መዝሙረ ዳዊት 49
49
የአሳፍ መዝሙር።
1የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ፥ ምድርንም ጠራት፤
ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ።
2ከክብሩ ውበት ከጽዮንም፥
3እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል።
አምላካችንም ዝም አይልም፤
እሳት በፊቱ ይነድዳል፥
በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ።
4በላይ ያለውን ሰማይን
ምድርንም በሕዝቡ ለመፍረድ ይጠራል፥
5እንደ ሕጉ መሥዋዕትን የሚያቀርቡትን፥
ጻድቃኑን ሰብስቡለት።
6ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥
እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና።
7ሕዝቤ፥ ስማኝ ልንገርህ፤
እስራኤልም እመሰክርብሃለሁ፤
አምላክስ እኔ አምላክህ ነኝ።
8ስለ መሥዋዕትህ የምዘልፍህ አይደለሁም፤
የሚቃጠል ቍርባንህም ሁልጊዜ በፊቴ ነው።
9ከቤትህ ፍሪዳን፥
ከመንጋህም ጊደርን#ዕብ. “ፍየል” ይላል። አልወስድም፤
10የዱር አራዊት ሁሉ፥
የምድረ በዳ እንስሶችና ላሞች ሁሉ የእኔ ናቸውና።
11የሰማይን አዕዋፍ ሁሉ አውቃለሁ፥
የዱር ውበትም#ዕብ. “አራዊት” ይላል። በእኔ ዘንድ አለ።
12ብራብም አልለምንህም፥
ዓለም ሁሉ በመላው የእኔ ነውና።
13የፍሪዳውን ሥጋ አልበላም፥
የፍየሉንም ደም አልጠጣም።
14ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥
ለልዑልም ጸሎትህን#ዕብ. “ስእለትህን” ይላል። ስጥ፤
15በመከራህ ቀን ትጠራኛለህ
አድንህማለሁ፥ አንተም ታከብረኛለህ።
16ኀጢአተኛውን ግን እግዚአብሔር አለው፦
“ለምን አንተ ሕጌን ትናገራለህ?
ኪዳኔንም በአፍህ ለምን ትወስዳለህ?
17አንተስ ተግሣጼን ጠላህ፥
ቃሌንም ወደ ኋላህ መለስኽ።
18ሌባውን ባየህ ጊዜ ከእርሱ ጋር ትሮጣለህ፥
ዕድል ፋንታህንም ከአመንዝሮች ጋር አደረግህ።
19አፍህ ክፋትን አበዛች፥
አንደበትህም ሽንገላን ተበተባት።
20ተቀምጠህ ወንድምህን ታማዋለህ፥
ለእናትህም ልጅ ዕንቅፋትን አኖርህ።
21ይህን አድርገህ ዝም አልሁህ፤
ኀጢአት አማረችህን?#በግእዝ ብቻ።
እኔ እንዳንተ እሆን ዘንድ ጠረጠርህ?
በፊትህ ቆሜ ልዝለፍህ?
22እግዚአብሔርን የምትረሱ እናንተ፥ ይህን አስተውሉ፤
አለዚያ ግን ይነጥቃል፥ የሚያድንም የለም።
23የከበረች መሥዋዕት ታከብረኛለች፥#ዕብ. “ምስጋናን የሚሠዋ ያከብረኛል” ይላል።
እግዚአብሔር ማዳኑን ያሳየባት መንገድ በዚያ አለች።”
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 49: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ