ኦሪት ዘኍልቍ 17
17
የአሮን በትር እንደ ለመለመች
1እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2“ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው፤ ከእነርሱም ከእያንዳንዱ ከየአባቶቻቸው ቤት አንድ አንድ በትር፥ ከአለቆቻቸውም ከየአባቶቻቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በትሮች ውሰድ፤ የእያንዳንዱንም ስም በየበትሩ ላይ ጻፍ። 3ለየአባቶቻቸው ቤት ወገን አንድ በትር ይሰጣሉና በሌዊ በትር ላይ የአሮንን ስም ጻፍ። 4እኔ ለእናንተ በምገለጥበት በዚያ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት አኑራቸው። 5እንዲህም ይሆናል፤ የመረጥሁት ሰው በትር ትለመልማለች፤ በእናንተም ላይ የሚያጕረመርሙባችሁ የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ።” 6ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ነገራቸው፤ አለቆቻቸውም ሁሉ አንድ አንድ በትር ሰጡት፤ ለአንድ አለቃ አንድ በትር፥ በየአባቶቻቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በትሮች፤ የአሮንም በትር በበትሮቻቸው መካከል ነበረች። 7ሙሴም በትሮቹን በእግዚአብሔር ፊት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ አኖራቸው።
8እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴና አሮን ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገቡ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነች የአሮን በትር አቈጠቈጠች፤ ለመለመችም፤ አበባም አወጣች፤ የበሰለ ለውዝም አፈራች። 9ሙሴም በትሮቹን ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ወደ እስራኤል ልጆች ሁሉ አወጣቸው፤ እነርሱም አዩ፤ እያንዳንዱም በትሩን ወሰደ። 10እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “ማጕረምረማቸው ከእኔ ዘንድ እንዲጠፋ፥ እነርሱም እንዳይሞቱ ለማይሰሙ#ዕብ. “ለሚያምፁብኝ” ይላል። ልጆች ምልክት ሆና ትጠበቅ ዘንድ የአሮንን በትር በምስክሩ ፊት አኑር።” 11ሙሴና አሮንም፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ፤ እንዲሁ አደረጉ።
12የእስራኤልም ልጆች ሙሴን አሉት፥ “እነሆ፥ እንሞታለን፤ እንጠፋለን፤ ሁላችንም እናልቃለን። 13የእግዚአብሔርን ድንኳን የሚነካ ሁሉ ይሞታል።#ዕብ. “የሚቀርብ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ የሚቀርብ ይሞታል” ይላል። በውኑ ሁላችን ፈጽመን እንሞታለን?”
Currently Selected:
ኦሪት ዘኍልቍ 17: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ