ዘፍጥረት 10
10
የኖኅ ልጆች ትውልድ
1የኖኅ ልጆች የሴም፣ የካምና የያፌት ትውልድ ይህ ነው፤ እነርሱም ራሳቸው ከጥፋት ውሃ በኋላ ወንዶች ልጆችን ወለዱ።
የያፌት ዝርያዎች
10፥2-5 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥5-7
2የያፌት ልጆች፣#10፥2 ልጆች ማለት ዘርዐ ትውልዶች ወይም ወራሾች ወይም ሕዝቦች ማለት ሊሆን ይችላል፤ እንዲሁ በ3፣ 4፣ 6፣ 7፣ 20-23፣ 29 እና 31 ይገኛል።
ጎሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሜሼኽ፣ ቴራስ።
3የጎሜር ልጆች፦
አስከናዝ፣ ሪፋት፣ ቶጋርማ።
4የያዋን ልጆች፦
ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም፣ ሮድኢ። 5ከእነዚህም በየነገዳቸው፣ በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች፣ በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ።
የካም ዝርያዎች
10፥6-20 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥8-16
6የካም ልጆች፦
ኵሽ፣ ምጽራይም፣#10፥6 13ትንም ጨምሮ ግብጽን ያመለክታል። ፉጥ፣ ከነዓን ናቸው።
7የኵሽ ልጆች፦
ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማ፣ ሰብቃታ ናቸው።
የራዕማ ልጆች፦
ሳባ፣ ድዳን ናቸው።
8ኵሽ የናምሩድን አባት ነበረ፤
እርሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኀያል ጦረኛ ሆነ። 9በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ዐዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም፣ “በእግዚአብሔር ፊት እንደ ናምሩድ ብርቱ ዐዳኝ” ይባል ነበር። 10የግዛቱም የመጀመሪያ ከተሞች፦ ባቢሎን፣ ኦሬክ፣ አርካድና ካልኔ ናቸው፤ እነዚህ በሰናዖር#10፥10 ወይም ኦሬክና አርካድ፣ ሁሉም#10፥10 ባቢሎን ነው። ምድር ነበሩ። 11ከዚያም ምድር ወደ አሦር ወጥቶ ነነዌን፣ ርኆቦትን፣#10፥11 ወይም ነነዌ ከነከተማዋ አደባባዮች ካለህን 12እንዲሁም በነነዌና በካለህ መካከል ሬስን ቈረቈረ፤ ታላቁንም ከተማ መሠረተ።
13ምጽራይም#10፥13 ወይም ግብጽ ተብሎ ሊተረጐም ይችላል።፦
የሉዳማውያን፣ የዐናሚማውያን፣ የላህቢያውያን፣ የነፍተሂማውያን፣ 14የፈትሩሲማውያን፣ ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው፣ የከስሉሂማውያንና የቀፍቶሪማውያን አባት ነበረ።
15ከነዓንም፦
የበኵር ልጁ#10፥15 ወይም ከሲዶናውያን የመጀመሪያው የሲዶን፣ የኬጢያውያን፣ 16የኢያቡሳውያን፣ የአሞራውያን፣ የጌርጌሳውያን፣ 17የኤዊያውያን፣ የዐርካውያን፣ የሲኒውያን፣ 18የአራዴዎያውያን፣ የሰማሪናውያንና የአማቲያውያን አባት ነበረ።
ከጊዜ በኋላ የከነዓን ጐሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ፤ 19የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል እስከ ጋዛ ይደርሳል፤ ከዚያም በሰዶም በኩል ገሞራን፣ አዳማንና ስቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል።
20እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የካም ዝርያዎች ናቸው።
የሴም ዝርያዎች
10፥21-31 ተጓ ምብ – ዘፍ 11፥10-27፤ 1ዜና 1፥17-27
21ለያፌት ታላቅ ወንድም#10፥21 ወይም ሴም፣ የ…ታላቅ ወንድም ለሴም ደግሞ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የዔቦር ልጆች ሁሉ ቅደመ አያት ነው።
22የሴም ልጆች፦
ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ናቸው።
23የአራም ልጆች፤
ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሜሼኽ።#10፥23 ሰብዓ ሊቃናትና 1ዜና 1፥17 ይመ፤ ዕብራይስጡ ማሽ ይለዋል።
24አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤#10፥24 ከዕብራይስጡ ጋራ ተመሳሳይ ሲሆን ሰብዓ ሊቃናት ግን የቃይናን አባት፣ ቃይናንም የ…አባት ነበረ ይላል።
ሳላም ዔቦርን ወለደ።
25ለዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤
አንደኛው ልጅ በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለ ነበር ፋሌቅ#10፥25 ፋሌቅ ማለት ክፍፍል ማለት ነው። ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።
26ዮቅጣንም፦
አልሞዳድን፣ ሣሌፍን፣ ሐስረሞትን፣ ያራሕን፣ 27ሀዶራምን፣ አውዛልን፣ ደቅላን፣ 28ዖባልን፣#10፥28 አንዳንድ የዕብራይስጥ ቅጆችና የሱርስቱ ትርጕም (እንዲሁም ዘፍ 10፥28 ይመ) ከዚህ ጋራ ይስማማል፤ ብዙ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን ዒባል ይላሉ። አቢማኤልን፣ ሳባን፣ 29የኦፊር፣ የኤውላጥ፣ የዮባብ አባት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው።
30መኖሪያ ስፍራቸውም እስከ ሶፋር ድረስ ይዘልቃል።
31እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የሴም ዝርያዎች ናቸው።
32የኖኅ ወንዶች ልጆች ጐሣዎች እንደ ትውልዳቸው በየነገዳቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውሃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ የተሠራጩት ከእነዚሁ ነው።
موجودہ انتخاب:
ዘፍጥረት 10: NASV
سرخی
شئیر
کاپی
کیا آپ جاہتے ہیں کہ آپ کی سرکیاں آپ کی devices پر محفوظ ہوں؟ Sign up or sign in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.