1
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:17
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም የሚነሣብሽን ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የጌታ አገልጋዮች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል ጌታ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:10
ተራሮች ይፈልሳሉ፥ ኮረብቶችም ይወገዳሉ፤ ቸርነቴ ግን ከአንቺ ዘንድ አይፈልስም የሰላሜም ቃል ኪዳን አይወገድም፥ ይላል የሚራራልሽ ጌታ።
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:4
አታፍሪምና አትፍሪ፤ አትዋረጂምና አትደንግጪ፤ የሕፃንነትሽንም እፍረት ትረሺዋለሽ፥ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም።
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:5
ፈጣሪሽ ባልሽ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ ነው፤ የእስራኤልም ቅዱስ ታዳጊሽ ነው፥ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል።
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:2
የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፥ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ።
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:13
ልጆችሽም ሁሉ ከጌታ የተማሩ ይሆናሉ፥ የልጆችሽም ሰላም ብዙ ይሆናል።
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:8
በጥቂት ቁጣ ለቅጽበተ ዐይን ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፥ በዘለዓለምም ቸርነት እምርሻለሁ፥ ይላል ታዳጊሽ ጌታ።
8
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:7
ጥቂት ጊዜ ተውሁሽ፥ በታላቅም ምሕረት እሰበስብሻለሁ።
9
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:9
ይህ ለኔ እንደ ኖኅ ውኃ ነው፤ የኖኅ ውኃ ደግሞ በምድር ላይ እንዳያልፍ እንደ ማልሁ፥ እንዲሁ አንቺን እንዳልቈጣ እንዳልዘልፍሽም ምያለሁ።
10
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:12
የግንብሽንም ጉልላት በቀይ ዕንቁ፥ በሮችሽንም በሚያብረቀርቅ ዕንቁ፥ ዳርቻሽንም ሁሉ በከበሩ ድንጋዮች እሠራለሁ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች