የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 72

72
የአ​ሳፍ መዝ​ሙር።
1ልባ​ቸው ለቀና ለእ​ስ​ራ​ኤል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ ቸር ነው።
2እኔ ግን እግ​ሮች ሊሰ​ና​ከሉ፥
አረ​ማ​መ​ዴም ሊወ​ድቅ ጥቂት ቀረ።
3የዐ​መ​ፀ​ኞ​ችን ሰላም አይቼ
በኃ​ጥ​ኣን ላይ ቀንቼ ነበ​ርና።
4ለሞ​ታ​ቸው እረ​ፍት#ዕብ. “መጣ​ጣር” ይላል። የለ​ው​ምና፤
ለመ​ቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸ​ውም#ዕብ. “ኀይ​ላ​ቸው ጠን​ካራ ነውና” ይላል። ኀይል የለ​ው​ምና፤
5በድ​ካ​ምም ጠላት አል​ሆ​ኑም።
ከሰው ጋርም አል​ተ​ገ​ረ​ፉም።
6ስለ​ዚ​ህም ትዕ​ቢት ያዛ​ቸው፤
ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንና በደ​ላ​ቸ​ውን ተጐ​ና​ጸ​ፉ​አት።
7 # ከዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ይለ​ያል። መቅን ከቅ​ል​ጥም እን​ደ​ሚ​ወጣ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ይወ​ጣል።
ልባ​ቸ​ውም ከት​ዕ​ቢት አለፈ።
8ዐስ​በው ከንቱ ነገ​ርን ተና​ገሩ።
በአ​ር​ያ​ምም ዐመ​ፃን ተና​ገሩ።
9አፋ​ቸ​ው​ንም በሰ​ማይ አኖሩ፥
አን​ደ​በ​ታ​ቸ​ውም በም​ድር ላይ ተመ​ላ​ለሰ።
10ስለ​ዚህ ሕዝቤ ወደ​ዚህ ይመ​ለ​ሳሉ፤
ፍጹም ጊዜም በላ​ያ​ቸው ይገ​ኛል፤
11“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዴት ያው​ቃል?
በአ​ር​ያ​ምስ በውኑ የሚ​ያ​ውቅ አለን?”#ዕብ. “በል​ዑ​ልስ ዘንድ በውኑ ዕው​ቀት አለን” ይላል። ይላሉ።
12እነሆ፥ እነ​ዚህ ኃጥ​ኣን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤
ሁል​ጊ​ዜም ባለ​ጠ​ግ​ነ​ታ​ቸ​ውን ያጸ​ኗ​ታል፤
13እን​ዲ​ህም አልሁ፥ “በውኑ ልቤን በከ​ንቱ አጸ​ደ​ቅ​ሁ​አ​ትን?”
እጆ​ቼ​ንም በን​ጽ​ሕና አጠ​ብሁ።
14ሁል​ጊ​ዜም የተ​ገ​ረ​ፍሁ ሆንሁ፥
መሰ​ደ​ቤም በማ​ለዳ ነው።
15እን​ደ​ዚህ ብዬ ብና​ገር ኖሮ፥
እነሆ፥ የል​ጆ​ች​ህን ትው​ልድ በበ​ደ​ልሁ ነበር።
16አው​ቅም ዘንድ ተቀ​በ​ል​ኸኝ፥#ዕብ. “ዐሰ​ብሁ” ይላል።
ይህ ግን በፊቴ ድካም ነው።
17ፍጻ​ሜ​አ​ቸ​ውን አውቅ ዘንድ
ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ እስ​ክ​ገባ ድረስ፥
18ነገር ግን ስለ ሽን​ገ​ላ​ቸው አቈ​የ​ሃ​ቸው፥
በመ​ነ​ሣ​ታ​ቸ​ውም ጣል​ኻ​ቸው።
19እን​ዴት ለጥ​ፋት ሆኑ! በድ​ን​ገት አለቁ፥
ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ጠፉ።
20ከእ​ን​ቅ​ልፍ እን​ደ​ሚ​ነቃ፥
አቤቱ፥ በከ​ተ​ማህ ምል​ክ​ታ​ቸ​ውን ታስ​ነ​ው​ራ​ለህ።
21ልቤ ነድ​ዶ​አል፥ ኵላ​ሊ​ቴም ቀል​ጦ​አ​ልና፤
22እኔ የተ​ና​ቅሁ ነኝ፥ አላ​ወ​ቅ​ሁ​ምም፥
በአ​ንተ ዘንድ እንደ እን​ስሳ ሆንሁ።
23እኔ ግን ዘወ​ትር ከአ​ንተ ጋር ነኝ፥
ቀኝ እጄ​ንም ያዝ​ኸኝ።
24በአ​ንተ ምክር መራ​ኸኝ፤
በክ​ብ​ርም ተቀ​በ​ል​ኸኝ።
25 # ግእዙ “ምንት ብከ ተሀሉ ውስተ ሰማይ?” ይላል። በሰ​ማይ ያለኝ ምን​ድን ነው?
በም​ድ​ርስ ውስጥ ከአ​ንተ በቀር ምን እሻ​ለሁ?
26የመ​ድ​ኀ​ኒቴ አም​ላክ ሆይ፥ ልቤና ሥጋዬ አለቀ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዕድል ፋን​ታዬ ነው።
27እነሆ፥ ከአ​ንተ የሚ​ርቁ ይጠ​ፋ​ሉና፤
ከአ​ንተ ርቀው የሚ​ያ​መ​ነ​ዝ​ሩ​ት​ንም ሁሉ አጠ​ፋ​ኻ​ቸው።
28ለእኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መከ​ተል ይሻ​ለ​ኛል፤
መታ​መ​ኛ​ዬም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ነው
በጽ​ዮን ልጅ በሮች ምስ​ጋ​ና​ህን ሁሉ እና​ገር ዘንድ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ