መጽሐፈ ተግሣጽ 3
3
1 # በዕብራይስጥና በግሪክ ሰባ. ሊ. ምሳሌ ምዕ. 27 ነው። ነገ የሚያመጣውን ምን እንደሆነ አታውቅምና
ነገ በሚሆነው አትመካ።
2ሌላ ያመስግንህ እንጂ አፍህ አይደለም፥
ባዕድ ሰው እንጂ ከንፈርህ አይደለም።#በዕብ. እና በግሪክ ሰባ. ሊ. ብቻ።
3ድንጋይ ከባድ ነው፥ አሸዋም ሸክሙ ጽኑ ነው፤
ከሁለቱ ግን ያላዋቂ ቍጣ ይከብዳል።
4ለቍጡና ቍጣን ለሚያፋጥን ምሕረት የለውም፥
ቀናተኛን ግን የሚተካከለው የለም።
5የተገለጠ ዘለፋ
ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል።
6ከጠላት መልካም አሳሳም
የወዳጅ ንክሻ ይሻላል።
7የጠገበች ሰውነት የማር ወለላን ትንቃለች፤
ለተራበች ሰውነት ግን የመረረ ነገር ሁሉ ጣፋጭ ሆኖ ይታያታል።
8ከጎጆዋ ወጥታ እንደምትበርር ወፍ
እንደዚሁ ከሀገር ወጥቶ እንግዳ የሚሆን ተገዥ ይሆናል።
9በሽቱና በዕጣን፥ በወይንም ልብ ደስ ይሰኛል፥
እንዲሁ ነፍስ በወዳጅ ምክር ደስ ይላታል።
10ወዳጅህንና የአባትህን ወዳጅ አትተው፥
አስቀድመህም ሳትነግረው በመከራህ ቀን ወደ ወንድምህ ቤት አትግባ።
የቀረበ ወዳጅ ከራቀ ወንድም ይሻላል።
11ልጄ ሆይ፥ ልቤ ደስ ይለው ዘንድ ጠቢብ ሁን፥
የሽሙጥንም ቃል ከአንተ አርቅ።
12ዐዋቂ ሰው ክፋቶች በመጡበት ጊዜ ይሸሸጋል፤
አላዋቂዎች ግን ተከራክረው ጥፋትን ያመጣሉ።
13የሌላውን የሚያጠፋ ጠላት መጥትዋልና
ልብስህን አርቅ።
14ባልንጀራውን በታላቅ ቃል ማለዳ የሚመርቅ ሰው፥
ከሚራገመው የሚተወው የለም።
15ፍሳሽ በክረምት ወራት ሰውን ከቤቱ ያወጣዋል፥
እንደዚሁም ነዝናዛ ሴት ባልዋን ከመልካም ቤቱ ታስወጣለች።
16የደቡብ ነፋስ ጽኑ ነው፥
በስሙ ግን ቀኝ ይባላል።
17ብረት ብረትን ይስለዋል፥
ሰውም ባልንጀራውን ይስላል።
18በለስን የተከለ ፍሬዋን ይበላል፥
ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል።
19ፊት ከፊት ጋር እንደማይመሳሰል፥
እንዲሁም የሰው ልብ አይመሳሰልም።
20ሲኦልና ሞት እንደማይጠግቡ፥
እንዲሁ የሰው ዐይኖች አይጠግቡም።
በዐይኑ የሚገላምጥ በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነው፤#በዕብራይስጥ የለም።
ትምህርት የሌላቸውም አንደበታቸውን አይገቱም።
21ወርቅና ብር በእሳት ግለት ይፈተናሉ፥
ሰውም በሚያመሰግኑት ሰዎች አፍ ይፈተናል።
የኃጥእ ልቡ ክፋትን ትፈልጋለች፥
ቀና ልቡና ግን ዕውቀትን ትሻለች።#በዕብራይስጥ የለም።
22አላዋቂን በማዋረድ በጉባኤ መካከል ብትገርፈው፥
አላዋቂነቱን አታስወግድለትም።
23የበጎችህን መንፈስ አስተውለህ ዕወቅ፥
በከብቶችህም ላይ ልብህን አኑር።
24ግዛትም፥ ኀይልም ለዘለዓለም ለሰው አይደለም፥
ከትውልድ ወደ ትውልድ አይተላለፍምና።
25የምድረ በዳ ልምላሜን ጠብቅ፥
ደረቅ ሣርንም እጨድ፥ የተራራውንም ሣር ሰብስብ።
26በጎችን ለልብስ ገንዘብ ታደርግ ዘንድ፥
መንጋዎችህም ይበዙ ዘንድ መስኩን ጠብቅ።
27ልጄ ሆይ፥ ከእኔ ዘንድ የጸናች ቃል አለችህ፥
ለሕይወትህና ለቤተ ሰቦችህም ሕይወት የፍየል ወተትን እለብ።#ብግሪክ ሰባ. ሊ. “ልጄ ሆይ ለሕይወትህና ለቤተ ሰቦችህ ሕይወት ከእኔ ዘንድ የጸናች ቃል አለችህ” ይላል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ተግሣጽ 3: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ