መዝሙረ ዳዊት 127

127
1የዕርገት መዝሙር።
ጌታ ቤትን ካልሠራ፥
ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፥
ጌታ ከተማን ካልጠበቀ፥
ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።
2 # መክ. 2፥24። እናንተ የመከራን እንጀራ የምትበሉ፥
ማለዳ መነሣታችሁ፥ አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው።
እርሱ ለሚወዱት እንቅልፍን ይሰጣልና።
3 # መዝ. 115፥14፤ 128፥3፤ ዘዳ. 28፥11፤ ምሳ. 17፥6። እነሆ፥ ልጆች የጌታ ስጦታ ናቸው፥
የማሕጸንም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው።
4በኃያል እጅ እንዳሉ ፍላጾች፥
የጐልማስነት ልጆች እንዲሁ ናቸው።
5ከእነርሱ ዘንድ ምኞቱን የሚፈጽም ሰው የታደለ ነው፥
ጠላቶቻቸውን በአደባባይ በተናገሩ ጊዜ እርሱ አያፍርም።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ