የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 28

28
በጢ​ሮስ ንጉሥ ላይ የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የጢ​ሮ​ስን አለቃ እን​ዲህ በለው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ልብህ ኰር​ት​ዋል፥ አንተ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሕር መካ​ከል እን​ዲ​ቀ​መጥ እኔም ተቀ​ም​ጫ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና፤ አንተ ሰው ስት​ሆን ልብ​ህን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ ብታ​ደ​ር​ግም አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ህም። 3ከዳ​ን​ኤል ይልቅ አንተ ጥበ​በኛ ነህን? ብል​ሃ​ተ​ኞ​ችም በጥ​በ​ባ​ቸው አላ​ስ​ተ​ማ​ሩ​ህም። 4በጥ​በ​ብ​ህና በማ​ስ​ተ​ዋ​ልህ ብል​ጽ​ግ​ናን ለራ​ስህ አግ​ኝ​ተ​ሃ​ልን? ወር​ቅ​ንና ብር​ንም በግ​ምጃ ቤትህ ውስጥ ሰብ​ስ​በ​ሃ​ልን? 5በታ​ላቅ ጥበ​ብ​ህና በን​ግ​ድህ ብል​ጽ​ግ​ና​ህን አብ​ዝ​ተ​ሃል፤ በብ​ል​ጽ​ግ​ና​ህም ልብህ ኰር​ቶ​አል። 6ሰለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ልብ​ህን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፤ 7ስለ​ዚህ እነሆ የሌላ ሀገር ሰዎ​ችን፥ የአ​ሕ​ዛብ ጨካ​ኞ​ችን አመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ሰይ​ፋ​ቸ​ው​ንም በጥ​በ​ብህ ውበት ላይ ይመ​ዝ​ዛሉ፤ ክብ​ር​ህ​ንም ያረ​ክ​ሳሉ። 8ወደ ጕድ​ጓድ ያወ​ር​ዱ​ሃል፤ በሰ​ይ​ፍም ትሞ​ታ​ለህ፤ ሬሳ​ህ​ንም ወደ ባሕር ይጥ​ሉ​ታል። 9አንተ ሰው ስት​ሆን ለሚ​ገ​ድ​ሉህ ሰዎች፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ትላ​ቸ​ዋ​ለ​ህን? ሰው ነህ እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ህም። 10የሚ​ወ​ጉ​ህም ሰዎች ብዙ​ዎች ናቸው፤ ያል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትን ሰዎች ሞት ትሞ​ታ​ለህ፤ የሚ​ገ​ድ​ሉ​ህም ሰዎች ያል​ተ​ገ​ረ​ዙት ናቸው፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም ትሞ​ታ​ለህ። እኔ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”
11የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 12“የሰው ልጅ ሆይ! በጢ​ሮስ ንጉሥ ላይ ሙሾ አሙ​ሽ​በት፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጥበ​ብን የተ​ሞ​ላህ፥ ውበ​ት​ህም የተ​ፈ​ጸመ መደ​ም​ደ​ሚያ አንተ ነህ። 13በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነት በዔ​ድን ነበ​ርህ፤ የከ​በረ ዕን​ቍስ ሁሉ፥ ሰር​ድ​ዮን፥ ቶጳ​ዝ​ዮን፥ አል​ማዝ፥ ቢረሌ፥ መረ​ግድ፥ ኢያ​ሰ​ጲድ፥ ሰን​ፔር፥ በሉር፥ የሚ​ያ​ብ​ረ​ቀ​ርቅ ዕንቍ፥ ወር​ቅም ልብ​ስህ ነበረ፤ የከ​በ​ሮ​ህና የእ​ን​ቢ​ል​ታህ ሥራ በአ​ንተ ዘንድ ነበረ፤ በተ​ፈ​ጠ​ር​ህ​በ​ትም ቀን ተዘ​ጋ​ጅ​ተው ነበር። 14አንተ ልት​ጋ​ርድ የተ​ቀ​ባህ ኪሩብ ነበ​ርህ፤ በተ​ቀ​ደ​ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ላይ አኖ​ር​ሁህ፤ በእ​ሳት ድን​ጋ​ዮች መካ​ከል ተመ​ላ​ለ​ስህ። 15ከተ​ፈ​ጠ​ር​ህ​በት ቀን ጀም​ረህ በደል እስ​ከ​ሚ​ገ​ኝ​ብህ ድረስ በመ​ን​ገ​ድህ ፍጹም ነበ​ርህ። 16በን​ግ​ድ​ህም ብዛት ግፍ በው​ስ​ጥህ ተሞላ፤ ኀጢ​አ​ት​ንም ሠራህ፤ ስለ​ዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ጣል​ሁህ፤ የም​ት​ጋ​ርድ ኪሩብ ሆይ! ከእ​ሳት ድን​ጋ​ዮች መካ​ከል አጠ​ፋ​ሁህ። 17በው​በ​ትህ ምክ​ን​ያት ልብህ ኰር​ቶ​አል፤ ከክ​ብ​ርህ የተ​ነሣ ጥበ​ብ​ህን አረ​ከ​ስህ፤ በም​ድር ላይ ጣል​ሁህ፤ ያዩ​ህም፥ ይዘ​ብ​ቱ​ብ​ህም ዘንድ በነ​ገ​ሥ​ታት ፊት አሳ​ልፌ ሰጠ​ሁህ። 18በበ​ደ​ልህ ብዛት፥ በን​ግ​ድ​ህም ኀጢ​አት መቅ​ደ​ስ​ህን አረ​ከ​ስህ፤ ስለ​ዚህ እሳ​ትን ከው​ስ​ጥህ አው​ጥ​ቻ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋም በል​ታ​ሃ​ለች፤ በሚ​ያ​ዩ​ህም ሁሉ ፊት በም​ድር ላይ አመድ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ። 19በአ​ሕ​ዛ​ብም ውስጥ የሚ​ያ​ው​ቁህ ሁሉ ያለ​ቅ​ሱ​ል​ሃል፤ አን​ተም ለድ​ን​ጋጤ ሆነ​ሃል፤ እስከ ዘለ​ዓ​ለ​ምም አት​ኖ​ርም።”
20የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 21የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን ወደ ሲዶና አቅ​ን​ተህ ትን​ቢት ተና​ገ​ር​ባት፤ እን​ዲ​ህም በል፦ 22ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሲዶና ሆይ! እነሆ በአ​ንቺ ላይ ነኝ፤ በው​ስ​ጥ​ሽም እከ​ብ​ራ​ለሁ፤ ፍር​ድ​ንም በአ​ደ​ረ​ግ​ሁ​ብሽ ጊዜ፥ በተ​ቀ​ደ​ስ​ሁ​ብ​ሽም ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ። 23ቸነ​ፈ​ር​ንም በአ​ንቺ ላይ፥ ደም​ንም በጎ​ዳ​ናሽ ላይ እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ከዙ​ሪ​ያ​ሽም በላ​ይሽ ባለ ሰይፍ የተ​ወጉ በመ​ካ​ከ​ልሽ ይወ​ድ​ቃሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ። 24ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት የሚ​ወጋ እሾህ፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ከአሉ ከና​ቋ​ቸው ሁሉ የሚ​ያ​ቈ​ስል ኩር​ን​ችት አይ​ሆ​ንም፤ እኔም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ። 25ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ከተ​በ​ተ​ኑ​ባ​ቸው አሕ​ዛብ ዘንድ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብና በሕ​ዝብ ፊትም እቀ​ደ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለባ​ሪ​ያዬ ለያ​ዕ​ቆ​ብም በሰ​ጠ​ኋት ምድ​ራ​ቸው ይቀ​መ​ጣሉ። 26ተዘ​ል​ለ​ውም ይቀ​መ​ጡ​ባ​ታል፤ ቤቶ​ች​ንም ይሠ​ራሉ፤ ወይ​ኑ​ንም ይተ​ክ​ላሉ፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም በአሉ በሚ​ን​ቋ​ቸው ሁሉ ላይ ፍር​ድን በአ​ደ​ረ​ግሁ ጊዜ ተዘ​ል​ለው ይቀ​መ​ጣሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አም​ላክ እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ