1
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 4:17
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ከዚህ በኋላ እኛ በሕይወት የምንገኘው ጌታን በአየር ላይ ለመገናኘት ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ ለዘለዓለምም ከጌታ ጋር እንሆናለን።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 4:16
የትእዛዝ ድምፅ፥ የመላእክት አለቃ ድምፅ፥ የእግዚአብሔር እምቢልታም ይሰማል፤ ጌታ ራሱም በእነዚህ ታጅቦ ከሰማይ ይወርዳል፤ በክርስቶስ አምነው የሞቱትም አስቀድመው ይነሣሉ።
3
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 4:3-4
የእግዚአብሔር ፈቃድ እናንተ እንድትቀደሱና ከዝሙት እንድትርቁ ነው። ከእናንተ እያንዳንዱ ሚስቱን በቅድስናና በክብር ጠብቆ መያዝን ይወቅ።
4
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 4:14
ኢየሱስ እንደ ሞተና ከሞትም እንደ ተነሣ እናምናለን፤ ስለዚህ በኢየሱስ አምነው የሞቱትን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋል።
5
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 4:11
በጸጥታም ለመኖር እንድትጣጣሩ እና የራሳችሁን ጉዳይ እንድታስቡ ከዚህ በፊት እንዳዘዝናችሁም በገዛ እጃችሁ እንድትሠሩ ነው።
6
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 4:7
እግዚአብሔር የጠራን በቅድስና እንድንኖር ነው እንጂ በርኲሰት እንድንኖር አይደለም።
Home
Bible
Plans
Videos