መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 19
19
ለስምዖን ነገድ የተሰጠ ርስት
1ሁለተኛውም ዕጣ ለስምዖን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፤ ርስታቸውም በይሁዳ ልጆች ርስት መካከል ነበረ። 2ዕጣቸውም እነዚህ ነበሩ፤ ቤርሳቤህ፥ ሰማህ፥ ቆሎዶን፤ 3አርሳላ፥ ባላ፥ ኢያሶንም፤ 4ኤርቱላ፥ ቡላ፥ ሔርማም፤ 5ሴቄላቅ፥ ቤተማኮሬብ፥ ሰርሱሲን፤ 6ቦታሩትና ሜዳዎቻቸው፥ ዐሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው፤ 7ሬሞን፥ ቴልካ፥ ኢያቴር፥ አሳንም፥ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው፤ 8እስከ ባሌቅ ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ያሉ መንደሮቻቸው ሁሉ ናቸው። ይህም በባሜት ላይ ወደ ደቡብ ያልፋል። የስምዖን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ። 9ከይሁዳ ልጆች ክፍል የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ፤ የይሁዳም ልጆች ዕድል ፋንታ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸው መካከል ወረሱ።
ለዛብሎን ነገድ የተሰጠ ርስት
10ሦስተኛውም ዕጣ ለዛብሎን ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ፤ የርስታቸውም ድንበር እስከ ኤሴዴቅ ጎላ ነበረ፤ 11ድንበራቸውም በምዕራብ በኩል ወደ ማራጌላ ይወጣል፤ እስከ ቤተ ራባም ይደርሳል፤ በኢያቃንም ፊት ለፊት ወዳለው ሸለቆም ይደርሳል፤ 12ከሴዱቅም ወደ ቤተ ሳሚስ ምሥራቅ ወደ ካሲሎቴት ዳርቻ ይዞራል፤ ወደ ዳቤሮትም ይወጣል፤ ወደ ፋንጊም ይደርሳል፤ 13ከዚያም ወደ ጌቤሮ ምሥራቅ ወደ ከታሤም ከተማ ያልፋል፤ ወደ ሪናሞን ወደ ማታርዮዛ ይወጣል። 14ድንበሩም በሰሜን በኩል ወደ አሞት ይዞራል፥ መውጫውም በሐናት በኩል በጌፋሄል ሸለቆ ነበረ። 15ቃጠናት፥ ናባሐል፥ ሲምዖን፥ ኢያሪሆ፥ ቤቴሜንም፤ ዐሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።#“ዐሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 16የዛብሎን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
ለይሳኮር ነገድ የተሰጠ ርስት
17አራተኛውም ዕጣ ለይሳኮር ልጆች ወጣ። 18ድንበራቸውም ኢይዝራኤል፥ ከልሰሉት፥ ሱሳን፤ 19አጊን፥ ሴዎንና፥ ርሄቱ፥ 20አንከሬት፥ ዳቤሮት፥ ቂሶን፥ ሮቤስ፤ 21ሬማስ፥ ያዖን፥ ቶማን፥ ኤሜሬቅ፥ ቤርሳፌስ ነበረ። 22ድንበራቸውም ወደ ታቦርና ወደ ሰሌም፥ በምዕራብ በኩል ወደ ቤተሳሚስ ይደርሳል፤ የድንበራቸው መውጫም ዮርዳኖስ ነበረ፤ ዐሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸውም።#“ዐሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸውም” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 23የይሳኮር ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
ለአሴር ነገድ የተሰጠ ርስት
24አምስተኛው ዕጣ ለአሴር ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። 25ድንበራቸውም ኤልኬት፥ ኤሌፍ፥ ቤቶቅ፥ ቂያፍ፤ 26አሊሜሌክ፥ አሜሕል፥ ማሕሳ ነበር፤ በባሕርም በኩል ወደ ቀርሜሎስ፥ ወደ ሴዎንና ሊበናት ይደርሳል፤ 27ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ቤቴጌነት ይዞራል፤ በመስዕም በኩል ከዛብሎንና ከጋይ ከይፍታሕኤል ይያያዛል ወደ ሳፍቱ ቤታሜሕና ወደ ኢንሂል ይደርሳል፤ ወደ ኮባ ማሾሜልም ያልፋል፤ 28ከዚያም ወደ ኤብሮን፥ ወደ ረዓብ፥ ወደ አሜማህን፥ ወደ ቀንታን እስከ ታላቁ ሲዶና ይደርሳል። 29ድንበሩም ወደ ራማ፥ ወደ መስፋጥ ምንጭ ወደ ጢሮስ ይዞራል፤ ድንበሩም ወደ ኢያሴፍ ይዞራል፤ መውጫውም በሌብና በኮዛብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፤ 30አርኮብ፥ አፌቅ፥ ረአውም ደግሞ ነበሩ፤ ሃያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸውም።#“ሃያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸውም” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 31የአሴር ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
ለንፍታሌም ነገድ የተሰጠ ርስት
32ስድስተኛውም ዕጣ ለንፍታሌም ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። 33ድንበራቸውም ከመሐላም፥ ከሞላም፥ ከቤሴሜይን፥ ከአርሜ፥ ከናቦቅና፥ ከኢያፍታሜን እስከ ይዳም ድረስ ነበረ፤ መውጫውም በዮርዳኖስ ነበረ። 34ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖትታቦር ይዞራል፤ ከዚያም ወደ ያቃና ይወጣል፤ ከዚያም በደቡብ በኩል ወደ ዛብሎን፤ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳኖስም በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ይደርሳል። 35የተመሸጉትም የሲዶና#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የጢሮሳውያን” ይላል። ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ጤሮስ፥ አማታዳቄት፥ ቄሬት፥ 36አርሜት፥ አራሂን፥ አሦር፥ 37ቃዴስ፥ አስራይስ፥ የአሦር ምንጭ፥ 38ቄሮህ፥ ሚጋላህሪም፥ ቤታሚና፥ ቴስሚስ፤ ዐሥራ ዘጠኝ መንደሮችና ከተሞቻቸው።#“ዐሥራ ዘጠኝ መንደሮችና ከተሞቻቸው” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 39የንፍታሌም ልጆች ነገድ ርስት እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።#“ከተሞችና መንደሮቻቸው” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
ለዳን ነገድ የተሰጠ ርስት
40ሰባተኛውም ዕጣ ለዳን ልጆች ወጣ። 41የርስታቸውም ዳርቻ ይህ ነበረ፤ ሠራሕት፥ አሳ፥ የሰመውስ ከተማ፥ 42ሰሊባን፥ አሞን፥ ሴላታ፥ 43ኤሎን፥ ቴምናታ፥ አቃሮን፥ 44አልቃታ፥ ቤጌቶን፥ ጌቤላን፥ 45አዞር፥ ቤኔቤቃት፥ ጌትሬሞን፤ 46በባሕር በኩል በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ኢያራቆን። 47የዳን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። የዳን ልጆችም በተራራው ላይ የሚያስጨንቋቸው አሞሬዎናውያንን አላስጨነቁአቸውም። አሞሬዎናውያንም ወደ ሸለቆዎች ይወርዱ ዘንድ አልፈቀዱላቸውም። ከእነርሱም ከርስታቸው ዳርቻ አንድ ክፍልን ወሰዱ። 48የዳን ልጆችም ሄደው ለኪስን መቱአት፤ ከተማቸውንም ያዟት፤ በሰይፍም መቱአት። በውስጥዋም ተቀመጡ። ስሟንም በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት። አሞሬዎናውያንም በኤዶምና በሰላሚን ለመኖር ቀጠሉ። የኤፍሬማውያንም እጅ በእነርሱ ላይ በረታች። ገባሪዎችም ሆኑላቸው።
ለኢያሱ የተሰጠ ርስት
49ምድሩንም ሁሉ በየድንበሩ ርስት እንዲሆን ከፍለው ከጨረሱ በኋላ፥ የእስራኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በእግዚአብሔር ትእዛዝ በመካከላቸው ርስት ሰጡት። 50በኤፍሬም ተራራማ ሀገር ያለችውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ ሰጡት፤ ከተማም ሠርቶ ተቀመጠባት። 51ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ነገዶች የአባቶች አለቆች በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ የተካፈሉት ርስት ይህ ነው። ምድሪቱንም መካፈል ፈጸሙ። #“ምድሪቱንም መካፈል ፈጸሙ” የሚለው በዕብ. ብቻ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 19: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ