1
የሉቃስ ወንጌል 23:34
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፦ “አባት ሆይ! የሚያደርጉትን ስለማያውቁ ይቅር በላቸው!” አለ። ወታደሮቹም ዕጣ ተጣጥለው የኢየሱስን ልብስ ተከፋፈሉ።
Uporedi
Istraži የሉቃስ ወንጌል 23:34
2
የሉቃስ ወንጌል 23:43
ኢየሱስም “በእውነት እልሃለሁ፤ ዛሬውኑ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ!” አለው።
Istraži የሉቃስ ወንጌል 23:43
3
የሉቃስ ወንጌል 23:42
ቀጥሎም ኢየሱስን፦ “ጌታ ሆይ! በመንግሥትህ ስትመጣ አስታውሰኝ!” አለው።
Istraži የሉቃስ ወንጌል 23:42
4
የሉቃስ ወንጌል 23:46
ኢየሱስም ድምፁን ከፍ አድርጎ፥ “አባት ሆይ! እነሆ! ነፍሴን በእጅህ ዐደራ እሰጣለሁ!” አለ፤ ይህንንም ካለ በኋላ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች።
Istraži የሉቃስ ወንጌል 23:46
5
የሉቃስ ወንጌል 23:33
ቀራንዮ ወይም የራስ ቅል ወደ ተባለ ስፍራም በደረሱ ጊዜ በዚያ ኢየሱስን ሰቀሉት፤ እንዲሁም ሁለቱን ወንጀለኞች በኢየሱስ ግራና ቀኝ ሰቀሉአቸው።
Istraži የሉቃስ ወንጌል 23:33
6
የሉቃስ ወንጌል 23:44-45
እነሆ፥ ይህ የሆነው ከቀኑ ስድስት ሰዓት ገደማ ነበር፤ ከዚያን ጊዜም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ። ፀሐይ ጨለመ፤ የቤተ መቅደስ መጋረጃም ከመካከሉ ተቀዶ ከሁለት ተከፈለ።
Istraži የሉቃስ ወንጌል 23:44-45
7
የሉቃስ ወንጌል 23:47
በዚያ የነበረው መቶ አለቃ፥ የሆነውን ነገር ባየ ጊዜ፥ “በእርግጥ ይህ ሰው ጻድቅ ኖሮአል!” ብሎ እግዚአብሔርን አከበረ።
Istraži የሉቃስ ወንጌል 23:47
Početna
Biblija
Planovi
Video zapisi