የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 76

76
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ ስለ ኤዶ​ታም የአ​ሳፍ መዝ​ሙር።
1በቃሌ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽሁ፥
ቃሌም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ እር​ሱም አደ​መ​ጠኝ።
2በመ​ከ​ራዬ ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለ​ግ​ሁት፤
እጆ​ቼም በሌ​ሊት በፊቱ ናቸው፥ ጠላ​ቶ​ቼም አል​ረ​ገ​ጡ​ኝም።
ነፍሴ ግን ደስ​ታን አጣች።#ዕብ. “መጽ​ና​ና​ትን አል​ቻ​ለ​ችም” ይላል።
3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዐሰ​ብ​ሁት፥ ደስ አለ​ኝም፤
ተና​ገ​ርሁ፥ ነፍ​ሴም ፈዘ​ዘች።
የጠ​ላ​ቶ​ቼን ሁሉ ሰዓ​ቶች ዐወ​ቅ​ኋ​ቸው#ዕብ. “ዐይ​ኖች እን​ዲ​ተጉ ጠበ​ቅ​ሃ​ቸው” የሚል ይጨ​ም​ራል።
4ደነ​ገ​ጥሁ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁ​ምም።
5የድ​ሮ​ውን ዘመን ዐሰ​ብሁ፤
የዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙን ዓመ​ታት ዐሰ​ብሁ፤ አነ​በ​ብ​ኹም፤
6በሌ​ሊት ከልቤ ጋር ተጫ​ወ​ትሁ፥
መን​ፈ​ሴ​ንም አነ​ቃ​ቃ​ኋት።
7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በውኑ ይጥ​ላ​ልን?
እን​ግ​ዲ​ህስ ይቅ​ር​ታ​ውን አይ​ጨ​ም​ር​ምን?
8ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምስ ምሕ​ረ​ቱን ለልጅ ልጅ ይቈ​ር​ጣ​ልን?
9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታን ይረ​ሳ​ልን?#ዕብ. ይጨ​ም​ራል።
በቍ​ጣ​ውስ ምሕ​ረ​ቱን ዘጋ​ውን?
10እነሆ፥ ዛሬ ጀመ​ርሁ አልሁ፥
ልዑል ቀኙን እን​ደ​ሚ​ያ​ፈ​ራ​ርቅ።
11የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ አስ​ታ​ወ​ስሁ፤
የቀ​ደ​መ​ውን ተአ​ም​ራ​ት​ህን አስ​ታ​ው​ሳ​ለ​ሁና፤
12በም​ግ​ባ​ር​ህም ሁሉ እና​ገ​ራ​ለሁ፥
በሥ​ራ​ህም እጫ​ወ​ታ​ለሁ።
13አቤቱ፥ መን​ገ​ድህ በመ​ቅ​ደስ ውስጥ ነው፤
እንደ አም​ላ​ካ​ችን ያለ ታላቅ አም​ላክ ማን ነው?
14ተአ​ም​ራ​ትን የም​ታ​ደ​ርግ አም​ላክ አንተ ብቻ ነህ፤
ለሕ​ዝ​ብህ ኀይ​ል​ህን አሳ​የ​ሃ​ቸው።
15የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንና የዮ​ሴ​ፍን ልጆች፥
ሕዝ​ብ​ህን በክ​ን​ድህ አዳ​ን​ሃ​ቸው።
16አቤቱ፥ ውኆች አዩህ፥
ውኆች አይ​ተው ፈሩ፤
የው​ኆች ጥል​ቆች ተነ​ዋ​ወጡ፥ ውኆ​ቻ​ቸ​ውም ጮኹ።
17ደመ​ናት ድም​ፅን ሰጡ፥
ፍላ​ጾ​ች​ህም ወጡ።
18የነ​ጐ​ድ​ጓ​ድህ ድምፅ በሰ​ረ​ገላ#ዕብ. “በዐ​ውሎ” ይላል። ነበረ፤
መብ​ረ​ቆች ለዓ​ለም አበሩ፤
ምድር ተና​ወ​ጠች፥ ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠ​ችም።
19መን​ገ​ድህ በባ​ሕር ውስጥ ነው፥
ፍለ​ጋ​ህም በብዙ ውኆች ነው፥
ፍለ​ጋ​ህም አይ​ታ​ወ​ቅም።
20በሙ​ሴና በአ​ሮን እጅ
ሕዝ​ብ​ህን እንደ በጎች መራ​ሃ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ