የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 57

57
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ አታ​ጥፋ። የዳ​ዊት ቅኔ።
1በእ​ው​ነት ጽድ​ቅን ብት​ና​ገ​ሩስ፥
የሰው ልጆች ሆይ፥ በቅን ትፈ​ር​ዳ​ላ​ችሁ፤
2በል​ባ​ችሁ በም​ድር ላይ ኀጢ​አ​ትን ትሠ​ራ​ላ​ች​ሁና፥
እጆ​ቻ​ች​ሁም ሽን​ገ​ላን#ዕብ. “ግፍ” ይላል። ይታ​ታ​ሉና።
3ኀጥ​ኣን ከማ​ኅ​ፀን ጀም​ረው ተለዩ፤
ከሆ​ድም ጀም​ረው ሳቱ፥ ሐሰ​ት​ንም ተና​ገሩ።
4ቍጣ​ቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፥
ጆሮ​ዋም እንደ ደነ​ቈረ እባብ፥
5ዐዋቂ ሲደ​ግ​ም​ባት የአ​ስ​ማ​ተ​ኛ​ውን ቃል እን​ደ​ማ​ት​ሰማ።
6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥር​ሳ​ቸ​ውን በአ​ፋ​ቸው ውስጥ ይሰ​ብ​ራል፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ን​በ​ሶ​ቹን መን​ጋ​ጋ​ቸ​ውን ያደ​ቅ​ቃል።
7እን​ደ​ሚ​ፈ​ስስ ውኃ ይቀ​ል​ጣሉ፤
እስ​ከ​ሚ​ያ​ደ​ክ​ማ​ቸው ድረስ ፍላ​ጻ​ቹን ይገ​ት​ራል።
8እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ ሰም ያል​ቃሉ፤
እሳት ወደ​ቀች፥ ፀሐ​ይ​ንም አላ​የ​ኋ​ትም።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አላ​ዩ​አ​ትም” ይላል።
9እሾ​ኻ​ችሁ ሳይ​ታ​ወቅ በትር ሆነ፤
ሕያ​ዋን ሳላ​ችሁ በመ​ዓቱ ይው​ጣ​ች​ኋል።
10ጻድቅ በቀ​ልን ባየ ጊዜ ደስ ይለ​ዋል፤
በኀ​ጢ​አ​ተ​ኛው ደምም እጁን ይታ​ጠ​ባል።
11ሰውም፥ “በእ​ው​ነት ለጻ​ድቅ ፍሬ አለው፤
በእ​ው​ነት በም​ድር ላይ የሚ​ፈ​ርድ አም​ላክ አለ” ይላል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ