ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል ?ናሙና
ዘለዓለማዊ የሆነ ውርስ አለኝ
“የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።”ሮሜ 8፡16-17
ሲድኒ ተካሂዶ በነበረው የ2000 እ.አ.አ የኦሎምፒክ ውድድር ወቅት የአሜሪካ ሴቶች ቀደም ሲል አሸናፊዎች የነበሩበትን 4x100 የሩጫ ውድድር እንደገና እንደሚያሸንፉ ሰው ሁሉ ጠብቆ ነበር፡፡ሆኖም ዕድሉን ሳይጠቀሙበት በሶስተኝነት ደረጃ ውድድሩን አጠናቀቁ፡፡
በ2004 እ.አ.አ አቴንስ ላይ ቡድኑ በአንደኝነት ደረጃ ያጠናቀቀበትን ድል ለመድገም በመሻት የመጀመሪያውን ዙር አቴንስ ላይ ከነበረው ፍጥነት በበለጠ ያጠናቀቁ ቢሆንም ከመወዳደሪያ ሜዳ ውጪ ዱላ በመቀባበላቸው ከጨዋታ ውጪ እንዲሆኑ ተደረጉ፡፡
በ2008 እ.አ.አ በቤይጂንግ በተካሄደው ውድድር ወቅት እንደገና ከውድቀት ለመዳን ያደረጉት ጥረት በ48 ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ ለሜዳሊያ እንዳይበቁ የወደቀ የውድድር ዱላ እንቅፋት ሆነባቸው፡፡
አንድን ነገር ስኬታማ በሆነ መንገድ ማስተላለፍ ምንኛ አስፈላጊ ነገር ነው?ውርስ በሩጫ ውድድር ወቅት ከሚጠቀሙበት ዱላ ጋር ይመሳሰላል፡፡እያንዳንዱ ትውልድ በሚቻለው ፍጥነት ይሮጥና ጊዜው ሲደርስ ዱላውን ለሚቀጥለው ትውልድ ያቀብሉታል፡፡አንዳንድ ጊዜ ያ ዱላ በገንዘብ ወይም በምድራዊ ሐብቶች ይመሰላል፡፡አንዳንድ ጊዜም ከዚህ የበለጠ ነገርን እንደሚወከወለወ ይታሰባል፡፡
ጳውሎስ መንፈሣዊ ውርስን በሚመለከት ለጢሞቴዎስ ሲገልፅለት “በአንተ ያለውን ግብዝነት የሌለበትን እምነትህን አስባለሁ፤ይህም እምነት ቀድሞ በአያትህ በሎይድ በእናትህም በኤውንቄ ነበረባቸው፥በአንተም ደግሞ እንዳለ ተረድቼአለሁ።”በማለት ይናገራል፡፡(2ተኛ ጢሞቴዎስ 1፡5)
ጌታ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛችን በምንቀበልበት ወቅት የእምነት“ዱላን”እንቀበላለን፡፡ከእርሱ ጋር ከትውልድ ወደ ትውልድ ተላልፎ የመጣውን የእርሱን መከራና የዘለዓለም ሕይወትን እንቀበላለን፡፡
አሁን ለእርሱ የምንሮጥ በመሆኑ የአሜሪካ ሴቶች በመጨረሻ ላይ በለንደን ተካሂዶ በነበረው የ2012 እ.አ.አ.በመሸለሚያ ቦታቸው ላይ ሆነው የወርቅ ሜዳሊያዎችን እንደወሰዱ ሁሉ እኛም ያንን ዱላ ለሚቀጥለው ሯጭ ለማስተላለፍ ወደፊታችን እንመከታለን፡፡እስከ ዛሬ ድረስ ሊሰበር ያልቻለውን 40፡82 የዓለም ሪከርድ ያስገኙት እያንዳንዱ የቡድኑ አባል እጅግ ፈጣን የሆነ ሩጫ በመሮጣቸውና የውድድር ዱላውን ስኬታማ በሆነ መንገድ ስላቀበሉትና ስለተቀበሉት ነው፡፡
ጳውሎስ ምድራዊ ሽልማቶች ጊዜያዊ እንደሆኑና የእኛ ውርስና የእኛ ሽልማት ግን ዘለዓለማዊ እንደሆነ ያሳስበናል፡፡”በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበአታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ፡፡የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙነው እኛ ግን የማይጠፋውን።”በማለት ይናገራል፡፡(1ኛ ቆሮንቶስ 9፡24-25)
ተግባራዊ ማድረግ፡- ሽልማታችሁን ተቀበሉ፤ ውርሳችሁን ተቀበሉ …ወደፊትም አስተላልፉት፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
እንደ አንድ አትሌት ሌሎች ሰዎች ሕይወታችሁንና አፈፃፀማችሁን በሚመለከት በሚያወሩበት ዓለም ውስጥ ነው የምትኖሩት፡፡ይህ የ11 ቀናት ዕቅድ እግዚአብሔር እናንተን እንደ ልጅ በመቁጠር ለእናንተ የሰጠውን ነገር እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡የሚሰጠው ተስፋ ያለው ሕይወትን፤ደህነትን፤ሠላምንና እገዛን ነው፡፡በእነዚህ ብርቱና ሕይወት ለዋጭ የሆኑ አስተሳሰቦችን የታጠቁ አትሌቶች ልዩ ይሆናሉ፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/