መዝሙረ ዳዊት 47
47
በሁለተኛ ሰንበት ማግሥት የቆሬ ልጆች የምስጋና መዝሙር።
1እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤
በአምላካችን ከተማ በመቅደሱ ተራራ ምስጋናው ብዙ ነው።
2ለምድር ሁሉ ደስታን የሚያዝዝ፥
የጽዮን ተራራዎች በመስዕ በኩል ናቸው።
የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናት።
3በተቀበሏት ጊዜ እግዚአብሔር በረከትዋን ያውቃል#መዝ. 47 ቍ. 3 ዕብ. “እግዚአብሔር በታላላቅ ቤቶችዋ የመጠጊያ አንባ ሆኖ ይታወቃል” ይላል።
4እነሆ፥ የምድር ነገሥታት ተሰብስበው በአንድነት መጥተዋል።
5እነርሱስ ይህን አይተው አደነቁ፥ ደነገጡ፥ ፈሩም።
6መንቀጥቀጥም ያዛቸው፥ እንደ ወላድም በዚያ አማጡ።
7በኀይለኛ ነፋስ የተርሴስን መርከቦች ትቀጠቅጣቸዋለህ።
8እንደሰማን እንዲሁ አየን፥
በሠራዊት ጌታ ከተማ፥ በአምላካችን ከተማ፤
እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያጸናታል።
9አምላክ ሆይ፥ በአሕዛብ መካከል ይቅርታህን ተቀበልን።
10አምላክ ሆይ፥ እንደ ስምህ
እንዲሁም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስጋናህ ነው።
ቀኝህ ጽድቅን የተመላ ነው።
11አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ የጽዮን ተራሮች ደስ ይላቸዋል፥
የይሁዳም ሴቶች ልጆች ሐሤት ያደርጋሉ።
12ጽዮንን ክበቡአት፥ ዕቀፉአትም።
በቅጥሮችዋም ተናገሩ፤
13በብርታቷ ልባችሁን አኑሩ፤
በረከቷንም ትካፈላላችሁ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አዳራሾችዋንም ቍጠሩ” ይላል።
ለሚመጣውም ትውልድ ትነግሩ ዘንድ።
14ለዓለምና ለዘለዓለም ይህ አምላካችን እንደ ሆነ፥
እርሱም ለዘለዓለም ይጠብቀናል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 47: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ