በክርስቶስ ያለን ማንነትናሙና

በክርስቶስ ያለን ማንነት

ቀን {{ቀን}} ከ5

የሠርግ ልብሳችሁን ልበሱ!

እዚህ ላይ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ከሠርግ ድግስ ጋር አመሳስሎታል። የሠርጉ አዳራሽ መጥፎም ሆኑ ጥሩ በእንግዶች እንደተሞላ ይናገራል። ንጉሱ የሠርግ ልብሶችን ያልለበሰ አንድ ሰው አየ። “የሠርግ ልብስ ሳትለብስ ወደዚህ እንዴት ገባህ…?” ሲል ጠየቀ። ይህ ምንባብ በብሉይና በአዲስ ኪዳናት መካከል ያለውን ልዩነት ለእኛ ያነፃፀራል። መልካሞችን ሰዎች ያበቃቸው በጎነታቸው አልነበረም፤  ክፉዎችንም ብቁነታቸውን የነሳቸው ሥራቸው አልነበረም። በዚህ የሠርግ ድግስ ላይ የታየው የሠርግ ልብስ ነበር። ይህ ከብሉይ ኪዳን ጋር በጣም ተቃራኒ ነው።

የሕዝቅኤል መጽሐፍ የብሉይ ኪዳናዊ መመዘኛዎችን ጥብቅነት እንዲህ ሲል ይገልጻል፡- “ጻድቅ ሰው ትእዛዝን በተላለፈ ጊዜ የቀድሞ ጽድቁ አያድነውም፤ ኀጢአተኛ ሰው ከኀጢአቱ ከተመለሰ፣ ከቀድሞ ክፋቱ የተነሣ አይጠፋም። ጻድቅ ሰው ኀጢአት ቢሠራ፣ በቀድሞ ጽድቁ ምክንያት በሕይወት እንዲኖር አይደረግም።

ልክ እግዚአብሔር የአዳምንና የሔዋንን እርቃንነትን ለመሸፈን እንዳገለደመላቸው (ዘፍ 3)፣ ልክ ያዕቆብም የታላቁን ወንድሙን ልብስ እንደለበሰና የበኩርነት በረከቱን እንደተቀበለ (ዘፍ. 27)፣ እና ልክ የኢያሱ አዲስ ልብስ ከኃጢአት መወገድ ጋር እንደተቆጠረ (ዘካ. 3)፣ እንዲሁም እንደ አዲስ ኪዳን አማኞች የእኛም ጽድቅ እንደ ልብስ ነው። ገላትያ 3፡27 'ክርስቶስን ለብሰናል' ይላል።

አንዳንዶች “ይህ ማለት አሁን እንደ አዲስ ኪዳን አማኞች ኃጢአት ለማድረግ ነፃ ሆነናል ማለት ነው?” ብለው ይጠይቃሉ። የተሳሳተ ጥያቄ ነው። በአዲሱ ኪዳን ውስጥ መመዘኛዎች ተለውጠዋል። በሠርጉ ድግስ ላይ ጥያቄው “ጥሩ ነህ/ነሽ?” የሚል አልነበረም። ጥያቄው “የሠርግ ልብስሽ ወዴት አለ?” የሚል ነበር። በእርሱ ውስጥ ስንሆን ኩነኔ የለም (ሮሜ 8፡1)። እኛ አዲስ ፍጥረት ነን፣ እናም ያ አዲስ ፍጥረት ክርስቶስ ነው (2 ቆሮ 5፥17)። ጽድቃችን የእኛ አይደለም። 

የሕይወት ተዛምዶ

በዚህ አዲስ ኪዳን ውስጥ የድሮውን መመዘኛዎች የመጠቀም ስህተት አትስሩ። እዚህ አይሰሩም።

ፀሎት

አባት ሆይ፣ እኔ በአፈፃፀሜ ላይ አልታመንም። የሠርግ ልብሶቼን በምስጋና ዛሬ በእምነት እቀበላለሁ።



ቀን 1ቀን 3

ስለዚህ እቅድ

በክርስቶስ ያለን ማንነት

በእውነት በክርስቶስ ማን እንደሆንን ራሳችንን ለማስታወስ የ5 ቀን ጉዞ። ክርስቶስ ምን እንዳደረገልንና ይህ ከእርሱ ጋር በየቀኑ የምንጓዝበት መንገድ ላይ ምን ሚና እንደሚጫወት እናስታውስ።

More

ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://bezainternational.org

ተዛማጅ እቅዶች