ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል ?ናሙና
የክርስቶስ አዕምሮ አለኝ
“እንዲያስተምረው የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።" 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡16
በፅሑፍ የሰፈሩ መመሪያዎችን ብቻ በማንበብ ዋና ለመዋኘት ልትማሩ ስትሞክሩ እስቲ አስቡት፡፡ያንን ማድረግ አስቂኝ ነው ነገር የሚሆነው፡፡ምክኒያቱም ዋና ለመማር የሚቻለው ዘሎ ውኃ ውስጥ በመግባት ብቻ ነው፡፡ይሄ ድርጊት ሰው የክርስቶሰ አዕምሮ ሣይኖረው እግዚአብሔርን ለማወቅ ከሚጥር ሰው ጋር ይመሳሰላል፡፡
መንፈሳችን ከክርስቶስ ውጪ ሆኖ ሙት በነበረበት ወቅት በክርስቶስ በኩል ያስተላለፈውና በቃሉ ማለትም በመፅሐፍ ቅዱስ በኩል የተናገረን ነገር ስሜት አይሠጠንም ነበር፡፡በ1ኛ ቆሮንቶስ 2፡11 ላይ ”በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም።”ብሎ ይናገራል፡፡
አንድ ሰው ከኃጢአት በመሸሽ በንሥሐ ወደ ክርስቶስ የሚመለስ ከሆነ እግዚአብሔር ለዚያ ሰው መንፈሱን ይሰጠዋል፡፡በውስጣችን ያለው የእግዚአብሔርመንፈስ ለእግዚአብሔር ነገሮች አዕምሯችንን ክፍት እንዲሆን ያደርገዋል፡፡የእግዚአብሔር መንፈስና አዕምሮ ከሌለን የጎዱንን ሰዎች ይቅር ማለት፤በማናየው እግዚአብሔር ላይ መደገፍ ወይም በክርስቶስ ውስጥ እንዴት አዲስ ፍጥረቶች እንደሚያደርገን ልንገነዘብ አንችልም፡፡
በ1ኛ ቆሮንቶስ 2፡10 ላይ “መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው።”በማለት ይናገራል፡፡መንፈሣዊ እውነታዎችን መረዳት የምንችለው በኢየሱስ በኩል በነፃ በሚሰጠን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነው፡፡
ዘለዓለማዊ ፍጡራን ስላልሆንና እርሱ ግን ዘለዓለማዊ ስለሆነ ማንኛውም ሰው የእግዚአብሔርን ነገር ሙሉ በሙሉ ለመረዳት አይችልም፡፡ነገር ግን የሚያዘንን ነገር ካዳመጥነውና ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚያስበውን ሃሣብ ካነበብንና መንገዱን የምናውቅ ከሆነ ቀስ በቀስ እግዚአብሔርን እያወቅነው ልንሄድ እንችላለን፡፡በመንፈሱና በከርስቶስ በሆነ አዕምሮ እግዚአብሔርንና ሌሎችን ሰዎችን ከእርሱ ዕይታ አንፃር ማየት እንጀምራለን፡፡
የጥንት ዕብራዊ ንጉሥ ሶስት አገራት ተባብረው ጥቃት ባደረሱበት ወቅት “ምን ማድረግ እንዳለብን አናውቅም ዓይኖቻችን ግን አንተን ይመለከታሉ”በማለት ፀሎት አደረገ፡፡ከሚገጥመን ችግር የተነሣ አንድን ነገር ለመቆጣጠር አዳጋች በሚሆንብን ወቅት እግዚአብሔር አዕምሮውንና መንፈሱን ስለሰጠን እግዚአብሔር ጥበብን እንዲሰጠን ልንጠይቀው እንችላለን፡፡
በእምነታችን እያደገን በሄድን ቁጥር እግዚአብሔር ኢየሱስን እንድንመስል እያደረገ ወደ ፍፁምነት ይመራናል፡፡ምንም እንኳን በዚህ ምድር ላይ ወደ ፍፁምነት ለመድረስ ባንችልም ወደ ሰማይ የምንገባው ግን ፍፁማን ተደርገን ነው፡፡ኃጢአታችንን ለማስወገድ በከፈለው ፍፁም የሆነ መሥዋዕትነት ስላመንን በእግዚአብሔር ፊት በምንቆምበት ወቅት እንደ ፍፁማን ሰዎች ነው የምንቆጠረው፡፡
ቲቶ 3 ፡ 5 "እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፡፡"
ተግባራዊ እርምጃ ፡-በሕይወታችሁ ውስጥ ስትጨነቁበት ወይም ስትታገሉት ከነበረው አሉታዊ አስተሳሰብ አሁኑኑ ለመታደስ እግዚአብሔርን ለምኑት፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
እንደ አንድ አትሌት ሌሎች ሰዎች ሕይወታችሁንና አፈፃፀማችሁን በሚመለከት በሚያወሩበት ዓለም ውስጥ ነው የምትኖሩት፡፡ይህ የ11 ቀናት ዕቅድ እግዚአብሔር እናንተን እንደ ልጅ በመቁጠር ለእናንተ የሰጠውን ነገር እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡የሚሰጠው ተስፋ ያለው ሕይወትን፤ደህነትን፤ሠላምንና እገዛን ነው፡፡በእነዚህ ብርቱና ሕይወት ለዋጭ የሆኑ አስተሳሰቦችን የታጠቁ አትሌቶች ልዩ ይሆናሉ፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/