1ኛ ጴጥሮስ: የ5 ቀናት የንባብ ዕቅድናሙና

የክርስቲያን የሆኑ ሚስቶች፣ ባሪያዎች እንዲሁም ዜጎች ለኢየሱስ ባላቸው ታማኝነት ይጎዳሉ፡፡ ማድረግ የሚቻለው ደግሞ አፀፋውን መመለስ ነው፡፡ ጴጥሮስ ግን የሚለን ክፉ አድርጎ መከራ ከመቀበል ይልቅ መልካምን አድርጎ መከራ መቀበል ይሻላል እያለን ነው፡፡ ከሁሉም በላይ የእግዚአብሔር ህዝቦች ለዓለም በረከት እንዲሆኑ እንጂ እርግማን እንዲሆኑ አልተጠሩም፡፡ ጴጥሮስ መዝሙር 34ን በመጥቀስ መልካም ህይወት የሚከተላቸው ፊታቸውን ከክፋት የመለሱትን ብቻ ነው ይለናል፡፡ ኢየሱስን በመጥቀስ ደግሞ ጴጥሮስ የሚነግረን ስለ ፅድቅ መከራን የሚቀበሉ የተባረኩ ናቸው እያለን ነው፡፡ ፍትህ በሌለበት ሁኔታ መልካምን ማድረግ የኢየሱስ መንገድ ነው፡፡
ኢየሱስ ለከሳሾቹ አፀፋውን ከመመለስ ይልቅ እኛን ወደ እግዚአብሔር መገኘት አቀረበን፡፡ እኛ የዳንነው እንደዚህ ከሆነ ለከሳሾቻችን አፀፋችን ሊሆን የሚገባው እንዲሁ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የኢየሱስ ከሞት መነሳት የሮማውያንን ባለስልጣናት፣ ሞትንና ሲዖልን እንዳሳፈረ የእኛም የዋህነትና አክብሮት ተሳዳቢዎቻችንንና አሳዳጆቻችንን ሊያሸማቅቅ ይችላል፡፡
ከዚያም ጴጥሮስ ለህዝቡ በክፉ መንፈሳውያንና የምድር ስልጣናት እንዲሁም በእግዚአብሔር ህዝቦች መካከል ያለው ግጭት ገና ከጥንት የጀመረ መሆኑን ያሳስባቸዋል፡፡ ነገር ግን ያ ግጭት አሁንም ድረስ በተመሳሳይ ሁኔታ ቢኖርም አግዚአብሔር ግን የራሱ የሆኑትን በማዳን ክፉን ደግሞ ያሳፍራል፡፡ እግዚአብሔር ጎርፍን በላከ ጊዜ ኖኅና ቤተሰቡን ሲያድን ኃይላትን ግን አሳፍሯል፡፡ ልክ ኖኅ በጎርፍ ውሃ እንደዳነ እኛም በጥምቀት ወሃ እንድናለን፡፡ ልክ የኖኅ ዘመን ሰዎች ከመርከቡ በታች እንደሰጠሙ ኃይላትና ስልጣናትም ከኢየሱስ እግር በታች ሆነዋል፡፡ በክፉ ሁኔታ ውስጥ መልካምን ማድረግ ማለት የደህንነት መንገድ ነው፡፡
በክፉ መሰቃየት ግን ደግሞ በስልጣን መነሳት አዲሱ የኢየሱስ ተከታዮች መገለጫቸው ነው፡፡ አብረውን በሚኖሩ ሰዎች እንጠላለንአልፎ ተርፎም መከራን ልንቀበል እንችላለን፡፡ ነገር ግን ወንጌል ሲናገር ብንሞት እንኳን እንነሳለን ይለናል፡፡
ስለ ፅድቅ መከራን መቀበል እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ኢየሱስን እየመሰሉ ለመኖር የሚፈልጉ የኢየሱስ ተከታዮች መከራን መጠበቅ የግድ ይላቸዋል፡፡ ለሚሰቃዩቱ የኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ ዝም ብሎ ምሳሌ ብቻ ሳይሆን ቅድመ-ሁኔታ ነው፡፡ እንደ ኢየሱስ መከራን ስንቀበል ልክ እንደ እርሱ እንነሳለን፡፡ ስለ ክፉ ሳይሆን ስለ መልካም ነገር መከራን ስንቀበል አናፍርም፡፡ ለአሮጌው፣ ለክፉው እና በቀል ለተሞላበት የህይወት ስርዓት ያለምንም ፍርሃት ልንሞት እንችላለን ምክንያቱም እንደምንነሳ እናውቀዋለንና፡፡
ለአሮጌው መሻታችንም ልንሞት እንችላለን፡፡ በኖኅ ዘመን ለነበሩት ህዝቦች፣ በጴጥሮስ ዘመን ለነበሩት አህዛብ እንዲሁም በእኛም ዙሪያ በዚህ ዘመን ላሉቱ በወሲብ ፣ በመጠጥ እና በምኞት ባህል ውስጥ አለመቀላቀላችን እንግዳ ነው፡፡ በዙሪያችን እንዳሉቱ ሳይሆኑ እንደ ኢየሱስ ስንኖር ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና አካላዊ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል፡፡ጴጥሮስ ግን የሚያሳስበን ልክ ኢየሱስ በእኛ ኃጢአት መከራ እንደተቀበለና እንደተነሳ እንዲሁም ልክ ክፉ አድራጊዎች ከጎርፉ ስር እንደሰጠሙና ኖኅ ደግሞ እንደ ዳነ መልካም በመስራት መከራን መቀበል ወደ ትንሳኤና ወደ ትድግና ይመራል፡፡
የምትኖረው ክርስትናን የሚፃረር ህግ በሚወጣበት ሀገር ቢሆን፣ ወይም ደግሞ አጉል ምኞትን በሚያወድስ በጨዋነትላይግን በሚሳለቅባህል ውስጥ ቢሆን ወይምየኢየሱስተከታዮችንበሚጠላዓለምውስጥየምትኖርቢሆንትንሳኤበሁሉምቦታአለ። ማንኛውም መከራችን ደህንነታችንን ያረጋግጣል፤ እንዲሁም ማንኛውም ሞት በውስጡ ህይወት ተሸክሟል፡፡ ክርስቲያኖች በማይረዳቸው ዓለም ውስጥ ተጠቂዎች አይደሉም፤ ነገር ግን ልክ እንደ ኢየሱስ እኛ በሁሉም ኃይል ላይ አሸናፊዎች ነን፡፡ ለዚህም ነው መልካም በማድረግ መከራ መቀበል የሚሻለው፡፡
በፅድቅ የሚፈርደውን እግዚአብሔርን ታይ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ዓይኖችህን ያብራልህ፡፡ ኢየሱስ መልካምን በማድረግ መከራን እንደ ተቀበለ እኛንም ከእርሱ ጋር ከሞት ሊያስነሳን የሚችል የትንሳኤው አዳኝ እንደሆነ ማየት ይሁንልህ፡፡
ስለዚህ እቅድ

ተስፋ ተኮር በሆነው ደብዳቤው ለመጀመሪያዋ ክፍለ ዘመን ቤተ-ክርስቲያን ጴጥሮስ በማመን፣ በመታዘዝ እና ፍርድና መከራ ሲገጥመን ፀንተን እንድንቆም ያበረታናል፡፡ ይህን የሚያሳስበን ምክንያት ደግሞ በክርስቶስ ማን እንደሆንን፣ ቅዱስ የሆነውን ኑሮ እንኖር ዘንድ ኃይል የሆነልንና ወደፊት ዘላለምን ለመውረስ የምንችል ነን በማለት ነው፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Spoken Gospel ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ http://www.spokengospel.com/