YouVersion Logo
تلاش

ኦሪት ዘፍጥረት 36

36
የዔሳው ሚስቶች እና በከንዓን የተወለዱ ልጆቹ
1የዔሳው ትውልድ ይህ ነው፥ እርሱም ኤዶም ነው። 2#ዘፍ. 26፥34።ዔሳው ከከነዓን ልጆች ሚስቶችን አገባ፥ የኬጢያዊውን የዔሎንን ልጅ ዓዳን፥ የሒዋዊው የፅብዖን ልጅ ዓና የወለዳትን ኦሆሊባማን፥ 3#ዘፍ. 28፥9።የእስማኤልን ልጅ የነባዮትን እኅት ባሴማትን። 4ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደች፥ ባሴማትም ራዑኤልን ወለደች፥ 5ኦሆሊባማም የዑሽን፥ ያዕላምን፥ ቆሬን ወለደች። በከነዓን ምድር የተወለዱለት የዔሳው ልጆች እነዚህ ናቸው።
የዔሳው ወደ ሌላ ቦታ መዘዋወር
6ዔሳውም ሚስቶቹን፥ ወንዶች ልጆቹንና ሴቶች ልጆቹን፥ ቤተሰቡንም ሁሉ፥ እንስሶቹንም ሁሉ፥ በከነዓንም ሀገር ያገኘውን ንብረቱን ሁሉ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ። 7ከብታቸው ስለ በዛ በአንድነት ይቀመጡ ዘንድ አልቻሉም፥ በእንግድነት የተቀመጡባትም ምድር ከከብታቸው ብዛት የተነሣ ልትበቃቸው አልቻለችም። 8ዔሳውም በሴይር ተራራ ተቀመጠ፥ ዔሳው ኤዶም ነው።
የዔሳው ዘሮች በሴይር
9በሴይር ተራራ የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት የዔሳው ትውልድም ይህ ነው። 10የዔሳው ልጆች ስም ይህ ነው፥ የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝ፥ የዔሳው ሚስት የባሴማት ልጅ ረዑኤል። 11የኤልፋዝም ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ቴማን፥ ኦማር፥ ስፎ፥ ጋታም፥ ቄናዝ። 12ቲምናዕም ለዔሳው ልጅ ለኤልፋዝ ቁባት ነበረች፥ አማሌቅንም ለኤልፋዝ ወለደችለት፥ የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጆች እነዚህ ናቸው። 13የረዑኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፦ ናሐት፥ ዘራሕ፥ ሻማና ሚዛ፤ እነዚህም የዔሳው ሚስት ባሴማት ልጆች ናቸው። 14የፅብዖን ልጅ የዓና ልጅ የኦሆሊባማ፥ የዔሳው ሚስት፥ ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ለዔሳውም የዑሽ፥ ያዕላምና፥ ቆሬን ወለደች።
የኤዶም የነገድ አለቆች
15የዔሳው መጀመሪያ ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፥ የዔሳው ልጆች አለቆች እነዚህ ናቸው፥ የቴማን አለቃ፥ ኦማር አለቃ፥ ስፎ አለቃ፥ ቄናዝ አለቃ፥ 16ቆሬ አለቃ፥ ገዕታም አለቃ፥ አማሌቅ አለቃ፥ በኤዶም ምድር የኤልፋዝ አለቆች እነዚህ ናቸው፥ እነዚህ የዓዳ ልጆች ናቸው። 17የዔሳው ልጅ የረዑኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ናሐት አለቃ፥ ዘራሕ አለቃ፥ ሻማ አለቃ፥ ሚዛህ አለቃ፥ በኤዶም ምድር የረዑኤል ልጆች አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እነዚህም የዔሳው ሚስት የባሴማት ልጆች ናቸው። 18የዔሳው ሚስት የኦሆሊባማ ልጆች እነዚህ ናቸው፦ የዑሽ አለቃ፥ ያዕላም አለቃ፥ ቆሬ አለቃ፥ የዔሳው ሚስት የዓና ልጅ የኦሆሊባማ አለቆች እነዚህ ናቸው። 19እነዚህ ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና አለቆቻቸው ናቸው።
በሖራውያን የሴይር ዘሮች
20በዚያች አገር የተቀመጡ የሖሪው የሴይር ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ሎጣን፥ ሾባል፥ ፅብዖን፥ ዓናና፥ 21ዲሶን፥ ኤጽር፥ ዲሳን፥ እነዚህ በኤዶም ምድር የሖሪው የሴይር ልጆች አለቆች ናቸው። 22የሎጣን ልጆችም ሖሪ፥ ሄማን ናቸው፥ የሎጣንም እኅት ቲምናዕ ናት። 23የሾባል ልጆችም፥ ዓልዋን፥ ማናሐት፥ ዔባል፥ ስፎ፥ ኦናም ናቸው። 24የፅብዖን ልጆችም፦ አያና ዓና ናቸው። ይህ ዓና የአባቱን የፅብዖንን አህዮች ሲጠብቅ በበረሓ ውስጥ የፍል ውሃ ምንጮችን ያገኘ ነው። 25የዓና ልጅ ዲሾን የተባለው ነው፤ ሴት ልጁም ኦሆሊባማ ትባላለች። 26የዲሾን ልጆች ሔምዳን፥ ኤሽባን፥ ይትራንና፥ ከራን ናቸው። 27የኤጽር ልጆች ቢልሃን፥ ዛዕዋንና፥ ዓቃን ናቸው። 28የዲሻን ልጆች ዑፅና አራን ናቸው። 29የሖሪ አለቆች እነዚህ ናቸው፥ ሎጣን አለቃ፥ ሾባል አለቃ፥ ፅብዖን አለቃ፥ ዓና አለቃ፥ 30የዲሾን አለቃ፥ ኤጽር አለቃ፥ ዲሻን አለቃ፥ በሴይር ምድር አለቆች የሆኑ የሖሪ አለቆቹ እነዚህ ናቸው።
የኤዶም ነገሥታት
31በእስራኤል ልጆች ላይ ንጉሥ ከመኖሩ በፊት በኤዶም አገር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው። 32የበዖር ልጅ ቤላዕ በኤዶም ነገሠ፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ናት። 33ቤላዕ ሞተ፥ በስፍራውም የባሶራው የዛራ ልጅ ዮባብ ነገሠ። 34ዮባብም ሞተ፥ በስፍራውም የቴማኒው አገር ሑሻም ነገሠ። 35ሑሻምም ሞተ፥ በስፍራውም የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ሜዳ የመታ የቤዳድ ልጅ ሃዳድ ነገሠ፥ የከተማውም ስም ዓዊት ተባለ። 36ሃዳድም ሞተ፥ በስፍራውም የማሥሬቃው ሠምላ ነገሠ። 37ሠምላም ሞተ፥ በስፍራውም በወንዝ አጠገብ ካለችው ከርሆቦት ሻኡል ነገሠ። 38ሻኡልም ሞተ፥ በስፍራውም የዓክቦር ልጅ በኣል-ሐናን ነገሠ። 39የዓክቦር ልጅ በኣል-ሐናንም ሞተ፥ በስፍራውም ሃዳር ነገሠ፥ የከተማውም ስም ፋዑ ነው፥ ሚስቱም የሜዛሃብ ልጅ ማጥሬድ የወለደቻት መሄጣብኤል ትባል ነበር።
ተጨማሪ የኤዶም የነገድ አለቆች
40የዔሳውም የአለቆቹ ስም በወገናቸው፥ በስፍራቸውም፥ በስማቸው ይህ ነው፦ ቲምናዕ አለቃ፥ ዓልዋ አለቃ፥ የቴት አለቃ፥ 41ኦሆሊባማ አለቃ፥ ኤላ አለቃ፥ ፊኖን አለቃ፥ 42ቄኔዝ አለቃ፥ ቴማን አለቃ፥ ሚብጻር አለቃ፥ 43ማግዲኤል አለቃ፥ ዒራም አለቃ፤ እነዚህ በግዛታቸው ምድር በየመኖሪያቸው የኤዶም አለቆች ናቸው። የኤዶማውያን አባት ዔሳው ነው።

سرخی

شئیر

کاپی

None

کیا آپ جاہتے ہیں کہ آپ کی سرکیاں آپ کی devices پر محفوظ ہوں؟ Sign up or sign in