መጽሐፈ ምሳሌ 9
9
የጥበብ ጥሪ
1ጥበብ ለራስዋ ቤቷን ሠራች፥
ሰባቱንም ምሰሶዎችዋን አቆመች።
2ፍሪዳዋን አረደች፥ የወይን ጠጅዋንም በማድጋዋ ጨመረች።
ማዕድዋን አዘጋጀች።
3አገልጋዮችዋን ልካ
በከፍተኛ ዐዋጅ ወደ ማዕድዋ ጠራች። እንዲህም አለች፦
4“አላዋቂ የሆነ ወደ እኔ ይምጣ፤”
አእምሮ የጎደላቸውንም እንዲህ አለች፦
5“ኑ፥ እንጀራዬን ብሉ፥
የጠመቅሁላችሁን የወይን ጠጅም ጠጡ።
6ስንፍናን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፥
በሕይወትም ትኖሩ ዘንድ ዕውቀትን ፈልጉ፥ በመረዳትም ዕውቀትን አቅኑ።”
7ክፉዎችን የሚያስተምር ለራሱ ውርደትን ይቀበላል፥
ኃጥእንም የሚገሥጽ ራሱን ያዋርዳል።
8ሰነፎችን አትገሥጽ እንዳይጠሉህ፥
ጠቢብን ገሥጽ ይወድድህማል።#ግእዝ “ሰነፍ ግን ይጠላሃል” የሚል ይጨምራል።
9ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤
ጻድቅንም አስተምረው፥ ዕውቀትንም ያበዛል።
10የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤
የቅዱሳንም ምክር ዕውቀት ነው፥ ሕግንም ማወቅ ለልብ ደግ ነው።
11በዚህ ሥርዐት ብዙ ዘመን ትኖራለህ፥
የሕይወትህም ዓመታት ይጨመሩልሃል።
12ልጄ ሆይ፥ ለራስህ ጠቢብ ብትሆን ለባልንጀራህም ጠቢብ ትሆናለህ፥
ክፉም ብትሆን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ።
# ቀጣዮቹ 7 መስመሮች በዕብ. የሉም። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚያዘጋጅ ሰው ይመስላል።
እርሱም የሚበርር ዎፍን እንደሚከተል ነው።
የወይኑ ቦታ መንገዱን ተወ፤
የሚሰማራባትን መንገድ ዘነጋ፤
ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥
ለጥም ወደ ተሠራች ምድርም ይሄዳል፤
የማያፈራና የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።
13ሰነፍና ነዝናዛ፥ እንጀራንም ያጣች ሴት
ኀፍረትን የማታውቅ ትሆናለች።
14በቤቷ ደጅ በአደባባይ
በወንበር ላይ በግልጥ ተቀምጣ፥
15በመንገድ የሚያልፉትን
አካሄዳቸውንም ያቀኑትን ትጠራለች።
16ከእነርሱ ወገን ሰነፍ የሆነው ወደ እርሷ ይቀርባል።
አእምሮ የጐደለውንም እንዲህ ብላ ታዝዘዋለች፦
17“የተሸሸገ እንጀራን አሰማምረህ ዳስስ።
ጣፋጭ የስርቆት ውኃንም ጠጣ፥”
18ነገር ግን እርሱ ከኀያላን ወገን በእርሷ ዘንድ የሚጠፉ እንዳሉ፥
# ቀጣዮቹ 8 መስመሮች በዕብ. የሉም። የሲኦል ወጥመድም በቤቷ እንደሚገኝ አያውቅም።
ነገር ግን ፈጥነህ ሂድ፥ በቦታዋም አትዘግይ፥
የባዕድን ውኃ እንደምትሻገር
በዐይንህ ወደ እርሷ መመልከትን አታዘውትር።
ከባዕድ ውኃ ራቅ፥
ብዙ ዘመን ትኖር ዘንድ
ከባዕድ ምንጭ ውኃ አትጠጣ።
የሕይወትህም ዓመታት ይጨመሩልሃል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 9: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in