1
የዮሐንስ ወንጌል 6:35
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤ በእኔ የሚያምንም በፍጹም አይጠማም።
So sánh
Khám phá የዮሐንስ ወንጌል 6:35
2
የዮሐንስ ወንጌል 6:63
ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋስ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው፤ ሕይወትም ነው።
Khám phá የዮሐንስ ወንጌል 6:63
3
የዮሐንስ ወንጌል 6:27
ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን የለዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው መብል ሥሩ፤ ይህም የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ነው፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”
Khám phá የዮሐንስ ወንጌል 6:27
4
የዮሐንስ ወንጌል 6:40
የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፤ ወልድን አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኝ ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።”
Khám phá የዮሐንስ ወንጌል 6:40
5
የዮሐንስ ወንጌል 6:29
ኢየሱስ መልሶ “የእግዚአብሔር ሥራ ይህ ነው፤ ይህም እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው፤” አላቸው።
Khám phá የዮሐንስ ወንጌል 6:29
6
የዮሐንስ ወንጌል 6:37
አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላስወጣውም፤
Khám phá የዮሐንስ ወንጌል 6:37
7
የዮሐንስ ወንጌል 6:68
ስምዖን ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ! ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘለዓለም ሕይወት ቃል አለህ፤
Khám phá የዮሐንስ ወንጌል 6:68
8
የዮሐንስ ወንጌል 6:51
እኔ ከሰማይ የወረደው ሕያው እንጀራ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘለዓለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።”
Khám phá የዮሐንስ ወንጌል 6:51
9
የዮሐንስ ወንጌል 6:44
የላከኝ አብ ካልሳበው በቀር ወደ እኔ መምጣት የሚችል የለም፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።
Khám phá የዮሐንስ ወንጌል 6:44
10
የዮሐንስ ወንጌል 6:33
የእግዚአብሔር እንጀራ ከሰማይ የሚወርድ ለዓለምም ሕይወትን የሚሰጥ ነውና፤” አላቸው።
Khám phá የዮሐንስ ወንጌል 6:33
11
የዮሐንስ ወንጌል 6:48
እኔ የሕይወት እንጀራ ነኝ።
Khám phá የዮሐንስ ወንጌል 6:48
12
የዮሐንስ ወንጌል 6:11-12
ኢየሱስም እንጀራውን ያዘ፤ አመስግኖም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለተቀመጡት ሰዎች ሰጡአቸው፤ እንዲሁም ከዓሣው በፈለጉት መጠን። ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን “አንድም እንኳን እንዳይጠፋ የተረፈውን ቁርስራሽ አከማቹ፤” አላቸው።
Khám phá የዮሐንስ ወንጌል 6:11-12
13
የዮሐንስ ወንጌል 6:19-20
ሃያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ከቀዘፉ በኋላም፥ ኢየሱስ በባሕር ላይ እየተራመደ ወደ ታንኳይቱ ሲቀርብ አይተው ፈሩ። እርሱ ግን “እኔ ነኝ፤ አትፍሩ፤” አላቸው።
Khám phá የዮሐንስ ወንጌል 6:19-20
Trang chủ
Kinh Thánh
Kế hoạch
Video