YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘዳ​ግም 23

23
ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጉባኤ የሚ​ለይ ሁኔታ
1“ፍሬ ዘሩ የተ​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ አባለ ዘሩም የተ​ቈ​ረጠ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ። 2ዲቃላ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ፤#ዕብ. “ዲቃላ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጉባኤ አይ​ግባ እስከ ዐሥር ትው​ልድ ድረስ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጉባኤ አይ​ግባ” ይላል።
3“አሞ​ናዊ ወይም ሞዓ​ባዊ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ፤ እስከ ዐሥር ትው​ልድ ድረስ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ። 4ከግ​ብፅ በወ​ጣ​ችሁ ጊዜ እን​ጀ​ራና ውኃ ይዘው በመ​ን​ገድ ላይ አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​አ​ች​ሁ​ምና፥ ከመ​ስ​ጴ​ጦ​ምያ የቢ​ዖ​ርን ልጅ በለ​ዓ​ምን ዋጋ ሰጥ​ተው ይረ​ግ​ማ​ችሁ ዘንድ ተዋ​ው​ለ​ው​ባ​ች​ኋ​ልና። 5ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በለ​ዓ​ምን ይሰማ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወድ​ዶ​ሃ​ልና ርግ​ማ​ኑን ወደ በረ​ከት ለወ​ጠ​ልህ። 6በዘ​መ​ንህ ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሰላም እን​ደ​ሚ​ገ​ባ​ቸው አታ​ና​ግ​ራ​ቸው።
7“ኤዶ​ማ​ዊዉ ወን​ድ​ምህ ነውና አት​ጸ​የ​ፈው፤ ግብ​ፃ​ዊ​ዉ​ንም በሀ​ገሩ ስደ​ተኛ ነበ​ር​ህና አት​ጸ​የ​ፈው። 8ከእ​ነ​ር​ሱም በሦ​ስ​ተ​ኛው ትው​ልድ የሚ​ወ​ለዱ ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ይግቡ።
ሰፈ​ርን በን​ጽ​ሕና መጠ​በቅ
9“ጠላ​ቶ​ች​ህን ልት​ወጋ በወ​ጣህ ጊዜ ከክፉ ነገር ሁሉ ሰው​ነ​ት​ህን ጠብቅ። 10በእ​ና​ንተ ውስጥ ሌሊት በሚ​ሆ​ነው ርኵ​ሰት የረ​ከሰ ሰው ቢኖር፥ ከሰ​ፈር ወደ ውጭ ይውጣ፤ ወደ ሰፈ​ርም አይ​ግባ። 11በመ​ሸም ጊዜ ሰው​ነ​ቱን በውኃ ይታ​ጠብ፤ ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ወደ ሰፈር ይመ​ለስ። 12ወደ ሜዳም ትወ​ጣ​ባት ዘንድ ከሰ​ፈር ውጭ ቦታ ይኑ​ርህ። 13ከመ​ሣ​ር​ያ​ህም ጋር መቈ​ፈ​ሪያ ያዝ፤ ሜዳም በተ​ቀ​መ​ጥህ ጊዜ ትም​ስ​በ​ታ​ለህ፤ ዞረ​ህም ከአ​ንተ የወ​ጣ​ውን በአ​ፈር ትከ​ድ​ነ​ዋ​ለህ። 14አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ድ​ንህ፥ ጠላ​ቶ​ች​ህ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሊሰ​ጥህ በሰ​ፈ​ርህ ውስጥ ይሄ​ዳ​ልና ስለ​ዚህ ነው​ረኛ ነገር እን​ዳ​ያ​ይ​ብህ፥ ፊቱ​ንም ከአ​ንተ እን​ዳ​ይ​መ​ልስ ሰፈ​ርህ የተ​ቀ​ደሰ ይሁን።
ልዩ ልዩ ሕግ​ጋት
15“ከጌ​ታዉ ኰብ​ልሎ ወደ አንተ የተ​ጠ​ጋ​ውን ባሪያ ለጌ​ታው አሳ​ል​ፈህ አት​ስጥ። 16ከአ​ንተ ጋር ይኑር፤ በመ​ካ​ከ​ል​ህም በሚ​ወ​ድ​ዳት በአ​ን​ዲቱ ስፍራ ይቀ​መጥ፤ አን​ተም አታ​ስ​ጨ​ን​ቀው።
17“ከእ​ስ​ራ​ኤል ሴቶች ልጆች ሴት አመ​ን​ዝራ አት​ገኝ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወን​ዶች ልጆች ወንድ አመ​ን​ዝራ አይ​ገኝ።#ግእዙ “አልቦ ዘያ​ገ​ብእ ጸባ​ሕተ እም​ደ​ቂቀ እስ​ራ​ኤል ...” ብሎ ይጨ​ም​ራል። 18ስለ ተሳ​ል​ኸው ስእ​ለት ሁሉ የአ​መ​ን​ዝ​ራ​ዪ​ቱን ዋጋና የው​ሻ​ውን ዋጋ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አታ​ቅ​ርብ፤ ሁለ​ቱም በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሚ​ያ​ጸ​ይፉ ናቸ​ውና።
19“ለወ​ን​ድ​ምህ በወ​ለድ አታ​በ​ድር፤ የብር ወይም የእ​ህል፥ ወይም የማ​ና​ቸ​ው​ንም ነገር ሁሉ ወለድ አት​ው​ሰድ። 20ለእ​ን​ግ​ዳው በወ​ለድ አበ​ድር፤ ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልት​ወ​ር​ሳት በም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር በሥ​ራህ ሁሉ ይባ​ር​ክህ ዘንድ ለወ​ን​ድ​ምህ በወ​ለድ አታ​በ​ድር።
21“ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት በተ​ሳ​ልህ ጊዜ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ፈጽሞ ይሻ​ዋ​ልና፥ ኀጢ​አ​ትም ይሆ​ን​ብ​ሃ​ልና መክ​ፈ​ሉን አታ​ዘ​ግይ። 22ባት​ሳል ግን ኀጢ​አት የለ​ብ​ህም። 23በአ​ፍህ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃ​ድህ ተስ​ለ​ሃ​ልና ከከ​ን​ፈ​ርህ የወ​ጣ​ውን ታደ​ርግ ዘንድ ጠብቅ።
24“ወደ ባል​ን​ጀ​ራህ እርሻ በገ​ባህ ጊዜ እሸ​ቱን በእ​ጅህ ቀጥ​ፈህ ብላ፤#“ብላ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ወዳ​ል​ታ​ጨ​ደው ወደ ባል​ን​ጀ​ራህ እህል ግን ማጭድ አታ​ግባ። 25ወደ ባል​ን​ጀ​ራህ የወ​ይን ቦታ በገ​ባህ ጊዜ እስ​ክ​ት​ጠ​ግብ ድረስ ከወ​ይኑ ብላ፤ ወደ ዕቃህ ግን ከእ​ርሱ ምንም አታ​ግባ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in