የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 6

6
እስ​ራ​ኤል ስለ በደሉ በም​ድ​ያ​ማ​ው​ያን እጅ እንደ ወደቁ
1የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድ​ያም እጅ ሰባት ዓመት አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው። 2የም​ድ​ያ​ምም እጅ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ጠነ​ከ​ረች፤ ከም​ድ​ያ​ምም ፊት የተ​ነሣ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በተ​ራ​ሮ​ችና በገ​ደ​ሎች ላይ ጕድ​ጓ​ድና ዋሻ፥ ምሽ​ግም አበጁ። 3የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘር በዘሩ ጊዜ ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንና አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን ይዘ​ም​ቱ​ባ​ቸው ነበር፥ በም​ሥ​ራ​ቅም የሚ​ኖሩ ልጆች አብ​ረው ይዘ​ም​ቱ​ባ​ቸው ነበር፤ 4በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ይሰ​ፍሩ ነበር፤ ወደ ጋዛም እስ​ከ​ሚ​ደ​ርሱ የእ​ር​ሻ​ቸ​ውን ፍሬ ያጠፉ ነበር፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምድር ለሕ​ይ​ወት የሚ​ሆን ምንም አይ​ተ​ዉም ነበር፤ ከመ​ን​ጋ​ዎ​ችም በሬ ወይም አህያ ቢሆን አይ​ተ​ዉም ነበር። 5እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ይዘው በብ​ዛት እንደ አን​በጣ ሆነው ይመ​ጡ​ባ​ቸው ነበር፤ ለእ​ነ​ር​ሱና ለግ​መ​ሎ​ቻ​ቸው ቍጥር አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ያጠ​ፏት ዘንድ ይመጡ ነበር። 6ከም​ድ​ያ​ምም ፊት የተ​ነሣ እስ​ራ​ኤል እጅግ ተቸ​ገሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጌዴ​ዎ​ንን ለእ​ስ​ራ​ኤል እንደ አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው
7እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በም​ድ​ያም ምክ​ን​ያት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጮኹ ጊዜ፥ 8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ነቢይ ላከ፤ እር​ሱም አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣ​ኋ​ችሁ፤ ከባ​ር​ነ​ትም ቤት አስ​ለ​ቀ​ቅ​ኋ​ችሁ፤ 9ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም እጅ ከሚ​ጋ​ፉ​አ​ች​ሁም ሁሉ እጅ አዳ​ን​ኋ​ችሁ፤ ከፊ​ታ​ች​ሁም አሳ​ደ​ድ​ኋ​ቸው፤ ሀገ​ራ​ቸ​ው​ንም ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ 10እና​ን​ተ​ንም፦ እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ በም​ድ​ራ​ቸው የተ​ቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ቸ​ውን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አማ​ል​ክት አት​ፍሩ አል​ኋ​ችሁ። እና​ንተ ግን ቃሌን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም።”
11የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ መጥቶ በኤ​ፍ​ራታ ባለ​ችው ለኤ​ዝሪ አባት ለኢ​ዮ​አስ በነ​በ​ረ​ችው ዛፍ በታች ተቀ​መጠ፤ ልጁም ጌዴ​ዎን ከም​ድ​ያ​ማ​ው​ያን ለማ​ሸሽ በወ​ይን መጭ​መ​ቂ​ያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር። 12የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ለእ​ርሱ ተገ​ልጦ፥ “አንተ ጽኑዕ ኀያል ሰው! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው” አለው። 13ጌዴ​ዎ​ንም፥ “ጌታዬ ሆይ! እሺ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረ​ሰ​ብን? አባ​ቶ​ቻ​ች​ንስ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቶ​ናል ብለው ይነ​ግ​ሩን የነ​በረ ተአ​ም​ራት ወዴት አለ? አሁን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቶ​ናል፤ በም​ድ​ያም እጅም አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ናል” አለው። 14የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወደ እርሱ ተመ​ለ​ከ​ተና፥ “በዚህ በጕ​ል​በ​ትህ ሂድ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ከም​ድ​ያም እጅ ታድ​ና​ቸ​ዋ​ለህ፤ እነሆ፥ ልኬ​ሃ​ለሁ” አለው። 15እር​ሱም፥ “ጌታ ሆይ! እሺ፥ እስ​ራ​ኤ​ልን በምን አድ​ና​ለሁ? ወገኔ በም​ናሴ ነገድ ዘንድ ጥቂ​ቶች ናቸው፤ እኔም በአ​ባቴ ቤት የሁሉ ታናሽ ነኝ” አለው። 16የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤ ምድ​ያ​ም​ንም እንደ አንድ ሰው አድ​ር​ገህ ታጠ​ፋ​ለህ” አለው። 17ጌዴ​ዎ​ንም፥ “በፊ​ትህ ሞገ​ስን ካገ​ኘሁ፥ የም​ት​ና​ገ​ረ​ኝም አንተ እንደ ሆንህ ምል​ክት አድ​ር​ግ​ልኝ፤ 18ወደ አን​ተም እስ​ክ​መ​ለስ ድረስ፥ መሥ​ዋ​ዕ​ቴ​ንም አም​ጥቼ እስ​ካ​ቀ​ር​ብ​ልህ ድረስ፥ እባ​ክህ፥ ከዚህ አት​ሂድ” አለው። እር​ሱም፥ “እስ​ክ​ት​መ​ለስ ድረስ እቈ​ያ​ለሁ” አለው። 19ጌዴ​ዎ​ንም ሄደ፤ የፍ​የ​ሉ​ንም ጠቦት፥ የኢፍ መስ​ፈ​ሪ​ያም ዱቄት የቂጣ እን​ጎቻ አዘ​ጋጀ፤ ሥጋ​ው​ንም በሌ​ማት አኖረ፤ መረ​ቁ​ንም በም​ን​ቸት ውስጥ አደ​ረገ፤ ሁሉ​ንም ይዞ በዛፍ በታች አቀ​ረ​በ​ለት። ሰገ​ደ​ለ​ትም። 20የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “ሥጋ​ው​ንና የቂ​ጣ​ውን እን​ጎቻ ወስ​ደህ በዚህ ድን​ጋይ ላይ አኑር፤ መረ​ቁ​ንም አፍ​ስስ” አለው። እን​ዲ​ሁም አደ​ረገ። 21የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በእጁ ያለ​ውን በት​ሩን ዘር​ግቶ ሥጋ​ዉ​ንና የቂ​ጣ​ዉን እን​ጎቻ አስ​ነካ፤ እሳ​ትም ከድ​ን​ጋዩ ውስጥ ወጥታ ሥጋ​ዉ​ንና የቂ​ጣ​ዉን እን​ጎቻ በላች። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከዐ​ይ​ኖቹ ተሰ​ወረ። 22ጌዴ​ዎ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ እንደ ሆነ ዐወቀ። ጌዴ​ዎ​ንም፥ “አቤቱ! አም​ላኬ ሆይ! ወዮ​ልኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ ፊት ለፊት አይ​ቻ​ለ​ሁና” አለ። 23እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሰላም ለአ​ንተ ይሁን፤ አት​ፍራ፤ አት​ሞ​ትም” አለው። 24ጌዴ​ዎ​ንም በዚያ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ፤ ስሙ​ንም እስከ ዛሬ ድረስ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰላም”#ዕብ. “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰላም” ይላል። ብሎ ጠራው። እር​ሱም እስከ ዛሬ ድረስ ለኤ​ዝሪ አባት በሆ​ነ​ችው በኤ​ፍ​ራታ አለ።
25እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዚ​ያች ሌሊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “የአ​ባ​ት​ህን በሬ፥ ሰባት ዓመት የሆ​ነ​ውን ሁለ​ተ​ኛ​ውን በሬ ውሰድ፤ የአ​ባ​ትህ የሆ​ነ​ው​ንም የበ​ዓል መሠ​ዊያ አፍ​ርስ፤ በእ​ር​ሱም ዙሪያ ያለ​ውን የማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸድ ቍረጥ፤ 26በዚ​ያም ተራራ አናት ላይ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ አሳ​ም​ረህ ሥራ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ዉ​ንም በሬ ውሰድ፤ በዚ​ያም በቈ​ረ​ጥ​ኸው በማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸዱ እን​ጨት ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርብ” አለው። 27ጌዴ​ዎ​ንም ከባ​ሪ​ያ​ዎቹ ዐሥራ ሦስት#ዕብ. እና አን​ዳ​ንድ የግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ዘርዕ “ዐሥር” ይላል። ሰዎ​ችን ወስዶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ለው አደ​ረገ፤ የአ​ባ​ቱ​ንም ቤተ ሰቦች፥ የከ​ተ​ማ​ዉ​ንም ሰዎች ስለ​ፈራ ይህን በቀን ለማ​ድ​ረግ አል​ቻ​ለም፤ ነገር ግን በሌ​ሊት አደ​ረ​ገው።
28የከ​ተ​ማ​ውም ሰዎች ማል​ደው ተነሡ፤ እነ​ሆም፥ የበ​ዓል መሠ​ዊያ ፈርሶ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያለው የማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸድ ተቈ​ርጦ፥ በተ​ሠ​ራ​ውም መሠ​ዊያ ላይ ሁለ​ተ​ኛው በሬ ተሠ​ውቶ አገ​ኙት። 29እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ይህን ነገር ያደ​ረገ ማን ነው?” ተባ​ባሉ። በጠ​የ​ቁና በመ​ረ​መ​ሩም ጊዜ፥ “ይህን ነገር ያደ​ረገ የኢ​ዮ​አስ ልጅ ጌዴ​ዎን ነው” አሉ። 30የከ​ተ​ማ​ዉም ሰዎች ኢዮ​አ​ስን፥ “የበ​ዓ​ልን መሠ​ዊያ አፍ​ር​ሶ​አ​ልና፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያለ​ውን የማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸድ ቈር​ጦ​አ​ልና ይገ​ደል ዘንድ ልጅ​ህን አምጣ” አሉት። 31ኢዮ​አ​ስም በእ​ርሱ ላይ የተ​ነ​ሡ​በ​ትን ሁሉ፥ “ለበ​ዓል እና​ንተ ዛሬ ትበ​ቀ​ሉ​ለ​ታ​ላ​ች​ሁን? ወይስ የበ​ደ​ለ​ውን ትገ​ድ​ሉ​ለት ዘንድ የም​ታ​ድ​ኑት እና​ንተ ናች​ሁን? እርሱ አም​ላክ ከሆ​ነስ የበ​ደ​ለው እስከ ነገ ድረስ ይሙት። መሠ​ዊ​ያ​ዉ​ንም ያፈ​ረ​ሰ​ውን እርሱ ይበ​ቀ​ለው” አላ​ቸው። 32በዚ​ያች ቀንም መሠ​ዊ​ያ​ዉን አፍ​ር​ሶ​አ​ልና በዓል ከእ​ርሱ ጋር ይሟ​ገት ሲል ጌዴ​ዎ​ንን ይሩ​በ​ኣል ብሎ ጠራው።
33ምድ​ያ​ምና አማ​ሌ​ቅም ሁሉ፥ የም​ሥ​ራ​ቅም ልጆች አንድ ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ፤ ተሻ​ግ​ረ​ውም በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ሸለቆ ሰፈሩ። 34ጌዴ​ዎ​ን​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ አጸ​ናው፤ እር​ሱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ነፋ፤ አብ​ዔ​ዜ​ርም በኋ​ላው ጮኸ። 35ወደ ምና​ሴም ነገድ ሁሉ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እር​ሱም ከኋ​ላው ሆኖ ጮኸ፤#“እር​ሱም በኋ​ላው ሁኖ ጮኸ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ንም ወደ አሴ​ርና ወደ ዛብ​ሎን ወደ ንፍ​ታ​ሌ​ምም ላከ፤ እነ​ር​ሱም ሊቀ​በ​ሉ​አ​ቸው ወጡ።
36ጌዴ​ዎ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እንደ ተና​ገ​ርህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በእኔ እጅ ታድን እንደ ሆነ፥ 37እነሆ! በዐ​ው​ድ​ማዉ ላይ የተ​ባ​ዘተ የበግ ጠጕር አኖ​ራ​ለሁ፤ በጠ​ጕሩ ብቻ ላይ ጠል ቢሆን በም​ድ​ሩም ሁሉ ደረቅ ቢሆን፥ እንደ ተና​ገ​ርህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በእኔ እጅ እን​ደ​ም​ታ​ድ​ና​ቸው አው​ቃ​ለሁ” አለ። 38እን​ዲ​ሁም ሆነ፤ በነ​ጋው ማልዶ ተነሣ፤ ጠጕ​ሩ​ንም ጨመ​ቀው፤ ከጠ​ጕ​ሩም የተ​ጨ​መ​ቀው ጠል አንድ መን​ቀል ሙሉ ውኃ ሆነ። 39ጌዴ​ዎ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “በቍ​ጣህ አት​ቈ​ጣኝ፤ ደግሞ አን​ዲት ነገር ልና​ገር፤ ጠጕሩ ብቻ​ውን ደረቅ ይሁን፤ በም​ድ​ሩም ላይ ጠል ይው​ረድ።” 40እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያች ሌሊት እን​ዲሁ አደ​ረገ፤ ጠጕሩ ብቻ ደረቅ ሆነ፥ በም​ድ​ሩም ሁሉ ላይ ጠል ወረደ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ