የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 38

38
ጎግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሣ​ሪያ ሆኖ እን​ደ​ሚ​ነሣ
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን በጎግ ላይና በማ​ጎግ ምድር ላይ፥ በሮስ#“በሮስ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። በሞ​ሳ​ሕና በቶ​ቤል አለቃ ላይ አቅ​ና​በት፤ ትን​ቢ​ትም ተና​ገ​ር​በት፤ 3እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሮስ፥ የሞ​ሣ​ሕና የቶ​ቤል አለቃ ጎግ ሆይ! እነሆ! እኔ በአ​ንተ ላይ ነኝ። 4እመ​ል​ስ​ህ​ማ​ለሁ፤ በመ​ን​ጋ​ጋ​ህም ልጓም አገ​ባ​ብ​ሃ​ለሁ፤ አን​ተ​ንና ሠራ​ዊ​ት​ህን ሁሉ፥ ፈረ​ሶ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን፥ የጦር ልብስ የለ​በ​ሱ​ትን ሁሉ፥ ጋሻና ራስ ቍርን፥ ሰይ​ፍ​ንም የያ​ዙ​ትን ሁሉ አወ​ጣ​ለሁ። 5ፋር​ስ​ንና ኢት​ዮ​ጵ​ያን፥ ሊብ​ያ​ንም፥#ዕብ. “ፉጥ” ይላል። ከእ​ነ​ርሱ ጋር ጋሻና የራስ ቍርን የለ​በ​ሱ​ትን ሁሉ፥ 6ጎሜ​ር​ንና ከእ​ርሱ ጋር ያሉ​ትን ሁሉ፥ በሰ​ሜን ዳር​ቻም ያለ​ውን የቴ​ር​ጋ​ማን ቤትና ጭፍ​ሮ​ቹን ሁሉ፥ ብዙ​ዎ​ች​ንም ሕዝ​ቦች ከአ​ንተ ጋር አወ​ጣ​ለሁ።
7“አን​ተና ወደ አንተ የተ​ሰ​በ​ሰቡ ወገ​ኖ​ችህ ሁሉ ተዘ​ጋጁ፤ አን​ተም ራስ​ህን አዘ​ጋ​ጅ​ተህ ጠባቂ ሁና​ቸው። 8ከብዙ ዘመ​ንም በኋላ ትፈ​ለ​ጋ​ለህ፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም ባድማ በነ​በሩ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ ከብዙ ሕዝብ ውስጥ ወደ ተሰ​በ​ሰ​በች፥ ከሰ​ይፍ ወደ ተመ​ለ​ሰች ምድር ትገ​ባ​ለህ፤ እር​ስ​ዋም ከሕ​ዝብ ውስጥ ወጥ​ታ​ለች፤ ሁሉም በሰ​ላም ይቀ​መ​ጡ​በ​ታል። 9እንደ ዝናም ትወ​ጣ​ለህ፤ እንደ ደመ​ናም ምድ​ርን ትሸ​ፍን ዘንድ ትደ​ር​ሳ​ለህ፤ አን​ተም ከብዙ ሕዝ​ብና ሠራ​ዊት ጋር ትወ​ድ​ቃ​ለህ።”
10ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዚያ ቀን ነገር ወደ ልብህ ይገ​ባል፥ ክፉ አሳ​ብ​ንም ታስ​ባ​ለህ፤ እን​ዲ​ህም ትላ​ለህ፦ 11ወደ ጠፋች ሀገር እወ​ጣ​ለሁ፤ ተዘ​ል​ለው በሰ​ላም ወደ​ሚ​ኖሩ፥ ሁላ​ቸው ሳይ​ፈሩ ያለ ቅጥ​ርና ያለ መወ​ር​ወ​ሪያ፥ ያለ መዝ​ጊ​ያም ወደ​ሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ምድር እገ​ባ​ለሁ፤ 12ምር​ኮን ትማ​ርክ ዘንድ፥ ብዝ​በ​ዛ​ንም ትበ​ዘ​ብዝ ዘንድ፥ ባድ​ማም በነ​በሩ፥ አሁ​ንም ሰዎች በሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸው ስፍ​ራ​ዎች ላይ፥ ከአ​ሕ​ዛ​ብም በተ​ሰ​በ​ሰበ፥ ከብ​ትና ዕቃ​ንም በአ​ገኘ፥ በም​ድ​ርም መካ​ከል በተ​ቀ​መጠ ሕዝብ ላይ እጅ​ህን ትመ​ል​ሳ​ለህ። 13ሳባና ድዳን፥ የተ​ር​ሴ​ስም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የካ​ር​ታ​ግና” ይላል። ነጋ​ዴ​ዎች፥ መን​ደ​ሮ​ች​ዋም ሁሉ፦ ምር​ኮን ትማ​ርክ ዘንድ መጥ​ተ​ሃ​ልን? ብዝ​በ​ዛ​ንስ ትበ​ዘ​ብዝ ዘንድ፥ ብር​ንና ወር​ቅ​ንስ ትወ​ስድ ዘንድ፥ ከብ​ት​ንና ዕቃ​ንስ ትወ​ስድ ዘንድ፥ እጅ​ግስ ብዙ ምርኮ ትማ​ርክ ዘንድ ወገ​ን​ህን ሰብ​ስ​በ​ሃ​ልን? ይሉ​ሃል።”
14አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ስለ​ዚህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ጎግ​ንም እን​ዲህ በለው፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን ሕዝቤ እስ​ራ​ኤል በሰ​ላም በተ​ቀ​መጠ ጊዜ አንተ የም​ት​ነሣ አይ​ደ​ለ​ምን? 15አን​ተም፥ ከአ​ን​ተም ጋር ብዙ ሕዝብ ሁላ​ቸው በፈ​ረ​ሶች ላይ የተ​ቀ​መጡ፥ ታላቅ ወገ​ንና ብርቱ ሠራ​ዊት፥ ከሰ​ሜን ዳርቻ ከስ​ፍ​ራ​ችሁ ትመ​ጣ​ላ​ችሁ። 16ምድ​ር​ንም ትሸ​ፍን ዘንድ እንደ ደመና በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትወ​ጣ​ለህ። በኋ​ለ​ኛው ዘመን ይሆ​ናል፤ ጎግ ሆይ!#“ጎግ ሆይ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። በፊ​ታ​ቸው በተ​ቀ​ደ​ስ​ሁ​ብህ ጊዜ፥ አሕ​ዛብ ያው​ቁኝ ዘንድ በም​ድሬ ላይ አወ​ጣ​ሃ​ለሁ።
17“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጎግ እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ነ​ርሱ ላይ እን​ደ​ማ​መ​ጣህ፥ በዚ​ያች ዘመን ብዙ ዓመት ትን​ቢት በተ​ና​ገሩ በባ​ሪ​ያ​ዎች በእ​ስ​ራ​ኤል ነቢ​ያት እጅ በቀ​ደ​መው ዘመን ስለ እርሱ የተ​ና​ገ​ርሁ አንተ ነህን? 18በዚ​ያም ቀን ጎግ በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ላይ በመጣ ጊዜ መቅ​ሠ​ፍቴ በመ​ዓቴ ይመ​ጣል ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 19በቅ​ን​አ​ቴና በመ​ዓቴ እሳት ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፦ በእ​ር​ግጥ በዚያ ቀን በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ጽኑ መና​ወጥ ይሆ​ናል፤ 20ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት የተ​ነሣ የባ​ሕር ዓሣ​ዎ​ችና የሰ​ማይ ወፎች፥ የም​ድረ በዳም አራ​ዊት፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ሁሉ፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ኖሩ ሰዎች ሁሉ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ተራ​ሮ​ችም ይገ​ለ​ባ​በ​ጣሉ፤ ገዳ​ላ​ገ​ደ​ሎ​ችም ይወ​ድ​ቃሉ፤ ቅጥ​ርም ሁሉ ወደ ምድር ይወ​ድ​ቃል። 21በተ​ራ​ሮ​ችም ሁሉ በእ​ርሱ ላይ ፍር​ሀ​ትን እጠ​ራ​ለሁ፤ የሰ​ውም ሁሉ ሰይፍ በወ​ን​ድሙ ላይ ይሆ​ናል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 22በቸ​ነ​ፈ​ርና በደም እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ ዶፍም፥ የበ​ረ​ዶም ድን​ጋይ፥ እሳ​ትና ድኝም በእ​ር​ሱና በጭ​ፍ​ሮቹ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር በአሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘ​ን​ባ​ለሁ። 23ታላቅ እሆ​ና​ለሁ፤ እቀ​ደ​ስ​ማ​ለሁ፤ እመ​ሰ​ገ​ና​ለ​ሁም፤ በብዙ አሕ​ዛ​ብም ዐይን የታ​ወ​ቅሁ እሆ​ና​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ