመ​ካ​ከ​ሉም ግንብ ሠራሁ፤ ደግ​ሞም የመ​ጥ​መ​ቂያ ጕድ​ጓድ ማስ​ሁ​ለት፤ ወይ​ን​ንም ያፈራ ዘንድ ጠበ​ቅ​ሁት፤ ዳሩ ግን እሾ​ህን አፈራ።
3አሁ​ንም እና​ንተ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ኖ​ሩና የይ​ሁዳ ሰዎች ሆይ፥ በእ​ኔና በወ​ይኑ ቦታዬ መካ​ከል እስኪ ፍረዱ። 4ለወ​ይኔ ያላ​ደ​ረ​ግ​ሁ​ለት፥ ከዚህ ሌላ አደ​ር​ግ​ለት ዘንድ የሚ​ገ​ባኝ ምን​ድን ነው? ወይ​ንን ያፈ​ራል ብዬ ጠበ​ቅ​ሁት፤ ነገር ግን እሾ​ህን አፈራ። 5አሁ​ንም በወ​ይኔ ላይ የማ​ደ​ር​ገ​ውን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ አጥ​ሩን እነ​ቅ​ላ​ለሁ፤ ለብ​ዝ​በ​ዛም ይሆ​ናል፤ ቅጥ​ሩ​ንም አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ ለመ​ራ​ገ​ጫም ይሆ​ናል። 6ባድማ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አይ​ገ​ረ​ዝም፤ አይ​ኰ​ተ​ኰ​ትም፤ እንደ ጠፍ ቦታ ኵር​ን​ች​ትና እሾህ ይበ​ቅ​ል​በ​ታል፤ ዝና​ብ​ንም እን​ዳ​ያ​ዘ​ን​ቡ​በት ደመ​ና​ዎ​ችን አዝ​ዛ​ለሁ። 7የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወይን ቦታ እርሱ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ነው፤ ተወ​ዳጁ አዲስ ተክ​ልም የይ​ሁዳ ሰዎች ናቸው፤ ፍር​ድን ያደ​ር​ጋል ብየ እጠ​ብቅ ነበር፤ እነ​ሆም፥ ዐመ​ፅን አደ​ረገ፤ ጽድ​ቅ​ንም አይ​ደ​ለም፥ ጩኸ​ትን እንጂ።
8ከጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቻ​ቸው እርሻ ይወ​ስዱ ዘንድ፥ ምድ​ር​ንም ለብ​ቻ​ቸው ይይ​ዟት ዘንድ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚ​ያ​ያ​ይዙ፥ እር​ሻ​ንም ከእ​ርሻ ጋር ለሚ​ያ​ቀ​ራ​ርቡ ወዮ​ላ​ቸው! 9ይህ በሠ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጆሮ ተሰ​ም​ቶ​አ​ልና፦ ቤቶች ቢሠሩ ባድማ ይሆ​ናሉ፤ ታላ​ላ​ቅና የሚ​ያ​ምሩ ቤቶ​ችም የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው አይ​ኖ​ርም። 10ዐሥር ጥማድ በሬ ካረ​ሰው የወ​ይን ቦታ አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ ይወ​ጣል፤ ስድ​ስት መስ​ፈ​ሪያ የዘራ ሦስት መሥ​ፈ​ሪያ ብቻ ያገ​ባል።
11በጥ​ዋት ወደ መሸታ ቤት ለሚ​ገ​ሠ​ግ​ሡና በመ​ጠጥ ቤት ለሚ​ውሉ ወዮ​ላ​ቸው! ወይኑ ያቃ​ጥ​ላ​ቸ​ዋ​ልና። 12በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ በከ​በ​ሮና በእ​ም​ቢ​ል​ታም እየ​ዘ​ፈኑ የወ​ይን ጠጅን ይጠ​ጣሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ግን አል​ተ​መ​ለ​ከ​ቱም፤ የእ​ጁ​ንም ሥራ አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም።
13ስለ​ዚ​ህም ሕዝቤ ወደ ምርኮ ሄዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ወ​ቁ​ት​ምና፤ ብዙ​ዎቹ በረ​ኃ​ብና በውኃ ጥም ሞቱ፤ 14ሲኦ​ልም ሆድ​ዋን አስ​ፍ​ታ​ለች፤ አፍ​ዋ​ንም ያለ ልክ ከፍ​ታ​ለች፤ የተ​ከ​በ​ሩና ታላ​ላቅ ሰዎች ባለ​ጠ​ጎ​ቻ​ቸ​ውና ድሆ​ቻ​ቸ​ውም ወደ እር​ስዋ ይወ​ር​ዳሉ። 15ታናሹ ሰውም ይጐ​ሰ​ቍ​ላል፤ ታላቁ ሰውም ይዋ​ረ​ዳል፤ የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችም ዐይ​ኖች ይዋ​ረ​ዳሉ፤ 16የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በፍ​ርድ ከፍ ከፍ ይላል፤ ቅዱ​ሱም አም​ላክ በጽ​ድቅ ይከ​ብ​ራል። 17የተ​ማ​ረኩ እንደ በሬ​ዎች ይሰ​ማ​ራሉ፤ የተ​ረ​ሱ​ትም ምግ​ባ​ቸ​ውን ሲፈ​ልጉ እንደ በግ ጠቦ​ቶች በማ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ይሰ​ማ​ራሉ።
18በደ​ልን እንደ ረዥም ገመድ ለሚ​ስቡ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም እንደ በሬ ቀን​በር ለሚ​ያ​ስሩ ወዮ​ላ​ቸው! 19“እናይ ዘንድ፥ ሥራ​ውን ያፋ​ጥን፤ እና​ው​ቃ​ትም ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ምክር፥ ትምጣ” ለሚሉ ወዮ​ላ​ቸው!
20ክፉ​ውን መል​ካም መል​ካ​ሙ​ንም ክፉ ለሚሉ፥ ጨለ​ማ​ውን ብር​ሃን ብር​ሃ​ኑ​ንም ጨለማ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ፥ ጣፋ​ጩን መራራ መራ​ራ​ው​ንም ጣፋጭ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ወዮ​ላ​ቸው!
21ለክ​ፋት ጥበ​በ​ኞች ለሆኑ፥ እኛ ጠቢ​ባን ነን ለሚ​ሉም#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በራ​ሳ​ቸው ጥበ​በ​ኞች በራ​ሳ​ቸ​ውም አስ​ተ​ዋ​ዮች” ይላል። ወዮ​ላ​ቸው!
22የወ​ይን ጠጅ ለሚ​ጠጡ ኀያ​ላን፥ የሚ​ያ​ሰ​ክ​ረ​ው​ንም መጠጥ ለሚ​ደ​ባ​ልቁ ጽኑ​ዓን ወዮ​ላ​ቸው! 23በደ​ለ​ኛ​ውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ፥ የጻ​ድ​ቁ​ንም ጽድቅ ለሚ​ያ​ስ​ወ​ግ​ዱ​በት ወዮ​ላ​ቸው!
24ስለ​ዚህ ገለባ በእ​ሳት ፍም እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል፥ በነ​በ​ል​ባ​ልም እን​ደ​ሚ​በላ፥ እን​ዲሁ የእ​ነ​ርሱ ሥር የበ​ሰ​በሰ ይሆ​ናል፤ አበ​ባ​ቸ​ውም እንደ ትቢያ ይበ​ን​ናል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ጥለ​ዋ​ልና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አቃ​ል​ለ​ዋ​ልና። 25ስለ​ዚህ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ ታላቅ ቍጣን ተቈጣ፤ እጁ​ንም በላ​ያ​ቸው ዘር​ግቶ መት​ቶ​አ​ቸ​ዋል፤ ተራ​ሮ​ችም ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ፤ ሬሳ​ቸ​ውም በመ​ን​ገድ መካ​ከል እንደ ጕድፍ ሆኖ​አል። በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።
26በሩቅ ላሉ አሕ​ዛ​ብም ምል​ክ​ትን ያቆ​ማል፤ ከም​ድ​ርም ዳርቻ በፉ​ጨት ይጠ​ራ​ቸ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ እየ​ተ​ጣ​ደፉ ፈጥ​ነው ይመ​ጣሉ። 27አይ​ራ​ቡም፤ አይ​ጠ​ሙ​ምም፤#“አይ​ጠ​ሙም” የሚ​ለው በግ​እዝ ብቻ። አይ​ደ​ክ​ሙም፤ አይ​ተ​ኙም፤ የወ​ገ​ባ​ቸ​ውን መታ​ጠ​ቂያ አይ​ፈ​ቱም፤ የጫ​ማ​ቸ​ውም ማዘ​ቢያ አይ​በ​ጠ​ስም። 28ፍላ​ጾ​ቻ​ቸው ተስ​ለ​ዋል፤ ቀስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ተለ​ጥ​ጠ​ዋል፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ኮቴ እንደ ቡላድ፥ የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም መን​ኰ​ራ​ኵር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይቈ​ጠ​ራል። 29ጩኸ​ታ​ቸው እንደ አን​በሳ ነው፤ እንደ አን​በሳ ደቦ​ሎ​ችም ይቆ​ማሉ፤ ከጕ​ድ​ጓዱ እን​ደ​ሚ​ወጣ አው​ሬም ይነ​ጥ​ቃሉ፤ ይጮ​ሃሉ፤ የሚ​ድ​ንም የለም።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እር​ሱም ያስ​ወ​ጣ​ቸ​ዋል ፤ የሚ​ያ​ድ​ና​ቸ​ውም የለም” ይላል። 30በዚ​ያም ቀን እንደ ባሕር መት​መም ይተ​ም​ሙ​ባ​ቸ​ዋል፤ ወደ ምድ​ርም ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማን ያያሉ፤ ይጨ​ነ​ቃ​ሉም።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ