የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 34

34
የኤ​ሞር ልጅ ዲናን እንደ አስ​ነ​ወ​ራት
1ለያ​ዕ​ቆብ የተ​ወ​ለ​ደች የልያ ልጅ ዲናም የዚ​ያን ሀገር ሴቶች ልጆ​ችን ለማ​የት ወጣች። 2የሀ​ገሩ አለቃ የኤ​ዊ​ያ​ዊው ሰው የኤ​ሞር ልጅ ሴኬም አያት፤ ወሰ​ዳ​ትም፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ተኛ፤ አስ​ነ​ወ​ራ​ትም። 3ልቡ​ና​ውም በያ​ዕ​ቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነ​ደፈ፤ ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱ​ንም ወደ​ዳት፤ ልብ​ዋ​ንም ደስ በሚ​ያ​ሰ​ኛት ነገር ተና​ገ​ራት። 4ሴኬ​ምም አባ​ቱን ኤሞ​ርን፥ “ይህ​ችን ብላ​ቴና አጋ​ባኝ” ብሎ ነገ​ረው። 5ያዕ​ቆ​ብም ልጁን ዲናን የኤ​ሞር ልጅ እን​ዳ​ስ​ነ​ወ​ራት ሰማ፤ ልጆ​ቹም ከከ​ብ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር በም​ድረ በዳ ነበሩ፤ ያዕ​ቆ​ብም ልጆቹ እስ​ኪ​መጡ ድረስ ዝም አለ። 6የሴ​ኬም አባት ኤሞ​ርም ይነ​ግ​ረው ዘንድ ወደ ያዕ​ቆብ መጣ። 7የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ከም​ድረ በዳ መጡ፤ ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ፈጽ​መው ደነ​ገጡ፤ የያ​ዕ​ቆ​ብን ልጅ በመ​ተ​ኛቱ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ኀፍ​ረ​ትን ስላ​ደ​ረገ አዘኑ፤ እጅ​ግም ተቈጡ፤ እን​ዲህ አይ​ደ​ረ​ግ​ምና። 8ኤሞ​ርም እን​ዲህ ብሎ ነገ​ራ​ቸው፥ “ልጄ ሴኬም ልጃ​ች​ሁን ወዶ​አ​ታ​ልና ሚስት እን​ድ​ት​ሆ​ነው እር​ስ​ዋን ስጡት። 9ጋብ​ቾ​ችም ሁኑን፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ስጡን፤ እና​ን​ተም የእ​ኛን ሴቶች ልጆች ለል​ጆ​ቻ​ችሁ ውሰዱ። 10ከእ​ኛም ጋር ተቀ​መጡ፤ ምድ​ራ​ች​ንም በፊ​ታ​ችሁ ሰፊ ናት፤ ኑሩ​ባት፤ ነግ​ዱም፤ ግዙ​አ​ትም።” 11ሴኬ​ምም አባ​ቷ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ዋን እን​ዲህ አለ፥ “በፊ​ታ​ችሁ ሞገ​ስን በአ​ገኝ የም​ት​ሉ​ትን ሁሉ እሰ​ጣ​ለሁ። 12ብዙ ማጫ አምጣ በሉኝ፤ በም​ት​ጠ​ይ​ቁ​ኝም መጠን እሰ​ጣ​ለሁ፤ ይህ​ችን ብላ​ቴና ግን ሚስት ትሆ​ነኝ ዘንድ ስጡኝ።” 13የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ለሴ​ኬ​ምና ለአ​ባቱ ለኤ​ሞር በተ​ን​ኰል መለሱ፤ እኅ​ታ​ቸ​ውን ዲናን አስ​ነ​ው​ሮ​አ​ታ​ልና፤ 14የዲና ወን​ድ​ሞች ስም​ዖ​ንና ሌዊም እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “እኅ​ታ​ች​ንን ላል​ተ​ገ​ረዘ ሰው ለመ​ስ​ጠት ይህን ነገር እና​ደ​ርግ ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ንም፤ ይህ ነውር ይሆ​ን​ብ​ና​ልና። 15እና​ን​ተም እንደ እኛ ወን​ዶ​ቻ​ች​ሁን ሁሉ ብት​ገ​ርዙ በዚህ ብቻ እን​መ​ስ​ላ​ች​ኋ​ለን፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር እን​ኖ​ራ​ለን፤ 16ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ን​ንም እን​ሰ​ጣ​ች​ኋ​ለን፤ የእ​ና​ን​ተ​ንም ሴቶች ልጆች ለሚ​ስ​ት​ነት እን​ወ​ስ​ዳ​ለን፤ አንድ ሕዝ​ብም ሆነን ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ኖ​ራ​ለን። 17ትገ​ረዙ ዘንድ እኛን ባት​ሰሙ ግን ልጃ​ች​ንን ይዘን እን​ሄ​ዳ​ለን።”
18ነገ​ራ​ቸ​ውም ኤሞ​ር​ንና የኤ​ሞ​ርን ልጅ ሴኬ​ምን ደስ አሰ​ኛ​ቸው። 19ብላ​ቴ​ና​ውም ይህን ነገር ያደ​ርግ ዘንድ አል​ዘ​ገ​የም፤ የያ​ዕ​ቆ​ብን ልጅ ወድ​ዶ​አ​ልና፤ እር​ሱም ከአ​ባቱ ቤተ ሰብእ ሁሉ የከ​በረ ነበረ። 20ኤሞ​ርና ልጁ ሴኬ​ምም ሄዱና ወደ ከተ​ማ​ቸው በር ደረሱ፤ ለከ​ተ​ማ​ቸ​ውም ሰዎች ሁሉ እን​ዲህ ብለው ነገሩ፦ 21“እነ​ዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰ​ላም ሰዎች ናቸው፤ በም​ድ​ራ​ችን ይቀ​መጡ፤ ይነ​ግ​ዱ​ባ​ትም፤ እነ​ሆም፥ ምድ​ሪቱ ሰፊ ናት፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለሚ​ስ​ት​ነት እን​ው​ሰድ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ንን እን​ስጥ። 22እነ​ርሱ እንደ እኛ ይሆኑ ዘንድ በዚህ ብቻ እን​ም​ሰ​ላ​ቸው። አንድ ወገ​ንም እን​ሁን፤ እነ​ርሱ እን​ደ​ሚ​ገ​ርዙ ወን​ዶ​ቻ​ች​ንን ሁሉ እን​ገ​ር​ዛ​ለን። 23መን​ጋ​ቸ​ውም፥ የጋማ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ ገን​ዘ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ ለእኛ አይ​ደ​ሉ​ምን? ነገር ግን በዚህ ብቻ ከመ​ሰ​ል​ና​ቸው ከእኛ ጋር ይቀ​መ​ጣሉ።” 24በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በር የሚ​ገቡ ሁሉ ኤሞ​ር​ንና ልጁን ሴኬ​ምን እሺ አሉ፤ ወን​ዶ​ችም ሁሉ የሰ​ው​ነ​ታ​ቸ​ውን ሸለ​ፈት ተገ​ረዙ።#ዕብ. “ከከ​ተ​ማ​ዪቱ አደ​ባ​ባይ የሚ​ወ​ጡት ወን​ዶች ሁሉ ተገ​ረዙ” ይላል።
የዲና ወን​ድ​ሞች በቀል
25እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን እጅግ ቈስ​ለው ሳሉ ሁለቱ የያ​ዕ​ቆብ ልጆች የዲና ወን​ድ​ሞች ስም​ዖ​ንና ሌዊ እየ​ራ​ሳ​ቸው ሰይ​ፋ​ቸ​ውን ይዘው ተደ​ፋ​ፍ​ረው ወደ ከተማ ገቡ፤ ወን​ዱ​ንም ሁሉ ገደሉ፤ 26ኤሞ​ር​ንና ልጁን ሴኬ​ም​ንም በሰ​ይፍ ገደሉ፤ እኅ​ታ​ቸው ዲና​ንም ከሴ​ኬም ቤት ይዘው ወጡ። 27የያ​ዕ​ቆብ ልጆ​ችም ወደ ሞቱት ገብ​ተው እኅ​ታ​ቸው ዲናን ያስ​ነ​ወ​ሩ​ባ​ትን ከተ​ማ​ዪ​ቱን ዘረፉ፤ 28ላሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ በጎ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ አህ​ዮ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሜ​ዳም፥ በከ​ተ​ማም ያለ​ውን ወሰዱ ። 29ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንና ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ የቤ​ታ​ቸ​ው​ንም ቈሳ​ቍስ#ዕብ. “ሀብ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ሕፃ​ና​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ሴቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ” ይላል። ሁሉ ማረኩ፤ በቤ​ትና በከ​ተማ ያለ​ው​ንም ሁሉ ዘረፉ። 30ያዕ​ቆ​ብም ስም​ዖ​ን​ንና ሌዊን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ክፉ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ብኝ፤ በዚች ሀገር በሚ​ኖሩ በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንና በፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን ሰዎች ዘንድ አስ​ጠ​ላ​ች​ሁኝ። እኔ በቍ​ጥር ጥቂት ነኝ፤ እነ​ርሱ በእኔ ላይ ይሰ​በ​ሰ​ቡና ይወ​ጉ​ኛል፤ እኔና ቤቴም እን​ጠ​ፋ​ለን።” 31እነ​ር​ሱም፥ “እኅ​ታ​ች​ንን እንደ አመ​ን​ዝራ አድ​ር​ገው ለምን አዋ​ረ​ዷት?” አሉት።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ