አመለካከታችንን በትክክል መቃኘትናሙና

አመለካከታችንን በትክክል መቃኘት

ቀን {{ቀን}} ከ4

የአመለካከት ጉልበት

ከ 3 እስከ 8 ዓመት ዕድሜ ሳለሁ በቺካጎ እኖር ነበር፡፡ የአሜሪካዊ አነጋገር ነበረኝ፣ እና እግር ኳስ እወድ ነበር (በእጆችዎ የሚጫወቱትን ዓይነት)። ከዚያ ቤተሰቤ ወደ ናይሮቢ ተዛወረና የኬንያዊ አነጋገር በፍጥነት ለመድኩ እና ከእግር ኳስ ጋር ፍቅር ያዘኝ (በእግርዎ የሚጫወቱት ዓይነት)፡፡ ነጥቡ - የአካባቢ ለውጥ ማለት የአመለካከት ለውጥ ማለት ነው፡፡ አመለካከት ኃይለኛ ነገር ነው፡፡

ጎልያድን ሲገጥም ዳዊት የጠቀመው ትልቅነቱ አልነበረም፤ አመለካከቱ ነበር፡፡ ግዙፍ ሰዎች በሚገጥሟቸው ጊዜ ኢያሱና የካሌብ የጠቀማቸው የእነርሱ ጥንካሬ አልነበረም፤ አመለካከታቸው ነበር፡፡ አመለካከት ሁልጊዜ የነባራዊ ሁኔታ ተያያዥ ውጤት ነው። ኬንያ ውስጥ በአሜሪካዊ አነጋገር አልናገርም ፣ በአሜሪካ ውስጥ “ሻንግ” አልናገርም። በጴንጤቆስጤ ቀን በድፍረት ኢየሱስን ሦስት ጊዜ ክዶት የነበረው ጴጥሮስ ደፍሮ ሰበከ፡፡ ተመሳሳይ ሰው፤ የተለየ ነባራዊ ሁኔታ!

ዓለማችን በዚህ ኮሮና ቫይረስ ተበብጥብጧል። ግን እውነተኛው ጥያቄ ፣ የእርስዎ አመለካከት ምንድን ነው የሚለው ነው፡፡ ይህን ተግዳሮት ከየትኛው ነባራዊ ሁኔታ እየተመለከቱት ነው? ኢየሱስ በሉቃስ 10፥41 ማርታን “ማርታ፣ ማርታ፤ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ትታወኪማለሽም፤ የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ማርያም እኮ የሚሻለውን ድርሻ መርጣለች፤ ይህም ከእርሷ አይወሰድም።” ትጨነቂያለሽ = ገና ስለሚሆነው ነገር መረበሽ፤ ትታወኪማለሽም = ቀድሞውኑ ስለተፈጠረው ጉዳይ ማሰብ። አስተውል ኢየሱስ “ማርያም መርጣለች” አለ፤ ይህ አመለካከትን መምረጥ እንደማንችል ይነግረኛል፣ ግን አካባቢን መምረጥ እንችላለን፡፡ ማርያም የተናገረውን ሁሉ እያዳመጠች በኢየሱስ እግር ሥር መቀመጥ መረጠች፡፡ ስለዚህ በብዙ ነገሮች አልተጨነቀችም እና አልተደናገጠችም፡፡

የሕይወት ተዛምዶ

ይህንን ጊዜ በጥበብ እንድትጠቀሙበት አበረታታችኋለሁ፡፡ በጣም ብዙ ዜና አይመልከቱ። በየቀኑ ለኢየሱስ ጊዜ ይስጡ፡፡ በመንፈሱ ከእኛ ጋር ነው፡፡ እርሱ አመለካከትን ይቀይራል፣ እናም አመለካከት ኃይለኛ ነገር ነው። እግር ኳስ እንኳን መጫወት ራሱ ሊጀምሩ ይችላሉ፡፡

ፀሎት

ኢየሱስ ሆይ ፣ አንተ ያለህበትን አካባቢ እመርጣለሁ፡፡


ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 2

ስለዚህ እቅድ

አመለካከታችንን በትክክል መቃኘት

አመለካከትዎን መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ቃል በማስተካከል 4ቱን ቀናት ያሳልፉ። የመጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ በድል ለመጓዝ የእግዚአብሔርን አመለካከት እንዴት እንደጠበቁ ከተለያዩ ታሪኮች ይማሩ።

More

ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://bezainternational.org

ተዛማጅ እቅዶች