መዝሙር 116

116
መዝሙር 116
1የልመናዬን ድምፅ ሰምቷልና፣
እግዚአብሔርን ወደድሁት።
2ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና፣
በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ።
3የሞት ወጥመድ ያዘኝ፤
የሲኦልም#116፥3 ዕብራይስጡ መቃብር ይላል። ጣር አገኘኝ፤
ጭንቅና ሐዘን አሸነፈኝ።
4እኔም የእግዚአብሔርን ስም ጠራሁ፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ ነፍሴን ታድናት ዘንድ እለምንሃለሁ” አልሁ።
5 እግዚአብሔር ቸርና ጻድቅ ነው፤
አምላካችን መሓሪ ነው።
6 እግዚአብሔር አላዋቂዎችን ይጠብቃል፤
እጅግ ተቸግሬ ሳለሁ አዳነኝ።
7ነፍሴ ሆይ፤ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፤
እግዚአብሔር መልካም አድርጎልሻልና።
8አንተ ነፍሴን ከሞት፣
ዐይኔን ከእንባ፣
እግሮቼን ከመሰናከል አድነሃልና።
9እኔም በሕያዋን ምድር፣
እግዚአብሔር ፊት እመላለሳለሁ።
10“እጅግ ተጨንቄአለሁ” ባልሁበት ጊዜ እንኳ፣#116፥10 ወይም ያኔ እንኳ
እምነቴን ጠብቄአለሁ።
11ግራ በተጋባሁ ጊዜ፣
“ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው” አልሁ።
12ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣
እግዚአብሔር ምን ልክፈለው?
13የመዳንን ጽዋ አነሣለሁ፤
እግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።
14በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣
ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ።
15የቅዱሳኑ ሞት፣
እግዚአብሔር ፊት የተከበረ ነው።
16 እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ በእውነት ባሪያህ ነኝ፤
እኔ የሴት ባሪያህ#116፥16 ታማኝ አገልጋይህ ወይም ታማኝ ልጅህ ልጅ፣ ባሪያህ ነኝ፤
ከእስራቴም ፈታኸኝ።
17ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤
እግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።
18በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣
ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ፤
19ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ይህን በመካከልሽ፣
እግዚአብሔር ቤት አደባባይ አደርጋለሁ።
ሃሌ ሉያ።#116፥19 አንዳንዶች እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ።

Currently Selected:

መዝሙር 116: NASV

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ