የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 27

27
ስለ ጢሮስ የወጣ ሙሾ
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ጢሮስ ሙሾ አድ​ርግ። 3በባ​ሕር መግ​ቢያ የም​ት​ኖር፥ በብ​ዙም ደሴ​ቶች ላይ ከሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ጋር ንግ​ድን የም​ታ​ደ​ርግ ጢሮ​ስን እን​ዲህ በላት፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ! አንቺ፦ በው​በት ፍጹም ነኝ ብለ​ሻል። 4ዳር​ቻሽ በባ​ሕር ውስጥ ነው፤ ልጆ​ች​ሽም#ዕብ. “ሠራ​ተ​ኞ​ችሽ” ይላል። ውበ​ት​ሽን ፈጽ​መ​ዋል። 5ሳን​ቃ​ዎ​ች​ሽን ሁሉ ከሳ​ኔር ጥድ ሠር​ተ​ዋል፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ሽ​ንም ይሠ​ሩ​ልሽ ዘንድ ከሊ​ባ​ኖስ ዝግ​ባን ወስ​ደ​ዋል። 6ከባ​ሳን ኮም​ቦል መቅ​ዘ​ፊ​ያ​ሽን ሠር​ተ​ዋል፤ መቅ​ደ​ስ​ሽ​ንም በዝ​ኆን ጥርስ ሠሩ፤ ከኪ​ቲም ደሴ​ቶች ዛፍም ቤቶ​ች​ሽን ሠር​ተ​ዋል። 7ዓላማ እን​ዲ​ሆ​ን​ልሽ ሸራሽ ከግ​ብፅ በፍ​ታና ከወ​ርቀ ዘቦ ተሠ​ር​ቶ​አል፤ መደ​ረ​ቢ​ያ​ሽም ከኤ​ሊሳ ደሴ​ቶች ሰማ​ያ​ዊና ቀይ ሐር ተሠ​ር​ቶ​አል። 8አለ​ቆ​ችሽ በሲ​ዶና ይኖሩ ነበር፤ የአ​ራድ ሰዎ​ችም ቀዛ​ፊ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ጢሮስ ሆይ! ጥበ​በ​ኞ​ችሽ በአ​ንቺ ዘንድ ነበሩ፤ የመ​ር​ከ​ቦ​ች​ሽም መሪ​ዎች ነበሩ። 9#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የቢ​ብ​ል​ያን ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና በአ​ንች ዘንድ የነ​በሩ ጥበ​በ​ኞች ጉባ​ኤ​ሽን ይረዱ ነበር ፤ የባ​ሕር መር​ከ​ቦች ሁሉና መር​ከ​በ​ኞ​ችም እስከ ሩቅ ምዕ​ራብ ድረስ ለአ​ንቺ ይነ​ግዱ ነበር” ይላል።በአ​ንቺ ውስጥ የነ​በሩ የጌ​ባል ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ጥበ​በ​ኞ​ችዋ ስብ​ራ​ት​ሽን ይጠ​ግኑ ነበር፤ ከአ​ን​ቺም ጋር ይነ​ግዱ ዘንድ የባ​ሕር መር​ከ​ቦች ሁሉና መር​ከ​በ​ኞ​ቻ​ቸው በመ​ካ​ከ​ልሽ ነበሩ። 10ፋር​ስና ሉድ፥ ሊብ​ያም#ዕብ. “ፉጥ” ይላል። በሠ​ራ​ዊ​ትሽ ውስጥ ሰል​ፈ​ኞ​ችሽ ነበሩ፤ ጋሻና ራስ ቍርም በአ​ንቺ ውስጥ ያን​ጠ​ለ​ጥሉ ነበር፤ እነ​ር​ሱም ክብ​ር​ሽን ሰጡ። 11የአ​ራድ ልጆ​ችና ሠራ​ዊ​ቶ​ችሽ በቅ​ጥ​ሮ​ችሽ ላይ በዙ​ሪያ ነበሩ፤ ገማ​ዳ​ው​ያ​ንም በግ​ን​ቦ​ችሽ ውስጥ ነበሩ፤ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ው​ንም በዙ​ሪያ በቅ​ጥ​ርሽ ላይ አን​ጠ​ለ​ጠሉ፤ ውበ​ት​ሽ​ንም ፈጽ​መ​ዋል።
12“ከኀ​ይ​ልሽ#ዕብ. “ከብ​ል​ጥ​ግ​ናሽ” ይላል። ሁሉ ብዛት የተ​ነሣ የተ​ር​ሴስ#ግሪኩ “የካ​ር​ቴጅ” ይላል። ሰዎች ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ገበ​ያ​ሽን ብር፥ ወር​ቅና ብረት፥ ቆር​ቆ​ሮና እር​ሳ​ስም አደ​ረጉ። 13ያዋ​ንና ቶቤል፥ ሞሳ​ሕም ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ንግ​ድ​ሽ​ንም በሰ​ዎች ነፍ​ሳ​ትና በናስ ዕቃ አደ​ረጉ። 14ከቴ​ር​ጋማ ቤትም የነ​በ​ሩት ሰዎች ፈረ​ሶ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን፥ በቅ​ሎ​ዎ​ች​ንም ወደ ገበ​ያሽ አመ​ጡ​ልሽ። 15የሮ​ድ​ያን ልጆ​ችም ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፥ ብዙ የሆኑ የደ​ስ​ያት ሰዎ​ችም የዝ​ኆን ጥርስ ይነ​ግ​ዱ​ልሽ ነበር፤ ከዚ​ያም የመጡ ሰዎች ዋጋ​ሽን ይሰ​ጡሽ ነበር። 16የሶ​ር​ያም ሰዎች ከገ​ን​ዘ​ብሽ ብዛት የተ​ነሣ ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፥ ከአ​ን​ቺም ጋር አንድ ከሆኑ ከብዙ ሰዎች ጋር ትነ​ግጂ ነበር፤ ነጭ ሐር​ንና ዕን​ቍን፥ ቀይ ሐር​ንና ወርቀ ዘቦን ከር​ከ​ዴን የሚ​ባል ዕን​ቍ​ንና ልባ​ን​ጃም የሚ​ባል ሽቱን ከተ​ር​ሴስ ያመ​ጡ​ልሽ ነበር፤ ገበ​ያ​ሽ​ንም ረዓ​ሙ​ትና ቆር​ኮር መሉት። 17ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤል ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ስን​ዴ​ንም ይሸ​ም​ቱ​ልሽ ነበር፤ ሰሊ​ሆ​ት​ንና በለ​ሶ​ንን፥ ዘይ​ት​ንና የተ​ወ​ደደ ማርን፥ ርጢ​ን​ንም ከአ​ንቺ ጋር አንድ ይሆኑ ዘንድ ሰጡሽ። 18ከሥ​ራሽ ብዛ​ትና ከብ​ል​ጽ​ግ​ናሽ ሁሉ ብዛት የተ​ነሣ የደ​ማ​ስቆ ሰዎች ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ በኬ​ል​ቦን የወ​ይን ጠጅ፥ በነ​ጭም የበግ ጠጕር ይነ​ግዱ ነበር። 19ዳንና ያዋን፤ ከኦ​ሴል የተ​ሠራ ብረ​ት​ንና ብር​ጕ​ድን፥ ቀረ​ፋ​ንም ያመ​ጡ​ልሽ ነበር። 20ድዳን በተ​መ​ረጡ እን​ስ​ሳ​ትና በሠ​ረ​ገ​ላ​ቸው፥ በክ​ብር ልብ​ስም ነጋ​ዴሽ ነበ​ረች። 21ዓረ​ብና የቄ​ዳር አለ​ቆች ሁሉ የእ​ጅሽ ነጋ​ዴ​ዎች ነበሩ፤ በግ​መ​ሎ​ችና በአ​ውራ በጎች፥ በፍ​የ​ሎ​ችም በእ​ነ​ዚህ ከአ​ንቺ ጋር ይነ​ግዱ ነበር። 22የሳ​ባና የራ​ዕማ ነጋ​ዴ​ዎች እነ​ዚህ ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ንግ​ድ​ሽን በጥሩ ሽቱና በከ​በረ ድን​ጋይ ሁሉ፥ በወ​ር​ቅም አደ​ረጉ። 23የካ​ራ​ንና የካኔ፥ የኤ​ደ​ንም ሰዎች ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ አሦ​ርና ኪል​ማ​ድም ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ። 24እነ​ዚህ በአ​ማረ ልብስ፥ በሰ​ማ​ያዊ ካባ፥ በወ​ርቀ ዘቦም፥ በዝ​ግባ በተ​ሠ​ራች፥ በገ​መ​ድም በታ​ሰ​ረች፥ በግ​ም​ጃም በተ​ሞ​ላች ሣጥን በገ​በ​ያሽ ይነ​ግዱ ነበር። 25የተ​ር​ሴስ መር​ከ​ቦች ሸቀ​ጥ​ሽን የሚ​ሸ​ከሙ ነበሩ፤ አን​ቺም ተሞ​ል​ተሽ ነበር፤ በባ​ሕ​ርም ውስጥ እጅግ ከበ​ርሽ።
26“ቀዛ​ፊ​ዎ​ችሽ ወደ ትልቁ ውኃ አመ​ጡሽ፤ የም​ሥ​ራቅ ነፋስ በባ​ሕር ውስጥ ሰበ​ረሽ። 27ኀይ​ል​ሽና ዋጋሽ፥ ንግ​ድ​ሽም፥ መር​ከ​በ​ኞ​ች​ሽም፥ መር​ከብ መሪ​ዎ​ች​ሽም፥ ሰባ​ራ​ሽን የሚ​ጠ​ግኑ ነጋ​ዴ​ዎ​ች​ሽም፥ በአ​ን​ቺም ዘንድ ያሉ ሰል​ፈ​ኞ​ችሽ ሁሉ በው​ስ​ጥሽ ከአ​ሉት ጉባኤ ሁሉ ጋር በወ​ደ​ቅ​ሽ​በት ቀን በባ​ሕር ውስጥ ይጠ​ፋሉ። 28ከጩ​ኸ​ትሽ የተ​ነሣ የመ​ር​ከ​ብሽ መሪ​ዎች ፍር​ሀ​ትን ፈሩ።#ዕብ. “ከመ​ር​ከብ መሪ​ዎች ጩኸት የተ​ነሣ በዙ​ሪ​ያሽ ያሉ ሁሉ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ” ይላል። 29ቀዛ​ፊ​ዎ​ችም ሁሉ፥ በመ​ር​ከብ የተ​ጫ​ኑ​ትም መር​ከብ መሪ​ዎ​ችም ሁሉ ከመ​ር​ከ​ቦ​ቻ​ቸው ይወ​ር​ዳሉ፤ በየ​ብ​ስም ላይ ይቆ​ማሉ፤ 30ድም​ፃ​ቸ​ው​ንም በአ​ንቺ ላይ ያሰ​ማሉ፤ ምርር ብለ​ውም ይጮ​ኻሉ፤ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ትቢያ ይነ​ሰ​ን​ሳሉ፤ አመ​ድም ያነ​ጥ​ፋሉ። 31ስለ አን​ቺም የራ​ሳ​ቸ​ውን ጠጕር ይላ​ጫሉ፤ ማቅም ያሸ​ር​ጣሉ፤ በነ​ፍ​ስም ምሬት ስለ አንቺ መራራ ልቅ​ሶን ያለ​ቅ​ሳሉ። 32ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ሙሾን ያሞ​ሹ​ል​ሻል፤ በባ​ሕር መካ​ከል እንደ ታወ​ከች እንደ ጢሮስ ያለ ማን ነበር? ይላሉ። 33በባ​ሕር ውስጥ ምን ያህል ዋጋ ታገኚ ነበር? በብ​ል​ጥ​ግ​ናሽ ብዛት ብዙ አሕ​ዛ​ብን አጠ​ገ​ብሽ፤ ከአ​ን​ቺም ጋር አንድ ከሆ​ኑት ለይ​ተሽ የም​ድ​ርን ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ባለ​ጸ​ጎች አደ​ረ​ግ​ሻ​ቸው። 34አሁን ግን በጥ​ልቅ ውኃ ውስጥ በባ​ሕር ተሰ​ብ​ረ​ሻል፤ ከአ​ንቺ ጋር አንድ የሆኑ ሁሉ በመ​ካ​ከ​ልሽ ወድ​ቀ​ዋል። ቀዛ​ፊ​ዎ​ች​ሽም ሁሉ ይወ​ድ​ቃሉ፤ 35በደ​ሴ​ቶች የሚ​ኖሩ ሁሉ አለ​ቀ​ሱ​ልሽ፤ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅግ ፈር​ተ​ዋል ፊታ​ቸ​ው​ንም ነጭ​ተው አለ​ቀሱ። 36የአ​ሕ​ዛብ ነጋ​ዴ​ዎ​ችም አፍ​ዋ​ጩ​ብሽ፤ አን​ቺም ፈጽ​መሽ ትጠ​ፊ​ያ​ለሽ፤ ከእ​ግ​ዲ​ህም ወዲያ እስከ ዘለ​ዓ​ለም አት​ኖ​ሪም።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ