መጽ​ሐፈ ሲራክ 2

2
ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታማኝ ስለ መሆን
1ልጄ ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትገዛ ዘንድ ብት​ሄድ
ሰው​ነ​ት​ህን ለመ​ከራ አዘ​ጋጅ።
2ልብ​ህን አቅና፥ ታገሥ፥ አታ​ወ​ላ​ው​ልም፥
ብት​ጨ​ነ​ቅም አት​ጠ​ራ​ጠር።
3ነገር ግን ተከ​ተ​ለው፥
በፍ​ጻ​ሜ​ህም ሕይ​ወ​ትህ ትበ​ለ​ጽግ ዘንድ አት​ተ​ወው።
4የደ​ረ​ሰ​ብ​ህን ሁሉ ተቀ​በል፥
በች​ግ​ር​ህም ወራት ታገሥ።
5ወር​ቅን በእ​ሳት ይፈ​ት​ኑ​ታ​ልና፥
ጻድ​ቅ​ንም ሰው በመ​ከራ ይፈ​ት​ኑ​ታ​ልና።
6ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እመ​ነው፤ እር​ሱም ይረ​ዳ​ሃል፤
መን​ገ​ድ​ህ​ንም አቅና፥ በእ​ር​ሱም እመን።
7እና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈ​ሩት ሆይ፥ ቸር​ነ​ቱን ደጅ ጥኗት፥
በመ​ከ​ራም እን​ዳ​ት​ወ​ድቁ ከእ​ርሱ አት​ራቁ።
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈ​ሩት ሆይ፥
ዋጋ​ች​ሁን እን​ዳ​ታጡ እመ​ኑት።
9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈሩ ሆይ፥
የዘ​ለ​ዓ​ለም በጎ​ነ​ቱን ምሕ​ረ​ቱ​ንና ደስ​ታ​ውን ተስፋ አድ​ርጉ።
10በዘ​መን የቀ​ደሙ ሰዎ​ችን ተመ​ል​ከቱ፤ ዕወ​ቁም፥
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምኖ ያፈረ ማን​ነው?
እር​ሱን በመ​ፍ​ራት የታ​ገ​ሠና የተ​ጣለ ማን​ነው?
ጠር​ቶ​ትስ ቸል ያለው ማን​ነው?
11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓሪ ይቅር ባይም ነውና፥
ኀጢ​አ​ትን ይቅር ይላል፥ በመ​ከራ ቀንም ያድ​ናል።
12ለሚ​ጠ​ራ​ጠር ልቡና ወዮ​ለት! ለጠ​ማ​ሞች እጆ​ችም ወዮ​ላ​ቸው!
ሥራው ሁለት ለሆነ፥ በሁ​ለ​ትም መን​ገድ ለሚ​ሄድ ኀጢ​አ​ተኛ ወዮ​ለት!
13ለሚ​ጠ​ራ​ጠ​ርና ለማ​ያ​ም​ንም ልብ ወዮ​ለት!
ስለ​ዚ​ህም አያ​መ​ል​ጥም።
14ትዕ​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ውን ላጡ ሰዎች ወዮ​ላ​ቸው!
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​መ​ለ​ሰ​ባ​ቸው ጊዜ ምን ያደ​ርጉ ይሆን?
15እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈሩ ቃሉን አይ​ረ​ሱም፥
የሚ​ወ​ዱ​ትም ትእ​ዛ​ዙ​ንና መን​ገ​ዱን ይጠ​ብ​ቃሉ።
16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈሩ ሰዎች ፈቃ​ዱን ይሻሉ፤
የሚ​ወ​ዱ​ትም በሕጉ ይረ​ካሉ፤
17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈሩ ልቡ​ና​ቸ​ውን ያዘ​ጋ​ጃሉ።
በፊ​ቱም ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ያዋ​ር​ዳሉ።
18በሰው እጅ ከም​ን​ወ​ድቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ እን​ው​ደቅ፥
እንደ ልዕ​ል​ናው የቸ​ር​ነቱ ብዛት እን​ዲሁ ነውና።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ