የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ዳን​ኤል 2

2
የና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ሕልም
1ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም በነ​ገሠ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት ሕልም አለመ፤ መን​ፈ​ሱም ታወከ፤ ሕል​ሙ​ንም ዘነ​ጋው።#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ዕን​ቅ​ልፍ ከእ​ርሱ ራቀ” ይላል። 2ንጉ​ሡም ሕል​ሙን እን​ዲ​ነ​ግ​ሩት የሕ​ልም ተር​ጓ​ሚ​ዎ​ቹ​ንና አስ​ማ​ተ​ኞ​ቹን፥ መተ​ተ​ኞ​ቹ​ንና ከለ​ዳ​ው​ያ​ኑ​ንም ይጠሩ ዘንድ አዘዘ፤ እነ​ር​ሱም ገብ​ተው በን​ጉሡ ፊት ቆሙ። 3ንጉ​ሡም፥ “ሕልም አል​ሜ​አ​ለሁ፤ መን​ፈ​ሴም ታወ​ከ​ብኝ፤ ሕል​ሜ​ንም ዘነ​ጋ​ሁት” አላ​ቸው። 4ከለ​ዳ​ው​ያ​ኑም ንጉ​ሡን በሱ​ር​ስት ቋንቋ፥ “ንጉሥ ሆይ! ለዘ​ለ​ዓ​ለም ኑር፤ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ሕል​ም​ህን ንገር፤ እኛም ፍቺ​ውን እን​ነ​ግ​ር​ሃ​ለን” ብለው ተና​ገ​ሩት። 5ንጉ​ሡም መለሰ፤ ከለ​ዳ​ው​ያ​ኑ​ንም፥ “ነገሩ ከእኔ ዘንድ ርቆ​አል፤ ሕል​ሙ​ንና ፍቺ​ውን ባታ​ስ​ታ​ው​ቁኝ፥ ትገ​ደ​ላ​ላ​ችሁ፤ ቤቶ​ቻ​ች​ሁም የጉ​ድፍ መጣያ ይደ​ረ​ጋሉ። 6ሕል​ሙ​ንና ፍቺ​ውን ግን ብት​ነ​ግ​ሩኝ፥ ከእኔ ዘንድ ስጦ​ታና ዋጋ፥ ብዙ ክብ​ርም ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ሕል​ሙ​ንና ፍቺ​ውን ንገ​ሩኝ” አላ​ቸው። 7ሁለ​ተ​ኛም ጊዜ መል​ሰው፥ “ንጉሡ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ሕል​ሙን ይን​ገር፥ እኛም ፍቺ​ውን እን​ና​ገ​ራ​ለን” አሉት። 8ንጉ​ሡም መልሶ፥ “ነገሩ ከእኔ ዘንድ እንደ ራቀ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና ጊዜ​ውን እን​ደ​ም​ታ​ስ​ረ​ዝሙ እኔ አው​ቃ​ለሁ። 9ሕል​ሙ​ንም አሁን ባት​ነ​ግ​ሩኝ አንድ ፍርድ አለ​ባ​ችሁ፥#“አንድ ፍርድ አለ​ባ​ችሁ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። ጊዜ​ውን ለማ​ሳ​ለፍ የሐ​ሰ​ት​ንና የተ​ን​ኰ​ልን ቃል#“የተ​ን​ኰ​ልን ቃል” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። ልት​ነ​ግ​ሩኝ አዘ​ጋ​ጅ​ታ​ች​ኋል፤ ስለ​ዚህ ሕል​ሙን ንገ​ሩኝ፤ ፍቺ​ው​ንም መና​ገር እን​ደ​ም​ት​ችሉ አው​ቃ​ለሁ።” 10ከለ​ዳ​ው​ያ​ኑም በን​ጉሡ ፊት መል​ሰው፥ “የን​ጉ​ሡን ነገር ያሳይ ዘንድ የሚ​ችል ሰው በም​ድር ላይ የለም፤ ታላቅ ንጉ​ሥና አለቃ የሆነ እን​ደ​ዚያ ያለ ነገር የሕ​ልም ተር​ጓ​ሚ​ንና አስ​ማ​ተ​ኛን፥ ከለ​ዳ​ዊ​ንም የሚ​ጠ​ይቅ የለም። 11ንጉ​ሡም የሚ​ጠ​ይ​ቀው ነገር ከባድ ነው፤ መኖ​ሪ​ያ​ቸው ከሥጋ ለባሽ ጋር ካል​ሆነ ከአ​ማ​ል​ክት በቀር በን​ጉሡ ፊት የሚ​ያ​ሳ​የው ማንም የለም” አሉ። 12ያን​ጊዜ ንጉሡ ፈጽሞ ተቈጣ፤ የባ​ቢ​ሎ​ን​ንም ጠቢ​ባን ሁሉ ያጠፉ ዘንድ አዘዘ። 13ከን​ጉ​ሡም ዘንድ ትእ​ዛዝ ወጣ፤ ጠቢ​ባ​ን​ንም ይገ​ድሉ ዘንድ ጀመሩ፤ ዳን​ኤ​ል​ንና ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹ​ንም ይገ​ድ​ሉ​አ​ቸው ዘንድ ፈለ​ጉ​አ​ቸው።
14የዚ​ያን ጊዜም ዳን​ኤል የባ​ቢ​ሎ​ንን ጠቢ​ባን ይገ​ድል ዘንድ የወ​ጣ​ውን የን​ጉ​ሡን የዘብ አለቃ አር​ዮ​ክን በፈ​ሊ​ጥና በማ​ስ​ተ​ዋል#“በማ​ስ​ተ​ዋል” የሚ​ለው በግ​እዝ የለም። ተና​ገ​ረው፤ 15የን​ጉሡ የዘብ አለቃ አር​ዮ​ክን፥ “ይህ ጭንቅ ትእ​ዛዝ ከን​ጉሡ ዘንድ ስለ ምን ወጣ?” ብሎ ጠየ​ቀው፤ አር​ዮ​ክም ነገ​ሩን ለዳ​ን​ኤል ነገ​ረው። 16ዳን​ኤ​ልም ገብቶ ፍቺ​ውን ለን​ጉሡ የሚ​ያ​ስ​ታ​ው​ቅ​በት#ግእዝ “እስከ ሦስት ቀን” የሚል ይጨ​ም​ራል። ጊዜ ይሰ​ጠው ዘንድ ንጉ​ሡን ለመነ።
17የዚ​ያን ጊዜም ዳን​ኤል ወደ ቤቱ ገባ። ነገ​ሩ​ንም ለባ​ል​ን​ጀ​ሮቹ ለአ​ና​ን​ያና ለሚ​ሳ​ኤል፥ ለአ​ዛ​ር​ያም አስ​ታ​ወ​ቃ​ቸው። 18ዳን​ኤ​ልና ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹም ከቀ​ሩት ከባ​ቢ​ሎን ጠቢ​ባን ጋር እን​ዳ​ይ​ሞቱ ስለ​ዚህ ምሥ​ጢር ምሕ​ረ​ትን ከሰ​ማይ አም​ላክ ለመኑ።
19የዚ​ያን ጊዜም ምሥ​ጢሩ በሌ​ሊት ራእይ ለዳ​ን​ኤል ተገ​ለ​ጠ​ለት። ዳን​ኤ​ልም የሰ​ማይ አም​ላ​ክን አመ​ሰ​ገነ። 20እን​ዲ​ህም አለ፥ “ጥበ​ብና ምክር፥ ኀይ​ልም ለእ​ርሱ ነውና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ይመ​ስ​ገን። 21እሱም ጊዜ​ያ​ት​ንና ዘመ​ና​ትን ይለ​ው​ጣል፤ ነገ​ሥ​ታ​ትን ያስ​ነ​ሣል፤ ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ይሽ​ራል፤ ጥበ​ብን ለጠ​ቢ​ባን፥ ዕው​ቀ​ት​ንም ለአ​ስ​ተ​ዋ​ዮች ይሰ​ጣል። 22የጠ​ለ​ቀ​ው​ንና የተ​ሰ​ወ​ረ​ውን ይገ​ል​ጣል፤ በጨ​ለማ ያለ​ውን ያው​ቃል፤ ብር​ሃ​ንም ከእ​ርሱ ጋር አለ። 23አንተ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ፈጣሪ! እው​ቀ​ት​ንና ጥበ​ብን#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ጥበ​ብና ኀይል” ይላል። ሰጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥ የለ​መ​ን​ሁ​ህ​ንም ነግ​ረ​ኸ​ኛ​ልና፥ የን​ጉ​ሡን ሕልም፥ ትር​ጓ​ሜ​ው​ንም ገል​ጠ​ህ​ል​ኛ​ልና እገ​ዛ​ል​ሃ​ለሁ፤ አመ​ሰ​ግ​ን​ህ​ም​አ​ለሁ።”
ዳን​ኤል ሕል​ሙን ከነ​ት​ር​ጕሙ ለን​ጉሡ እንደ ነገረ
24ከዚ​ህም በኋላ ዳን​ኤል ንጉሡ የባ​ቢ​ሎ​ንን ጠቢ​ባን ያጠፋ ዘንድ ወደ አዘ​ዘው ወደ አር​ዮክ ገባ፤ “የባ​ቢ​ሎ​ንን ጠቢ​ባን አታ​ጥ​ፋ​ቸው፤ ወደ ንጉሡ አስ​ገ​ባኝ፥ እኔም ሕል​ሙ​ንና ፍቺ​ውን ለን​ጉሡ እነ​ግ​ረ​ዋ​ለሁ” አለው 25የዚ​ያን ጊዜም አር​ዮክ ዳን​ኤ​ልን ፈጥኖ ወደ ንጉሡ አስ​ገ​ባ​ውና፥ “ከይ​ሁዳ የም​ርኮ ልጆች ለን​ጉሡ ሕል​ሙ​ንና ፍቺ​ውን የሚ​ነ​ግ​ረ​ውን ሰው አግ​ኝ​ቼ​አ​ለሁ” አለው። 26ንጉ​ሡም መለሰ፤ ብል​ጣ​ሶ​ርም የሚ​ባ​ለ​ውን ዳን​ኤ​ልን፥ “ያየ​ሁ​ትን ሕል​ምና ፍቺ​ው​ንም ትነ​ግ​ረኝ ዘንድ ትች​ላ​ለ​ህን?” አለው። 27ዳን​ኤ​ልም በን​ጉሡ ፊት እን​ዲህ ሲል መለሰ፥ “ንጉሥ የሚ​ጠ​ይ​ቀው ይህ ምሥ​ጢር ለአ​ዋ​ቂ​ዎ​ችና ለፈ​ላ​ስ​ፎች፥ ለሟ​ር​ተ​ኞ​ችና ለጠ​ን​ቋ​ዮች የሚ​ገ​ለጥ አይ​ደ​ለም።” 28ነገር ግን ምሥ​ጢ​ርን የሚ​ገ​ልጥ አም​ላክ በሰ​ማይ ውስጥ አለ፤ እር​ሱም በኋ​ለ​ኛው ዘመን የሚ​ሆ​ነ​ውን ለን​ጉሡ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር አሳ​ይ​ቶ​ታል። በአ​ል​ጋህ ላይ የሆ​ነው ሕል​ምና የራ​ስህ ራእይ ይህ ነው። 29ንጉሥ ሆይ! ከአ​ንተ በኋላ የሚ​ሆ​ነው ምን እንደ ሆነ በአ​ል​ጋህ ላይ ታስብ ነበር፤ ምሥ​ጢ​ር​ንም የሚ​ገ​ል​ጠው የሚ​ሆ​ነ​ውን ነገር አሳ​ይ​ቶ​ሃል። 30ነገር ግን ይህ ምሥ​ጢር ለእኔ መገ​ለጡ ፍቺው ለን​ጉሡ ይታ​ወቅ ዘንድ፥ አን​ተም የል​ብ​ህን አሳብ ታውቅ ዘንድ ነው እንጂ በዚህ ዓለም ከአሉ ሰዎች ይልቅ በጥ​በብ ስለ በለ​ጥሁ አይ​ደ​ለም።
31“ንጉሥ ሆይ! አንተ አየህ፤ እነሆ ይኸ​ውም አንድ ታላቅ ምስል ነበር፤ እር​ሱም በፊ​ትህ ቆሞ ነበር፤ መል​ኩም ግሩም ነበር። 32የዚ​ህም ምስል ራስ ጥሩ ወርቅ፥ እጆቹ፥ ደረ​ቱና ክን​ዶ​ቹም ብር፥ ሆዱና ወገ​ቡም ናስ፤ 33ጭኖ​ቹም ብረት፥ እግ​ሮ​ቹም እኩሉ ብረት እኩ​ሉም ሸክላ ነበረ። 34እጅም ሳይ​ነ​ካው ታላቅ ድን​ጋይ ከተ​ራ​ራው ተፈ​ን​ቅሎ ከብ​ረ​ትና ከሸ​ክላ የሆ​ነ​ውን የም​ስ​ሉን እግ​ሮች እስከ መጨ​ረ​ሻው ሲመ​ታና ሲፈጭ አየህ። 35የዚ​ያን ጊዜም ብረ​ቱና ሸክ​ላው፥ ናሱና ብሩ፥ ወር​ቁም በአ​ን​ድ​ነት ተፈጨ፤ በመ​ከ​ርም ጊዜ በአ​ው​ድማ ላይ እን​ደ​አለ እብቅ ሆነ፤ ነፋ​ስም ወሰ​ደው፤ ቦታ​ውም አል​ታ​ወ​ቀም፤ ምስ​ሉ​ንም የመ​ታው ድን​ጋይ ታላቅ ተራራ ሆነ፤ ምድ​ር​ንም ሁሉ ሞላ።
36“ሕል​ምህ ይህ ነው፤ ፍቺ​ው​ንም በን​ጉሡ ፊት እና​ገ​ራ​ለሁ። 37ንጉሥ ሆይ! የሰ​ማይ አም​ላክ ጠን​ካራ መን​ግ​ሥ​ትን፥ ኀይ​ል​ንና ክብ​ርን የሰ​ጠህ የነ​ገ​ሥ​ታት ንጉሥ አንተ ነህ። 38የሰው ልጆች በሚ​ኖ​ሩ​በት ስፍራ ሁሉ የም​ድር አራ​ዊ​ትን፥ የሰ​ማይ ወፎ​ችን፥ የባ​ሕር ዓሣ​ዎ​ች​ንም በእ​ጅህ ሰጥ​ቶ​ሃል፤ ለሁ​ሉም ገዢ አድ​ርጎ ሹሞ​ሃል፤ የወ​ርቁ ራስ አንተ ነህ። 39ከአ​ን​ተም በኋላ ከአ​ንተ የሚ​ያ​ንስ ሌላ መን​ግ​ሥት ይነ​ሣል፤ እር​ሱም የብሩ ነው። ከዚ​ያም በኋላ በም​ድር ሁሉ ላይ የሚ​ገዛ ሌላ ሦስ​ተኛ መን​ግ​ሥት ይነ​ሣል፤ እር​ሱም የናሱ ነው። 40አራ​ተ​ኛ​ውም መን​ግ​ሥት ሁሉን እን​ደ​ሚ​ቀ​ጠ​ቅ​ጥና እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ቅቅ ብረት ይበ​ረ​ታል፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ሁሉ እን​ደ​ሚ​ፈጭ ብረት ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል፤ ይፈ​ጭ​ማል። 41እግ​ሮ​ቹና ጣቶ​ቹም እኩሉ ሸክላ፥ እኩ​ሉም ብረት ሆኖ እን​ደ​አ​የህ፥ እን​ዲሁ የተ​ከ​ፋ​ፈለ መን​ግ​ሥት ይሆ​ናል፤ ብረ​ቱም ከሸ​ክ​ላው ጋር ተደ​ባ​ልቆ እንደ አየ​ኸው፥ የብ​ረት ብር​ታት ለእ​ርሱ ይሆ​ናል። 42የእ​ግ​ሮ​ቹም ጣቶች እኩሉ ብረት፥ እኩ​ሉም ሸክላ እንደ ነበሩ፥ እን​ዲሁ መን​ግ​ሥቱ እኩሉ ብርቱ፥ እኩሉ ደካማ ይሆ​ናል። 43ብረ​ቱም ከሸ​ክ​ላው ጋር ተደ​ባ​ልቆ እን​ዳ​የህ፥ እን​ዲሁ ከሰው ዘር ጋር ይደ​ባ​ለ​ቃሉ፤ ነገር ግን ብረት ከሸ​ክላ ጋር እን​ደ​ማ​ይ​ጣ​በቅ እን​ዲሁ እርስ በር​ሳ​ቸው አይ​ጣ​በ​ቁም 44በእ​ነ​ዚ​ያም ነገ​ሥ​ታት ዘመን የሰ​ማይ አም​ላክ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የማ​ይ​ፈ​ርስ መን​ግ​ሥት ያስ​ነ​ሣል፤ ለሌላ ሕዝ​ብም የማ​ይ​ሰጥ መን​ግ​ሥት ይሆ​ናል፤ እነ​ዚ​ያ​ንም መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ድል ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለች፤ ታጠ​ፋ​ቸ​ው​ማ​ለች፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ትቆ​ማ​ለች። 45ድን​ጋ​ዩም እጅ ሳይ​ነ​ካው ከተ​ራራ ተፈ​ን​ቅሎ ብረ​ቱ​ንና ናሱን፥ ሸክ​ላ​ው​ንና ብሩን፥ ወር​ቁ​ንም ሲፈ​ጨው እንደ አየህ፥ እን​ዲሁ ከዚህ በኋላ የሚ​ሆ​ነ​ውን ታላቁ አም​ላክ ለን​ጉሡ አሳ​ይ​ቶ​ታል፤ ሕል​ሙም እው​ነ​ተኛ፥ ፍቺ​ውም የታ​መነ ነው።”
ንጉሡ፥ ዳን​ኤ​ልን እንደ አከ​በ​ረው
46የዚ​ያን ጊዜም ንጉሡ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በግ​ም​ባሩ ተደ​ፍቶ ለዳ​ን​ኤል ሰገ​ደ​ለት። ፈጽ​ሞም አከ​በ​ረው፥#“ፈጽ​ሞም አከ​በ​ረው” የሚ​ለው በግ​እዝ ብቻ። ገጸ በረ​ከ​ትም ሰጠው፤ መል​ካም መዓ​ዛም#ዕብ. “የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና ዕጣ​ኑን ...” ይላል። ያቀ​ር​ቡ​ለት ዘንድ አዘዘ። 47ንጉ​ሡም ዳን​ኤ​ልን፥ “ይህን ምሥ​ጢር ትገ​ልጥ ዘንድ ተች​ሎ​ሃ​ልና በእ​ው​ነት አም​ላ​ካ​ችሁ የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ፥ የነ​ገ​ሥ​ታ​ትም ጌታ፥ ምሥ​ጢ​ርም ገላጭ ነው” ብሎ ተና​ገ​ረው። 48ንጉ​ሡም ዳን​ኤ​ልን ከፍ ከፍ አደ​ረ​ገው፤ ብዙም ታላቅ ስጦታ ሰጠው፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም አው​ራ​ጃ​ዎች ሁሉ ላይ ሾመው፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም ጠቢ​ባን ሁሉ ላይ ዋነኛ አለቃ አደ​ረ​ገው። 49ዳን​ኤ​ልም ንጉ​ሡን ለመነ፤ እር​ሱም ሲድ​ራ​ቅ​ንና ሚሳ​ቅን፥ አብ​ደ​ና​ጎ​ንም በባ​ቢ​ሎን አው​ራጃ ሥራ ላይ ሾማ​ቸው፤ ዳን​ኤል ግን በን​ጉሡ አደ​ባ​ባይ ነበረ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ