የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 16

16
ሶም​ሶን በጋዛ
1ሶም​ሶ​ንም ወደ ጋዛ ሄደ፥ በዚ​ያም ጋለ​ሞታ ሴት አይቶ ወደ እር​ስዋ ገባ። 2ለጋዛ ሰዎ​ችም፥ “ሶም​ሶን ወደ​ዚህ መጥ​ቶ​አል” ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው፤ ከበ​ቡ​ትም። ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ በከ​ተ​ማ​ዪቱ በር ሸመ​ቁ​በት፥ “ማለዳ እን​ገ​ድ​ለ​ዋ​ለን” ብለ​ውም ሌሊ​ቱን ሁሉ በዝ​ምታ ተቀ​መጡ። 3ሶም​ሶ​ንም እስከ እኩለ ሌሊት ተኛ፤ በእ​ኩለ ሌሊ​ትም ተነ​ሥቶ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱን በር መዝ​ጊያ ያዘ፤ ከሁ​ለቱ መቃ​ኖ​ችና ከመ​ወ​ር​ወ​ሪ​ያው ጋር ነቀ​ለው፤ በት​ከ​ሻ​ውም ላይ አደ​ረገ፤ በኬ​ብ​ሮ​ንም ፊት ወዳ​ለው ተራራ ራስ ላይ ተሸ​ክ​ሞት ወጣ፤ በዚ​ያም ጣለው።
ሶም​ሶን ደሊ​ላን እንደ አገባ
4ከዚህ በኋላ በሶ​ሬሕ ሸለቆ የነ​በ​ረች ደሊላ የተ​ባ​ለች አን​ዲት ሴትን ወደደ። 5የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መሳ​ፍ​ን​ትም ወደ እር​ስዋ ወጥ​ተው፥ “እር​ሱን አባ​ብ​ለሽ በእ​ርሱ ያለ ታላቅ ኀይል በምን እንደ ሆነ፥ እኛም እር​ሱን ለማ​ዋ​ረድ እና​ስ​ረው ዘንድ የም​ና​ሸ​ን​ፈው በምን እንደ ሆነ ዕወቂ፤ እኛም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችን ሺህ አንድ መቶ ብር እን​ሰ​ጥ​ሻ​ለን” አሉ​አት። 6ደሊ​ላም ሶም​ሶ​ንን፥ “ታላቅ ኀይ​ልህ በምን እንደ ሆነ፥ በም​ንስ ብት​ታ​ሰር እን​ደ​ምትዋ​ረድ እባ​ክህ ንገ​ረኝ” አለ​ችው። 7ሶም​ሶ​ንም፥ “በሰ​ባት ባል​ደ​ረቀ በር​ጥብ ጠፍር ቢያ​ስ​ሩኝ፥ እደ​ክ​ማ​ለሁ፤ እንደ ሌላም ሰው እሆ​ና​ለሁ” አላት ። 8የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መሳ​ፍ​ን​ትም ሰባት ያል​ደ​ረቀ ርጥብ ጠፍር አመ​ጡ​ላት፤ በእ​ነ​ር​ሱም አሰ​ረ​ችው። 9የሚ​ያ​ደ​ቡ​ትም ሰዎች በጓ​ዳዋ ውስጥ ተደ​ብ​ቀው ነበር። እር​ስ​ዋም፥ “ሶም​ሶን ሆይ! ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መጡ​ብህ” አለ​ችው። እር​ሱም ፈትል እሳት በሸ​ተ​ተው ጊዜ እን​ዲ​በ​ጠስ ጠፍ​ሩን በጣ​ጠ​ሰው፤ ኀይ​ሉም በምን እንደ ሆነ አል​ታ​ወ​ቀም።
10ደሊ​ላም ሶም​ሶ​ንን፥ “እነሆ፥ አታ​ለ​ል​ኸኝ፤ የነ​ገ​ር​ኸ​ኝም ሐሰት ነው፤ አሁ​ንም የም​ት​ታ​ሰ​ር​በት ምን እን​ደ​ሆነ፥ እባ​ክህ ንገ​ረኝ” አለ​ችው። 11እር​ሱም፥ “ሥራ ባል​ተ​ሠ​ራ​ባ​ቸው ሰባት አዳ​ዲስ ገመ​ዶች ቢያ​ስ​ሩኝ፥ እደ​ክ​ማ​ለሁ፤ እንደ ሌላ​ውም ሰው እሆ​ና​ለሁ” አላት። 12ደሊ​ላም ሰባት አዳ​ዲስ ገመ​ዶች ወስዳ በእ​ነ​ርሱ አሰ​ረ​ችው፤ የሚ​ያ​ደ​ቡ​ትም ሰዎች በጓ​ዳዋ ውስጥ ተቀ​ም​ጠው ነበር። እር​ስ​ዋም፥ “ሶም​ሶን ሆይ! ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መጡ​ብህ” አለ​ችው። ገመ​ዶ​ች​ንም ከክ​ንዱ እንደ ፈትል በጣ​ጠ​ሳ​ቸው።
13ደሊ​ላም ሶም​ሶ​ንን፥ “እስከ አሁን ድረስ አታ​ለ​ል​ኸኝ፤ የነ​ገ​ር​ኸ​ኝም ሐሰት ነው፤ የም​ት​ታ​ሰ​ር​በት ምን እን​ደ​ሆነ ንገ​ረኝ” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “የራ​ሴን ጠጕር ሰባ​ቱን ጕን​ጕን ከድር ጋር ብት​ጐ​ነ​ጕ​ኚው፥ በግ​ድ​ግ​ዳም ላይ በች​ካል ብት​ቸ​ክ​ዪው፥ ከሰ​ዎች እንደ አንዱ እደ​ክ​ማ​ለሁ፥” አላት። 14ደሊ​ላም አስ​ተ​ኛ​ችው፤ የራ​ሱ​ንም ጠጕር ሰባ​ቱን ጕን​ጕን ከድር ጋር ጐነ​ጐ​ነ​ችው፤ በግ​ድ​ግ​ዳም ላይ በች​ካል ቸከ​ለ​ቻ​ቸው፥ “ሶም​ሶን ሆይ! ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መጡ​ብህ” አለ​ችው። ከእ​ን​ቅ​ል​ፉም ነቃ፥ ችካ​ሉ​ንም ከነ​ቈ​ን​ዳ​ላው ከግ​ድ​ግ​ዳው ነቀለ፤ ኀይ​ሉም አል​ታ​ወ​ቀም።
15ደሊ​ላም፥ “ ‘አንተ እወ​ድ​ድ​ሻ​ለሁ’ እን​ዴት ትለ​ኛ​ለህ? ልብህ ከእኔ ጋር አይ​ደ​ለም፤ ስታ​ታ​ል​ለኝ ይህ ሦስ​ተኛ ጊዜህ ነው፥ ታላቅ ኀይ​ል​ህም በምን እንደ ሆነ አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ኝም” አለ​ችው። 16ከዚ​ህም በኋላ ሌሊ​ቱን ሁሉ በነ​ገር በዘ​በ​ዘ​በ​ች​ውና በአ​ደ​ከ​መ​ችው ጊዜ፥ ልሙት እስ​ኪል ድረስ ተበ​ሳጨ። 17እር​ሱም፥ “ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ጀምሬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናዝ​ራዊ ነኝና ራሴን ምላጭ አል​ነ​ካ​ኝም፤ የራ​ሴ​ንም ጠጕር ብላጭ ኀይሌ ከእኔ ይነ​ሣል፤ እደ​ክ​ማ​ለ​ሁም፤ እንደ ሌላም ሰው ሁሉ እሆ​ና​ለሁ” ብሎ የል​ቡን ሁሉ ነገ​ራት። 18ደሊ​ላም የል​ቡን ሁሉ እንደ ነገ​ራት ባወ​ቀች ጊዜ፥ “የል​ቡን ሁሉ ነግ​ሮ​ኛ​ልና ይህን ጊዜ ደግሞ ኑ” ብላ ላከ​ችና የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መሳ​ፍ​ንት ጠራች። የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም መሳ​ፍ​ንት ብሩን በእ​ጃ​ቸው ይዘው ወደ እር​ስዋ መጡ። 19እር​ስ​ዋም በጕ​ል​በቷ ላይ አስ​ተ​ኛ​ችው፤ ጠጕር ቈራ​ጭም ጠራች፤ እር​ሱም ሰባ​ቱን የራ​ሱን ጕን​ጕን ላጨው። ይደ​ክ​ምም ጀመረ፤ ኀይ​ሉም ከእ​ርሱ ሄደ። 20ደሊ​ላም፥ “ሶም​ሶን ሆይ! ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መጡ​ብህ” አለ​ችው። ከእ​ን​ቅ​ል​ፉም ነቅቶ፥ “እወ​ጣ​ለሁ፤ እንደ ወት​ሮ​ውም ጊዜ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም” አለ። ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ እንደ ተለ​የው አላ​ወ​ቀም። 21ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ይዘው ዐይ​ኖ​ቹን አወ​ጡት፤ ወደ ጋዛም አው​ር​ደው በእ​ግር ብረት አሰ​ሩት፤ በግ​ዞ​ትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር። 22የራ​ሱም ጠጕር ከላ​ጩት በኋላ ያድግ ጀመር።
የሶ​ም​ሶን ሞት
23የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም መሳ​ፍ​ን​ትም፥ “አም​ላ​ካ​ችን ጠላ​ታ​ች​ንን ሶም​ሶ​ንን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጠን” እያሉ ለአ​ም​ላ​ካ​ቸው ለዳ​ጎን ታላቅ መሥ​ዋ​ዕት ይሠዉ ዘንድ፥ ደስም ይላ​ቸው ዘንድ ተሰ​በ​ሰቡ። 24ሕዝ​ቡም ሁሉ ባዩት ጊዜ፥ “ምድ​ራ​ች​ንን ያጠ​ፋ​ውን፥ ከእ​ኛም ብዙ ሰው የገ​ደ​ለ​ውን ጠላ​ታ​ች​ንን አም​ላ​ካ​ችን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጠን እያሉ አም​ላ​ካ​ቸ​ውን አመ​ሰ​ገኑ። 25ከዚ​ህም በኋላ ልባ​ቸ​ውን ደስ ባለው ጊዜ፥ “በፊ​ታ​ችን እን​ዲ​ጫ​ወት ሶም​ሶ​ንን ከእ​ስር ቤት ጥሩት” አሉ። ሶም​ሶ​ን​ንም ከእ​ስር ቤት ጠሩት፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ተጫ​ወተ፤ ተዘ​ባ​በ​ቱ​በ​ትም፤ በም​ሰ​ሶና በም​ሰ​ሶም መካ​ከል አቆ​ሙት። 26ሶም​ሶ​ንም የሚ​መ​ራ​ውን ብላ​ቴና፥ “ቤቱን የደ​ገ​ፉ​ትን ምሰ​ሶ​ዎች እደ​ገ​ፍ​ባ​ቸው ዘንድ እባ​ክህ አስ​ይ​ዘኝ” አለው፥ ብላ​ቴ​ና​ውም እን​ዳ​ለው አደ​ረ​ገ​ለት። 27በቤ​ትም ውስጥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ሞል​ተ​ው​በት ነበር፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም መሳ​ፍ​ን​ትም ሁሉ በዚያ ነበሩ፤ በቤ​ቱም ሰገ​ነት ላይ ሶም​ሶን ሲጫ​ወት የሚ​ያዩ ሦስት ሺህ የሚ​ያ​ህሉ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ነበሩ።
28ሶም​ሶ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፥ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ ጌታዬ ሆይ! አስ​በኝ፤ ጌታዬ ሆይ! አንድ ጊዜ አበ​ር​ታኝ፤ እን​ግ​ዲህ ስለ ሁለቱ ዐይ​ኖቼ ፋንታ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አን​ዲት በቀ​ልን እበ​ቀ​ላ​ለሁ።” 29ሶም​ሶ​ንም ቤቱ ተደ​ግ​ፎ​ባ​ቸው የነ​በ​ሩ​ትን ሁለ​ቱን መካ​ከ​ለ​ኞች ምሰ​ሶ​ዎች ያዘ፤ አን​ዱን በቀኝ እጁ፥ አን​ዱ​ንም በግራ እጁ ይዞ ገፋ​ቸው። 30ሶም​ሶ​ንም፥ “ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ነፍሴ ትውጣ” አለ፤ ተጎ​ን​ብ​ሶም ምሰ​ሶ​ዎ​ቹን በሙሉ ኀይሉ ገፋ​ቸው፤ ቤቱም በው​ስጡ በነ​በ​ሩት በመ​ሳ​ፍ​ንቱ፥ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ላይ ወደቀ፤ በሞ​ቱም የገ​ደ​ላ​ቸው ሙታን በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ከገ​ደ​ላ​ቸው በዙ። 31ወን​ድ​ሞ​ቹም፥ የአ​ባቱ ቤተ ሰቦ​ችም ሁሉ ወረዱ፤ ይዘ​ውም አመ​ጡት፤ በሶ​ሬ​ሕና በኢ​ስ​ታ​ሔል መካ​ከል ባለው በአ​ባቱ በማ​ኑሄ መቃ​ብር ቀበ​ሩት። እር​ሱም እስ​ራ​ኤ​ልን ሃያ ዓመት ገዛ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ