BibleProject | ስለ ሐዋርያው ጳውሎስ ዐጭር ትምህርት

BibleProject | ስለ ሐዋርያው ጳውሎስ ዐጭር ትምህርት

10 ቀናት

በዚህ ዐሥር ቀን ዕቅድ ውስጥ፣ ከአራት የሐዋርያው ጳውሎስ ጽሑፎች ጋር ይተዋወቃሉ። ገላቲያ ላይ፣ ጳውሎስ አሕዛብ የሙሴን ሕግ ማክበር አለባቸው ወይ ለሚለው ዐሳብ ምላሽ ይሰጣል። በኤፌሶን መጽሐፍ ላይ፣ ወንጌል በእኛ እና በእግዚአብሔር መካከል እንዲሁም እርስ በእርስ እንዴት ዕርቅን እንዳመጣ ያሳያል። ፊልጵስዩስ፣ የኢየሱስ ራስን የመስጠት ፍቅር እንደ ምሳሌ በመጠቀም አማኞችን ያበረታታቸዋል፤ ተሰሎንቄ ላይም፣ ጳውሎስ በስደት ላይ ያሉ ክርስቲያኖችን በንጉሡ ኢየሱስ ላይ ተስፋ እንዲያደርጉ ያበረታታቸዋል።

BibleProject መጽሐፍ ቅዱስን የበለጠ እንዲያውቁት የሚያግዝዎ ነጻ አገልግሎት ነው። አገልግሎታችንን የምናከናውነው፣ በዓለም ዙሪያ ያሉ ወገኖች በሚያደርጉልን ቸርነት የሞላበት ስጦታ ነው። ስለ ባይብል ፕሮጀክት የበለጠ ለማወቅ ድረ ገጻችንን የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ይጎብኙ፦ bibleproject.com/Amharic

ስለ አሳታሚው