ዘፀአት 32:5-6
ዘፀአት 32:5-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አሮንም ባየው ጊዜ መሠዊያን በፊቱ ሠራ፤ አሮንም፦ ነገ የእግዚአብሔር በዓል ነው ሲል አወጀ። በነጋውም ማልደው ተነሥተው የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዉ፥ የደኅነትም መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሕዝቡም ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፥ ሊዘፍኑም ተነሡ።
Share
ዘፀአት 32 ያንብቡዘፀአት 32:5-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አሮንም በአየው ጊዜ መሠዊያውን በፊቱ ሠራ፤ አሮንም፥ “ነገ የእግዚአብሔር በዓል ነው” ሲል አወጀ። አሮንም በነጋው ማልዶ ተነሣ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትንም ሠዋ፤ የደኅንነት መሥዋዕትንም አቀረበ ሕዝቡም ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፤ ሊዘፍኑም ተነሡ።
Share
ዘፀአት 32 ያንብቡዘፀአት 32:5-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አሮን ይህን ባየ ጊዜ በወርቅ ጥጃው ፊት ለፊት መሠዊያ ሠርቶ፣ “ነገ ለእግዚአብሔር በዓል ይሆናል” ብሎ ዐወጀ። በማግስቱም ሕዝቡ በማለዳ ተነሥተው የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዉ፤ የኅብረት መሥዋዕት አቀረቡ፤ ከዚህም በኋላ ይበሉና ይጠጡ ዘንድ ተቀመጡ፤ ሊዘፍኑም ተነሡ።
Share
ዘፀአት 32 ያንብቡ