መዝሙር 115
115
መዝሙር 115
115፥4-11 ተጓ ምብ – መዝ 135፥15-20
1ለእኛ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለእኛ ሳይሆን፣
ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህ፣
ለስምህ ክብርን ስጥ።
2አሕዛብ፣ “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ?
3አምላካችንስ በሰማይ ነው፤
እርሱ ደስ የሚለውን ያደርጋል።
4የእነርሱ ጣዖታት ግን የሰው እጅ ያበጃቸው፣
ብርና ወርቅ ናቸው።
5አፍ አላቸው፤ አይናገሩም፤
ዐይን አላቸው፤ አያዩም፣
6ጆሮ አላቸው፤ አይሰሙም፤
አፍንጫ አላቸው፤ አያሸትቱም፤
7እጅ አላቸው፤ አይዳስሱም፤
እግር አላቸው፤ አይሄዱም፤
በጕሮሯቸውም ድምፅ አይፈጥሩም።
8እነዚህን የሚያበጁ፣
የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።
9የእስራኤል ቤት ሆይ፤ በእግዚአብሔር ታመኑ፤
ረዳታቸውና ጋሻቸው እርሱ ነው።
10የአሮን ቤት ሆይ፤ በእግዚአብሔር ታመኑ፤
ረዳታቸውና ጋሻቸው እርሱ ነው።
11እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ፤ በእግዚአብሔር ታመኑ፤
ረዳታቸውና ጋሻቸው እርሱ ነው።
12 እግዚአብሔር ያስበናል፤ ይባርከናልም፤
እርሱ የእስራኤልን ቤት ይባርካል፤
የአሮንንም ቤት ይባርካል።
13 እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሁሉ፣
ትልቁንም ትንሹንም ይባርካል።
14 እግዚአብሔር እናንተንና ልጆቻችሁን፣
በባርኮቱ ያብዛችሁ።
15ሰማይንና ምድርን በፈጠረ፣
በእግዚአብሔር የተባረካችሁ ሁኑ።
16ሰማየ ሰማያት የእግዚአብሔር ናቸው፤
ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።
17 እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑት የሞቱት አይደሉም፤
ወደ ዝምታው ዓለም የሚወርዱም አይደሉም።
18ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣
እግዚአብሔርን የምንባርክ እኛ ነን።
እግዚአብሔር ይመስገን።#115፥18 ዕብራይስጡ ሃሌ ሉያ ይላል።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.