የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 27

27
የመ​ሠ​ው​ያው አሠ​ራር
(ዘፀ. 38፥1-7)
1“ርዝ​መቱ አም​ስት ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት ክንድ መሠ​ዊ​ያን ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አድ​ርግ፤ አራት ማዕ​ዘ​ንም ይሁን፤ ከፍ​ታ​ውም ሦስት ክንድ ይሁን። 2በአ​ራ​ቱም ማዕ​ዘን ቀን​ዶ​ችን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ቀን​ዶቹ ሥረ-ወጥ ይሁኑ፤ በና​ስም ለብ​ጣ​ቸው። 3ለመ​ሠ​ዊ​ያው ክዳን ሥራ​ለት፤ መሸ​ፈ​ኛ​ውን፥ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ የሥጋ ሜን​ጦ​ዎ​ቹን፥ የእ​ሳት መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አድ​ርግ። ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ከናስ አድ​ርግ። 4ለመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም እንደ መረብ ሆኖ የተ​ሠራ የናስ መከታ አድ​ር​ግ​ለት፤ ለመ​ከ​ታ​ውም አራት የናስ ቀለ​በት በአ​ራት ማዕ​ዘኑ አድ​ር​ግ​ለት። 5መከ​ታ​ውም እስከ መሠ​ዊ​ያው እኩ​ሌታ ይደ​ርስ ዘንድ ከመ​ሠ​ዊ​ያው እር​ከን በታች አኑ​ረው። 6ለመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ችን ሠር​ተህ በናስ ለብ​ጣ​ቸው፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹም በቀ​ለ​በ​ቶች ውስጥ ይግቡ፤ 7መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ስት​ሸ​ከሙ መሎ​ጊ​ያ​ዎቹ በመ​ሠ​ዊ​ያው በሁ​ለት ወገን ይሁኑ። 8ሰሌ​ዳ​ውም ፍል​ፍል ይሁን፤ በተ​ራ​ራው እን​ዳ​ሳ​የ​ሁህ ምሳሌ እን​ዲሁ አድ​ርግ።
የቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አደ​ባ​ባይ
(ዘፀ. 38፥9-20)
9“ለድ​ን​ኳ​ኑም አደ​ባ​ባይ ሥራ፤ ከጥሩ በፍታ የተ​ሠሩ የአ​ደ​ባ​ባዩ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችም በደ​ቡብ በኩል ይሁኑ። የአ​ን​ዱም ወገን ርዝ​መት መቶ ክንድ ይሁን፤ 10ከናስ የተ​ሠሩ ሃያ ምሰ​ሶ​ዎ​ችና ሃያ እግ​ሮች ይሁ​ኑ​ለት፤ የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም ኩላ​ቦ​ችና ዘን​ጎች የብር ይሁኑ። 11እን​ዲ​ሁም በሰ​ሜን ወገን መቶ ክንድ ርዝ​መት ያላ​ቸው መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ ከናስ የተ​ሠሩ ሃያ ምሰ​ሶ​ዎች፥ ሃያም እግ​ሮች ይሁኑ፤ ለም​ሰ​ሶ​ዎ​ችም በብር የተ​ለ​በጡ ኩላ​ቦ​ችና ዘን​ጎች ይሁኑ። 12በም​ዕ​ራ​ብም ወገን ለአ​ደ​ባ​ባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ርዝ​መት ያላ​ቸው መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ ዐሥ​ርም ምሰ​ሶ​ዎች፥ ዐሥ​ርም እግ​ሮች ይሁ​ኑ​ለት። 13በም​ሥ​ራ​ቅም ወገን የአ​ደ​ባ​ባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ይሁን፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ችም ዐሥር፥ እግ​ሮ​ቹም ዐሥር ይሁኑ። 14በአ​ንድ ወገን የመ​ጋ​ረ​ጃ​ዎቹ ርዝ​መት ዐሥራ አም​ስት ክንድ ይሁን፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹም ሦስት፥ እግ​ሮ​ቹም ሦስት ይሁኑ። 15በሌ​ላ​ውም ወገን የመ​ጋ​ረ​ጃ​ዎቹ ርዝ​መት ዐሥራ አም​ስት ክንድ ይሆ​ናል፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹም ሦስት፥ እግ​ሮ​ቹም ሦስት ይሁኑ። 16ለአ​ደ​ባ​ባዩ ደጅም ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም ከቀ​ይም ግምጃ ከጥሩ በፍ​ታም በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ ሃያ ክንድ መጋ​ረጃ ይሆ​ናል፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹም አራት፥ እግ​ሮ​ቹም አራት ይሁኑ። 17በዙ​ሪ​ያ​ውም ያሉ የአ​ደ​ባ​ባዩ ምሰ​ሶ​ዎች ሁሉ በብር የተ​ለ​በጡ ይሁኑ፤ የብ​ርም ክባ​ሶች፥ የና​ስም እግ​ሮች ይሁ​ኑ​ላ​ቸው። 18የአ​ደ​ባ​ባዩ ርዝ​መት በየ​ገጹ መቶ ክንድ፥ ስፋ​ቱም በየ​ገጹ አምሳ ክንድ ይሁን፤ የመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም ከፍታ አም​ስት ክንድ ይሁን፤ መጋ​ረ​ጃ​ውም ከጥሩ በፍታ፥ እግ​ሮ​ቹም ከናስ የተ​ሠሩ ይሁኑ። 19ለማ​ገ​ል​ገል ሁሉ የድ​ን​ኳን ዕቃ ሁሉ፥ አው​ታ​ሮቹ ካስ​ማ​ዎ​ቹም ሁሉ፤ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ካስ​ማ​ዎች ሁሉ የናስ ይሁኑ።
የመ​ብ​ራቱ ዘይት
(ዘሌ. 24፥1-4)
20“አን​ተም መብ​ራ​ቱን ሁል ጊዜ ያበ​ሩት ዘንድ ለመ​ብ​ራት ተወ​ቅጦ የተ​ጠ​ለለ ጥሩ የወ​ይራ ዘይት እን​ዲ​ያ​መ​ጡ​ልህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እዘ​ዛ​ቸው። 21በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋ​ረጃ ውጭ አሮ​ንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያብ​ሩት፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃ​ቸው የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ