መጽ​ሐፈ ጥበብ 6

6
የገ​ዥ​ዎች ሐላ​ፊ​ነት
1ነገ​ሥ​ታት ሆይ፥ ስሙ፤ አስ​ተ​ው​ሉም፤ የም​ድር ዳር​ቻ​ንም የም​ት​ገዙ መኳ​ን​ንት ሆይ፥ ዕወቁ። 2ብዙ ምድ​ርን የም​ት​ገዙ፥ በሠ​ራ​ዊ​ትም ብዛት የም​ት​ታ​በዩ ስሙ። 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይ​ልን ሰጥ​ት​ዋ​ች​ኋ​ልና፤ ግዛ​ታ​ች​ሁም ከል​ዑል ዘንድ ነው፤ ምግ​ባ​ራ​ች​ሁ​ንም የሚ​መ​ረ​ምር እርሱ ነው፤ ምክ​ራ​ች​ሁ​ንም ይመ​ረ​ም​ራል። 4እና​ንተ የመ​ን​ግ​ሥቱ መል​እ​ክ​ተ​ኞች ስት​ሆኑ የቀና ፍር​ድን እን​ዴት አት​ፈ​ር​ዱም? ሕጉ​ንስ እን​ዴት አል​ጠ​በ​ቃ​ች​ሁም? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ መን​ገድ እን​ዴት አል​ሄ​ዳ​ች​ሁም? 5ፈጥኖ የሚ​ቃ​ወ​ማ​ችሁ ድን​ጋ​ፄን በላ​ያ​ችሁ ያመ​ጣል፥ ቍርጥ ፍርድ በመ​ኳ​ን​ንት ላይ ይሆ​ና​ልና። 6ለተ​ዋ​ረ​ደው ድሃ ግን ከቸ​ር​ነት ሥራ የተ​ነሣ ይቀ​ል​ለ​ታል፤ ኀይ​ለ​ኞች ሰዎች ግን በጽ​ኑዕ ምር​መራ ይመ​ረ​መ​ራሉ። 7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አይቶ አያ​ዳ​ላ​ምና፤ የታ​ላ​ቁ​ንም መከ​በር አያ​ፍ​ር​ምና፤ እን​ደ​ዚ​ሁም ታና​ሹ​ንና ታላ​ቁን ስለ ፈጠረ ለገ​ዡና ለተ​ገዡ ሁሉ ያስ​ባል፤ ይወ​ስ​ን​ላ​ቸ​ዋ​ልም። 8በኀ​ያ​ላን ግን ጽኑዕ ምር​መራ ይደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ዋል። 9ክፉ​ዎ​ችና ግፈ​ኞች#“ክፉ​ዎ​ችና ግፈ​ኞች” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። መኳ​ን​ንት ሆይ፥ ጥበ​ብን እን​ድ​ታ​ው​ቁና እን​ዳ​ት​ሰ​ነ​ካ​ከሉ ነገሬ ለእ​ና​ንተ ነው። 10እው​ነ​ተኛ ትእ​ዛ​ዙን ዐው​ቀው የሚ​ጠ​ብቁ በእ​ው​ነት ይከ​ብ​ራ​ሉና የተ​ማ​ሯ​ትም ሰዎች ምሕ​ረ​ትን ያገ​ኛ​ሉና። 11እን​ግ​ዲህ ወዲህ ነገ​ሬን ተመ​ኝ​ዋት፥ ውደ​ዷ​ትም፤ ይቅ​ር​ታ​ንና ቸር​ነ​ት​ንም ታገኙ ዘንድ ተመ​ከሩ።
የጥ​በብ ዋጋ
12ጥበብ ፈጽማ የጐ​ላች ናት፤ ውበ​ቷም አይ​ጠ​ወ​ል​ግም፤ የሚ​ወ​ድ​ዷ​ትም ሰዎች ፈጥ​ነው ያዩ​አ​ታል፥ የሚ​ፈ​ል​ጉ​አ​ትም ያገ​ኙ​አ​ታል። 13ለሚ​ወ​ዷ​ትም ትደ​ር​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ አስ​ቀ​ድ​ማም ትገ​ለ​ጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለች። 14በደ​ጃፉ ስት​ጠ​ብ​ቀው ሁል ጊዜ እርሱ ያገ​ኛ​ታ​ልና ወደ​ር​ስዋ የሚ​ገ​ሠ​ግሥ ሰው አይ​ደ​ክ​ምም። 15እር​ስ​ዋን ማሰብ የዕ​ው​ቀት ፍጻሜ ነውና፥ ፈጥኖ ስለ እር​ስዋ የሚ​ተጋ ሰው ያለ ኀዘን ይኖ​ራል። 16ለእ​ር​ስዋ የሚ​ገ​ቧ​ትን ሰዎች ፈልጋ ትመ​ጣ​ለ​ችና፥ በመ​ን​ገ​ድም ድን​ገት እንደ ሥዕል አምራ ትታ​ያ​ቸ​ዋ​ለች፤ በአ​ሳ​ብም ሁሉ ትገ​ና​ኛ​ቸ​ዋ​ለች። 17የጥ​በብ መጀ​መ​ሪያ ተግ​ሣ​ጽን መው​ደድ ነው፤ ተግ​ሣ​ጽ​ንም ማሰብ እር​ሷን መው​ደድ ነው። 18እር​ሷ​ንም መው​ደድ ሕጓን መጠ​በቅ ነው፤ ሕጓ​ንም መስ​ማት ሕይ​ወ​ትን መረ​ዳት ነው። 19ሕይ​ወ​ትም ሰውን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ረበ ታደ​ር​ጋ​ለች። 20ጥበ​ብን መው​ደድ ወደ መን​ግ​ሥት ታደ​ር​ሳ​ለ​ችና።
21የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት ሆይ፥ ዙፋ​ን​ንና በትረ መን​ግ​ሥ​ትን ከወ​ደ​ዳ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትነ​ግሡ ዘንድ ጥበ​ብን አክ​ብ​ሯት። 22ጥበብ ምን​ድን ናት? እንደ ምንስ ነበ​ረች? እኔ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ የተ​ሰ​ወረ ምሥ​ጢ​ሯ​ንም ከእ​ና​ንተ አል​ሰ​ው​ርም። ነገር ግን ከጥ​ንት ጀምሮ አኳ​ኋ​ኗን እመ​ረ​ም​ራ​ለሁ፤ እር​ሷን ማወ​ቅ​ንም የተ​ገ​ለጠ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እው​ነ​ት​ንም አል​ተ​ላ​ለ​ፍም። 23በም​ቀኛ ቅን​አት አል​ኖ​ርም፤ እን​ዲህ ያለ ሰው ከጥ​በብ ጋራ አንድ አይ​ሆ​ን​ምና። 24የጠ​ቢ​ባን ብዛት የዓ​ለም መድ​ኀ​ኒት ነውና። 25አስ​ተ​ዋይ ንጉ​ሥም ለሕ​ዝቡ ጠበቃ ነው፤ በቃ​ሌም ተመ​ከሩ፤ ትጠ​ቀ​ማ​ላ​ች​ሁም።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ