1ኛ ጴጥሮስ: የ5 ቀናት የንባብ ዕቅድናሙና

በዘጸዓት መፅሐፍ ላይ እግዚአብሔር ለህዝቡ እርሱን ከታዘዙት የእርሱ የክብር ዕቃ እንዲሁም ይህን ዓለም የመባረኪያ የተለየ የካህናት መንግስት እንደሚሆኑ ይናገራቸዋል፡፡ ጴጥሮስ የእግዚአብሔርን የቀደመ ጥሪ በማንሳት ይህንንም ለእስራኤል ብቻ ሳይሆን በኢየሱስ ላመኑት ሁሉ ተግባራዊ ሲያደርገው እናያለን፡፡ ጴጥሮስ እኛ የንጉስ ካህናትና የክብር ዕቃዎች ብቻ ሳንሆን የአዲሱ ቤተ መቅደስ ህያዋን ድንጋዮች ነን ብሎ ጨምሮ ይነግረናል፡፡ በእስራኤል ቤተ መቅደስ ማለት ህዝብ እግዚአብሔርን የሚያገኝበትና መስዋዕት የሚያቀርብበት ነው፡፡ አሁን ግን ቤተ መቅደስ መንፈሳዊ እውነት ነው ይኸውም ልክ እንደ እስራኤል የምንለይበት፣ እንደ አዲስ ካህናት ህይወታችንንና ኑሮአችንን ለሌሎች በረከት ይሆን ዘንድ የምንሰዋበት ነው፡፡
እያደገ እና አለምአቀፍ የሆነው ይህ ቤተመቅደስ የጀመረው በኢየሱስ ነው፡፡ እርሱ የማዕዘን ራስ ነው፡፡ ያለእርሱ መስዋዕትነት እና ምሳሌነት በህዝቡ በኩል አለምን ለመባረክ ያለው የእግዚአብሔር አዲሱ እቅድ ከንቱ ይሆናል፡፡ ጴጥሮስ ሲናገር እኛ በተቀደሰ ሕይወት ስንኖር በረከትን የምናስተላልፍአዲስ የመሰብሰቢያ ቦታን ያቀፍን “ሕያዋን ድንጋዮች” ነን በማለት ነው፡፡
እኛ ከእግዚአብሔር ጋር እየገነባን ያለነው ይህ ህያው ህንፃ የተገነባው በመገፋት ነው፡፡ ኢየሱስ ቤተ-መቅደሳችን፣ ካህናችን እንዲሁም ሁሉን በሁሉ የሆነ መስዋዕታችንና ለዚህም የሞተልን ነው፡፡ እንደ አዲስ፣ እንደ ተመረጠ ቤተ-መቅደስ እንዲሁም በኢየሱስ ደግሞ የንጉስ ካህናት ሆነን አሁን ባለው የሀይማኖት ስርዓታችን ላይ እንሰራለን። እንደ እግዚአብሔር ውድ ዕቃነት ወደ ብርሃን ተጠርተናል፤ ጨለማ ደግሞ ለሰው ሁሉ ይህንን ስለምንመሰክር ይጠላናል፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሔር መመረጥ ማለት መፃተኞች መሆንና እንግዶች መሆን ማለት ነው፡፡ ለእግዚአብሔር የተመረጥን ውድ መሆን ማለት ልክ የእኛ የማዕዘን ራስ እንደሆነው በዚህች ዓለም ደግሞ እንገፋለን፡፡
ነገር ግን ያ መሆን ስለተገባው ነው፡፡ የቅዱሱ መንግስት ዜጎች የአሮጌውን ምድራዊ ሀገር መሻትና ፍላጎት እምቢ ይላሉ፡፡ ይህ ደግሞ ስደትን አልፎ ተርፎም ሞትን ያመጣል፤ ኢየሱስም የሚያሳየን በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ እንደ ተወላጆች በመኖር ዜጎቻችን ከሙታን ሕይወትን ከሚፈጥሩት ይልቅ።
ጴጥሮስ አክሎም ይህ መንፈሳዊ እውነታ በገዓዱ ዓለም ስለሚኖረው ሚና ሦስት ምሳሌዎችን ይሰጠናል፡፡ ምሳሌዎቹም ከሮም ባለስልጣናት ተግዳሮት የገጠማቸው ክርስቲያን ዜጎች፤ ክርስቲያን ባሪያ ከማያምን ጌታው ጋር ስላለው ግንኙነት እንዲሁም ከማያምን ባሏ ስለተለየች አማኝ ሚስት ናቸው፡፡ እንደ ካህናት፣ እንደ ዜጎች እና እንደ እግዚአብሔር መንግስት ቤተ-መቅደስ በህዝባቸው መካከል፣ በስራቸውና በጋብቻቸው መፃተኞችና እንግዶች ናቸው፡፡ ጴጥሮስ እያንዳንዳቸው ስላቅ፣ መከራ እና መገለል እንደሚደርስባቸው ያውቃል። ጴጥሮስ የአዲሶች የእግዚአብሔር ምርጦች ሰዎች የመሥዋዕትነት ሕይወት ዓለምን እንደሚባርክ ግን ተስፋ አለው።
የኢየሱስ መከራና መገፋት ወደ ትንሳኤውና ወደ ደህንነታችን መርቶታል፡፡ የኢየሱስ እንደ እኛ ቤተ-መቅደስ፣ እንደ ካህን እና እንደ እግዚአብሔር ውድ ልጅ ነው ማለት ዓለም በሞላ ተባርካለች ማለት ነው፡፡ ጴጥሮስ ጋብቻ እንደሚያንሰራራ፣ ጌቶች ለባሪያዎቻቸው ንስሃ እንደሚገቡ ያውቃል፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ምርጦች የሆኑት መፃተኞች የዚህችን ዓለም ዜጎች ላለመምሰል እምቢ ብለው ይልቁንም የኢየሱስን ምሳሌነት ለመከተል ሲወስኑ መንግስታት ይንበረከካሉ፡፡
ምንም እንኳን ኢየሱስ በሮም አገዛዝ ውስጥ ቢኖርም እንዲሁም በፈሪሳውያኑ ክስ ቢገደልም ለእግዚአብሔር የታዘዘ በመሆኑ ግን ከሞት ተነስቷል፤ የሮማውያንን ኃይልና የፈሪሳውያንንም ውሸት ፀጥ አሰኝቷል፡፡ ኢየሱስ ሲሰቃይና እንደ ባሪያ በተገረፈ ጊዜ ያሰቃዩትን አልጠላም ይልቅ እንደ ካህን ምህረትን አቀረበላቸው! በእርሱ ታማኝነትና መስዋዕት ባሪያዎች ፃድቃን ሆኑ እንዲሁም ከቁስላቸው ተፈወሱ፡፡ ልክ ኢየሱስ ሙሽሪትን ሊያድናትና ንፅህት ሊያደርጋት እንደሞተ ሁሉ አማኝ የሆኑ ሚስቶችም በየዋህትና በመገዛት ባሎቻቸውን ማሸነፍ ይችላሉ፡፡
ኢየሱስ ምሳሌያችን ነው፡፡ ኢየሱስ እያመለከትን ያለው የእግዚአብሔር ህዝቦች በመስዋዕትነት እንደተመረጡ መፃተኞች፣ እንደ ንጉስ ካህናትና እንደ ክቡር ህዝብ ሲኖሩ ዓለም እንደምትባረክ፣ የሚያሰቃዩን እንደሚለወጡና እኛም ከውርደታችን እንደምንነሳ ነው፡፡
የእርሱ ህያው መቅደሱ እንሆን ዘንድ የመረጠንን እግዚአብሔርን ታይ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ዓይኖችህን ያብራልህ፡፡ የኢየሱስ መከራና ትንሳኤ እኛን ብቻ ሳይሆን በዙሪያችን ያሉትን ሊለውጥ የሚችል ህያው ተስፋ እንደሆነ ማየት ይሁንልህ፡፡
ስለዚህ እቅድ

ተስፋ ተኮር በሆነው ደብዳቤው ለመጀመሪያዋ ክፍለ ዘመን ቤተ-ክርስቲያን ጴጥሮስ በማመን፣ በመታዘዝ እና ፍርድና መከራ ሲገጥመን ፀንተን እንድንቆም ያበረታናል፡፡ ይህን የሚያሳስበን ምክንያት ደግሞ በክርስቶስ ማን እንደሆንን፣ ቅዱስ የሆነውን ኑሮ እንኖር ዘንድ ኃይል የሆነልንና ወደፊት ዘላለምን ለመውረስ የምንችል ነን በማለት ነው፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Spoken Gospel ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ http://www.spokengospel.com/