የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

በየእለቱ ከእግዚአብሔር መስማትናሙና

 በየእለቱ ከእግዚአብሔር መስማት

ቀን {{ቀን}} ከ14

እግዚአብሔር በተለያየ መንገደ ይናገራል

በጽድቅ የምናገረው ለማዳንም የምስረታ እኔ ነኝ፡፡ ኢሣ 63:1

ከዛሬ ጥቅስ እንደምንረዳው እግዚአብሔር እንደምናገርና የምናገረውም በጽድቅ እንደሆነ ያወጀበት ክፍል ነው፡፡ ሁልጊዜ መታመን ያለበት እርሱ ያለው ትክክል እንደሆነ ነው፡፡ እግዚአብሔር በተለያዩ መንገዶች ይናገራል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በቃሉ፣ በተፈጥሮ፣ በሰዎች፣ በሁኔታዎች፣ በሠላም፣ በጥበብ፣ በመለኮታዊ ጣልቃ ገብነት፣ በሕልም፣ ብራያ አንዳንዶች እንደሚሉት የውስጥ የልብ ምስክርነት፡- በጥሩ አገላለፅ ‹‹ማወቅ›› የሚባል የውስጥ የልብ መረዳት፣ እንዲሁም በታላቅ ፀጥታ ውስጥ ብሎ መጽሐፍ ቅዱስ የሚገልፀው ‹‹ትንሽ ድምጽ›› እኔም በጣም የማምንበት የውስጥ የልብ ምስክርነቶች ስሆን የመናገሪያው መንገዶች የተወሰኑ አይደለም፡፡

እንዲሁም እግዚአብሔር በሕሊናችን፣ በፍላጎታችን፣ ዝግ ባለ ድምፅ ውስጥ ይናገራል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ሁልጊዜ ሲናገር ትክክለኛና ከተፃፈው ቃሉ ጋር የማይጋጭ እንደምናገር ማስተወስ አለብን፡፡ አልፎ አልፎ የእግዚአብሔር ጥቅል የሆነ ድምፅ መስማት እንችላለን፡፡ በሕይወት ዘጫ ለሦስትና ለአራት ጊዜ ብቻ ሰምቻለሁ፡፡ ሁለቱ ተኝቼ ሳለሁ ስሜቴን በመጥራት አነቃኝ የሰማሁትም ጆሲ የሚል ብቻ ቢሆንም እግዚአብሔር እንደተናገረኝ አውቃለሁ፡፡ ምን እንደፈለገ አልገለፀልኝም፡፡ ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር አንድ የተለየ ነገር እንዳደረጉለት እንደፈለገ ተረድቻለሁ፡፡ ምንም እንኳ ግልጽ የሆነ ነገር በዚያ ጉዳይ ላይ ለዓመታት ባይመጣም፡፡

ዛሬ እኔ የማደፋፈርህ እግዚአብሔር በማንኛውም መንገድ ድምፅን እንዲያሰማና እንዲነገርህ እንድትጠይቀው ነው፡፡ እርሱ ይወድሃል፣ ለአንተ ለሕይወት ጥሩ እቅድ አለው፣ ስለእነዚህ ነገሮች ደግሞ ልናገርህ ይፈልጋል፡፡

ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚአብሔር በተለያየ መንገድ ይናገራል፣ ነገር ግን አስተውል ቃሉን በመቃረን መንገድ አይደለም፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 2

ስለዚህ እቅድ

 በየእለቱ ከእግዚአብሔር መስማት

ይህ አምልኳዊ አገልግሎት ከእግዚአብሄር ጋር አብዛኛውን ጊዜዎን እንዲጠቀሙ እና ከእግዚአብሔር ጋር የበለጠ የግል ጊዜን በማሳለፍ ግንኙነቶችዎን እንዲያሳድጉ እርስዎን ለማነሳሳት እና ለማበረታታት የሚያስችሉ ማስታወሻዎችን ይሰጣል።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረቡ Joyce Meyer Ministries ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://tv.joycemeyer.org/amharic/

ተዛማጅ እቅዶች