መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 27
27
ዳዊት በፍልስጥኤም መካከል
1ዳዊትም በልቡ፥ “አንድ ቀን በሳኦል እጅ እሞታለሁ፤ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ምድር ከመሸሸ በቀር የሚሻለኝ የለም፤ ሳኦልም በእስራኤል አውራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተዋል፤ እንዲሁም ከእጁ እድናለሁ” አለ። 2ዳዊትም ከእርሱም ጋር የነበሩት ስድስቱ መቶ ሰዎች ተነሥተው ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አሜህ ልጅ ወደ አንኩስ አለፉ። 3ዳዊትና ሰዎቹም እያንዳንዳቸው ከነቤተሰቡ ከአንኩስ ጋር በጌት ተቀመጡ፤ ከዳዊትም ጋር ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት አቤግያ ሁለቱ ሚስቶቹ ነበሩ። 4ለሳኦልም ዳዊት ወደ ጌት እንደ ኰበለለ ነገሩት፤ ከዚያም በኋላ ደግሞ አልፈለገውም።
5ዳዊትም አንኩስን፥ “አገልጋይህ በዐይንህ ፊት ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ በዚህ ሀገር ከከተሞችህ በአንዲቱ የምቀመጥበት ስፍራ ስጠኝ፤ ስለ ምን እኔ አገልጋይህ ከአንተ ጋር በንጉሥ ከተማ እቀመጣለሁ?” አለው።። 6በዚያም ቀን አንኩስ ሴቄላቅን ሰጠው፤ ስለዚህም ሴቄላቅ እስከ ዛሬ ድረስ ለይሁዳ ንጉሥ ሆነች። 7ዳዊትም በፍልስጥኤማውያን ሀገር የተቀመጠበት የዘመን ቍጥር አራት ወር#ዕብ. “አንድ ዓመት ከአራት ወራት” ይላል። ነበረ።
8ዳዊትና ሰዎቹም ወጥተው በጌሴራውያንና#ዕብ. “ጌርዛውያንን” ይጨምራል። በአማሌቃውያን ላይ አደጋ ጣሉ፤ እነዚህንም ቅጽር ባላቸው በጌላምሱርና በአኔቆንጦን እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ተቀምጠው አገኙአቸው። 9ዳዊትም ሀገሪቱን መታ፤ ወንድም ሆነ፥ ሴትም ሆነ፥ ማንንም በሕይወት አልተወም፤ በጎችንና ላሞችን፥ አህያዎችንና ግመሎችን፥ ልብስንም ማረከ፤ ተመልሶም ወደ አንኩስ መጣ። 10አንኩስም ዳዊትን፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” አለው፤ ዳዊትም፥ “በይሁዳ ደቡብ፥ በያሴሜጋ ደቡብ፥ በቄኔዛውያን ደቡብ ላይ ዘመትን” አለው። 11ዳዊት እንዲህ አደረገ፤ በፍልስጥኤማውያንም ሀገር በሚቀመጥበት ዘመን ሁሉ ልማዱ ይህ ነበረ ብለው እንዳይናገሩብን ብሎ ዳዊት ወደ ጌት ያመጣቸው ዘንድ ወንድም ሆነ ሴትም ሆነ ማንንም በሕይወት አልተወም። 12አንኩስም፥ “በሕዝቡ በእስራኤል ዘንድ እጅግ የተጠላ ሆኖአል፤ ስለዚህም ለዘለዓለም ባሪያ ይሆነኛል” ብሎ ዳዊትን አመነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 27: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ