የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 17

17
የአ​ሮን በትር እንደ ለመ​ለ​መች
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 2“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ንገ​ራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ከእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ከየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት አንድ አንድ በትር፥ ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም ከየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በት​ሮች ውሰድ፤ የእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱ​ንም ስም በየ​በ​ትሩ ላይ ጻፍ። 3ለየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ወገን አንድ በትር ይሰ​ጣ​ሉና በሌዊ በትር ላይ የአ​ሮ​ንን ስም ጻፍ። 4እኔ ለእ​ና​ንተ በም​ገ​ለ​ጥ​በት በዚያ በመ​ገ​ና​ኛው ድን​ኳን ውስጥ በም​ስ​ክሩ ፊት አኑ​ራ​ቸው። 5እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የመ​ረ​ጥ​ሁት ሰው በትር ትለ​መ​ል​ማ​ለች፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙ​ባ​ችሁ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማጕ​ረ​ም​ረም ከእኔ ዘንድ አጠ​ፋ​ለሁ።” 6ሙሴም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ነገ​ራ​ቸው፤ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ አንድ አንድ በትር ሰጡት፤ ለአ​ንድ አለቃ አንድ በትር፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በት​ሮች፤ የአ​ሮ​ንም በትር በበ​ት​ሮ​ቻ​ቸው መካ​ከል ነበ​ረች። 7ሙሴም በት​ሮ​ቹን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ አኖ​ራ​ቸው።
8እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በነ​ጋው ሙሴና አሮን ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ገቡ፤ እነ​ሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆ​ነች የአ​ሮን በትር አቈ​ጠ​ቈ​ጠች፤ ለመ​ለ​መ​ችም፤ አበ​ባም አወ​ጣች፤ የበ​ሰለ ለው​ዝም አፈ​ራች። 9ሙሴም በት​ሮ​ቹን ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ አወ​ጣ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም አዩ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በት​ሩን ወሰደ። 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “ማጕ​ረ​ም​ረ​ማ​ቸው ከእኔ ዘንድ እን​ዲ​ጠፋ፥ እነ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሞቱ ለማ​ይ​ሰሙ#ዕብ. “ለሚ​ያ​ም​ፁ​ብኝ” ይላል። ልጆች ምል​ክት ሆና ትጠ​በቅ ዘንድ የአ​ሮ​ንን በትር በም​ስ​ክሩ ፊት አኑር።” 11ሙሴና አሮ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ፤ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።
12የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሙሴን አሉት፥ “እነሆ፥ እን​ሞ​ታ​ለን፤ እን​ጠ​ፋ​ለን፤ ሁላ​ች​ንም እና​ል​ቃ​ለን። 13የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድን​ኳን የሚ​ነካ ሁሉ ይሞ​ታል።#ዕብ. “የሚ​ቀ​ርብ ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ የሚ​ቀ​ርብ ይሞ​ታል” ይላል። በውኑ ሁላ​ችን ፈጽ​መን እን​ሞ​ታ​ለን?”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ