አመለካከታችንን በትክክል መቃኘትናሙና
![አመለካከታችንን በትክክል መቃኘት](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2Fhttps%3A%2F%2Fs3.amazonaws.com%2Fyvplans-staging%2F25417%2F1280x720.jpg&w=3840&q=75)
የምላሽ ኃይል
በየዘመናቱ ብዙ የእግዚአብሔር ሰዎች ከገቡበት ከባድና አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መውጣት የቻሉት ከአምላካቸው ጋር በመወገን በሚሰጡት የምላሽ ውሳኔ ነው። ምላሻችን ከእግዚአብሔር ጋር በመቆምና በመወገን መሆን አለበት። ዛሬ ግን በተማረከበት የምርኮ ምድር ሆኖ ለጊዜያዊው ተግዳሮት ሳይበገር ከበላተኛ ጋር አድሮ ሌሊቱን በድል ያነጋውን ጀግና አስታውሳችኋለሁ።
ዳንኤል በዚያች ሌሊት በጉድጓድ ተወስኖ ከአንበሳ ጋር ተፋጦ ሲያድር ቃል በቃል ምን እንዳለ ባንረዳም ምናልባት በውስጡ ግን ብዙ ነገሮችን እንደ ሰው አስቦ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ንጉሱ ሲጠራው የውስጡን ድምፅ ያሸነፈና የውጭውን ጫና የጣሰ የአንደበቱ ምላሽ የተናገረው ንጉሱን ንገስ ማለትና ቅንነቱን ነበር። ይህም የአዳሩን ቆይታና የዳንኤልን የውስጥ የሕይወት ጥንካሬ ይገልፃል። የምላሻችን አቅም የሚፈተነውና የሚለካው በሁኔታዎች ውስጥ ስንገባ ብቻ ነው። ዳንኤል ንጉሱንም ሆነ ወደ አንበሳ ጉድጓድ እንዲጣል ያሴሩበትን የሥራ ባልደረቦች ሁሉ ክፉ ቃል የመናገርና የበቀል ምላሽ የመስጠት ምክንያት ነበረው። ምላሽ ግን የምርጫ ጉዳይ ነውና፣ ዳንኤል በውስጡ የታጠቀው የእውነት ምላሽ ትሁት ሆኖ እንዲወጣ ስላደረገው ለማን ምን ምላሽ መስጠት እንዳለበት ተረድቶ ነበር። የምላሽ ኃይል ከገባንበት የጥፋት ሥፍራ ገብተን ስንወጣ ይዘነው የምንወጣው የሕይወት ልዕቀት ነው። ለዚህ ነው ኢየሱስ በዚያች አጣብቂኝ የመስቀል የጣር ወቅት ላሰቃዩት፣ ላንገላቱትና ላፌዙበት ሰዎች የነበረው ምላሽ ከእነርሱ ተቃራኒ ሆኖ የተገኘው። (ሉቃ. 23÷32-34) እንዲሁም እስጢፋኖስ እየተወገረ ይፀልይ የነበረው ከሚያርፍበት የድንጋይ አለሎ እንዲተርፍ ሳይሆን ከአንደበቱ የሚወጣው የምህረት የምላሽ ቃል ነበር። (ሐሥ. 7÷54-60)
እንግዲህ ይህንን ወቅት ስንመለከት ሁሉ ነገር ክልከላና ገደብ የተበጀበት፣ የምንነካው ሁሉ ሥጋት እንዲሁም ዋጋ የሚያስከፍል አስፈሪና ጨለማ የሆነበት ጊዜ ነው። ነገር ግን ከዚህ ፍርሃት፣ ጭንቀትና ሥጋት በመውጣት የነገን ንጋት በማየት ዛሬ ላይ የምንሰጠው ምላሽ የወደፊቱን የሕይወት ዕጣ ፈንታ ሁሉ ይወስናል። እንዲሁም አሁን ላለንበት ሁኔታ የምንሰጠው ምላሽ ሚዛን ላይ የሚወድቅበት ጊዜም ይሆናል ማለት ነው።
የሕይወት ተዛምዶ
ዳንኤል በዚያ ከባድና አጣብቂኝ ወቅት በገባ ጊዜ እርሱ ከሰጠው ምላሽ እኛ የምንወስደው ትምህርት ምንድን ነው? እስቲ ነገሩን በጥልቀት ተመልከቱት።
ፀሎት
ጌታ ሆይ፣ በጊዜውም አለጊዜውም በነገር ሁሉ መፅናት ይሁንልን።
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
![አመለካከታችንን በትክክል መቃኘት](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2Fhttps%3A%2F%2Fs3.amazonaws.com%2Fyvplans-staging%2F25417%2F1280x720.jpg&w=3840&q=75)
አመለካከትዎን መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ቃል በማስተካከል 4ቱን ቀናት ያሳልፉ። የመጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ በድል ለመጓዝ የእግዚአብሔርን አመለካከት እንዴት እንደጠበቁ ከተለያዩ ታሪኮች ይማሩ።
More
ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://bezainternational.org