ኦሪት ዘፍጥረት 35
35
ያዕቆብ በቤትኤል
1 #
ዘፍ. 28፥11-17። እግዚአብሔርም ያዕቆብን አለው፦ “ተነሥተህ ወደ ቤቴል ውጣ፥ በዚያም ኑር፥ ከወንድምህ ከዔሳው ፊት በሸሸህ ጊዜ ለተገለጠልህ ለእግዚአብሔርም መሠውያውን ሥራ።” 2ስለዚህ ያዕቆብ ለቤተሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፦ “እንግዶቹን አማልክት ከመካከላችሁ አስወግዱ ንጹሐንም ሁኑ፥ ልብሳችሁንም ለውጡ፥ 3ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ፥ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው ለእግዚአብሔር መሠውያን እሠራለሁ።” 4እነርሱም በእጃቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት ሁሉ፥ እንዲሁም በጆሮአቸውም ያሉትን ጉትቾች ለያዕቆብ ሰጡት፥ ያዕቆብም በሴኬም አጠገብ ካለችው የባሉጥ ዛፍ በታች ቀበራቸው። 5ተነሥተውም ሄዱ፥ የእግዚአብሔርም ፍርሃት በዙሪያቸው ባሉት ከተሞች ሁሉ ወደቀ፥ የያዕቆብንም ልጆች ለማሳደድ አልተከተሉአቸውም። 6ያዕቆብም፥ እርሱ ከእርሱ ጋርም የነበሩት ሰዎች ሁሉ፥ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሎዛ መጡ፥ እርሷም ቤቴል ናት። 7በዚያም መሠዊያውን ሠራ፥ የዚያንም ቦታ ስም “ኤልቤቴል”#35፥7 “የቤትኤል አምላክ” ማለት ነው። ብሎ ጠራው፥ እርሱ ከወንድሙ ፊት በሸሸበት ጊዜ እግዚአብሔር በዚያ ተገልጦለት ነበርና። 8የርብቃ ሞግዚት ዲቦራም ሞተች፥ በቤቴልም ከባሉጥ ዛፍ በታች ተቀበረች፥ ስሙም “አሎንባኩት”#35፥8 “የለቅሶ ወርካ” ማለት ነው። ተብሎ ተጠራ።
9እግዚአብሔርም ለያዕቆብ ከፓዳን-ኣሪም ከተመለስ በኋላ እንደገና ተገለጠለት፥ ባረከውም። 10#ዘፍ. 32፥28።እግዚአብሔርም፦ “ስምህ ያዕቆብ ነው፥ ከእንግዲህም ወዲህ፥ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ፥ ስምህ ያዕቆብ ተብሎ አይጠራ፥” አለው። ስሙንም እስራኤል ብሎ ጠራው። 11#ዘፍ. 17፥4-8።እግዚአብሔርም አለው፦ “ሁሉን ቻይ#35፥11 በዕብራይስጥ “ኤልሻዳይ” ማለት ነው። አምላክ እኔ ነኝ፥ ብዛ፥ ተባዛም፥ ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል፥ ነገሥታትም ከጉልበትህ ይወጣሉ። 12ለአብርሃምና ለይስሐቅም የሰጠኋትን ምድር ለአንተ እሰጣለሁ፥ ከአንተም በኋላ ለዘርህ ምድሪቱን እሰጠለሁ።” 13እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ከተነጋገረበት ስፍራ ወደ ላይ ወጣ። 14#ዘፍ. 28፥18፤19።ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ቦታ የድንጋይ ዐምድ አኖረ፤ የመጠጥ መሥዋዕትንም በእርሱ ላይ አፈሰሰ፥ ዘይትንም አፈሰሰበት። 15ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የተነጋገረበትን ያን ቦታ ቤቴል ብሎ ጠራው።
የብንያም ልደት እና የራሔል ሞት
16ከቤቴልም ተነሡ፥ ወደ ኤፍራታም ሊደርሱ ጥቂት ሲቀራቸው ራሔልን ምጥ ያዛት፥ በምጡም ተጨነቀች። 17ምጡም ባስጨነቃት ጊዜ አዋላጂቱ፦ “አትፍሪ፥ ይኸኛው ደግሞ ወንድ ልጅ ይሆንሻልና” አለቻት። 18እርሷም ስትሞት ነፍስዋ በምትወጣበት ጊዜ ስሙን “ቤንኦኒ”#35፥18 “የሐዘኔ ልጅ” ማለት ነው። ብላ ጠራችው፥ አባቱ ግን ብንያም አለው። 19ራሔልም ሞተች፥ ወደ ኤፍራታ በምትወስድም መንገድ ተቀበረች፥ እርሷም ቤተልሔም ናት። 20ያዕቆብም በመቃብርዋ ላይ ሐውልት አቆመ፥ እርሱም እስከ ዛሬ የራሔል የመቃብርዋ ሐውልት ነው።
የሮቤል በዝሙት መጸየፍ
21እስራኤልም ከዚያ ተነሣ፥ ድንኳኑንም ከዔዴር ግንብ ባሻገር ተከለ። 22#ዘፍ. 49፥4።እስራኤልም በዚያች አገር በተቀመጠ ጊዜ ሮቤል ሄደ የአባቱንም ቁባት ባላን ተገናኛት፥ እስራኤልም ሰማ።
ዐሥራ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች
የያዕቆብም ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው፥ 23የልያ ልጆች፥ የያዕቆብ በኩር ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፥ 24የራሔል ልጆች፥ ዮሴፍና ብንያም ናቸው። 25የራሔል አገልጋይ የነበረችው የባላ ልጆች፥ ዳንና ንፍታሌም ናቸው። 26የልያ ባርያ የዚልፋ ልጆችም፥ ጋድ፥ አሴር ናቸው። እነዚህ በፓዳን-ኣሪም በሶርያ የተወለዱለት የያዕቆብ ልጆች ናቸው።
የይስሐቅ ሞት
27 #
ዘፍ. 13፥18። ያዕቆብም ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ መምሬ፥ አብርሃምና ይስሐቅ እንግዶች ሆነው ወደ ተቀመጡባት፥ ወደ ቂርያት-አርባ፥ እርሷም ኬብሮን ወደምትባለው መጣ።
28የይስሐቅም ዕድሜ መቶ ሰማንያ ዓመት ሆነ። 29ይስሐቅም ነፍሱን ሰጠ፥ ሞተም፥ ሸምግሎ ዕድሜንም ጠግቦ ወደ ወገኖቹ ተከማቸ፥ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት።
موجودہ انتخاب:
ኦሪት ዘፍጥረት 35: መቅካእኤ
سرخی
شئیر
کاپی
کیا آپ جاہتے ہیں کہ آپ کی سرکیاں آپ کی devices پر محفوظ ہوں؟ Sign up or sign in