የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ጥርጣሬዎቻችንና ተስፋ መቁረጦችናሙና

ጥርጣሬዎቻችንና ተስፋ መቁረጦች

ቀን {{ቀን}} ከ5

የእግዚአብሔር ጥገኝነት

ኢየሱስ ለመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ተመልሰው ሄደው በኢየሱስ ተዓምራት ዓይነ-ስውሮች ዓይናቸው ስለመብራቱ፣ ሽባዎች እየዘለሉ ስለመሆኑ፣ ለምፃሞች ስለመፈወሳቸው፣ ደንቆሮዎች እየሰሙ ስለመሆናቸው፣ ሙታን እየተነሱ ስለመሆኑ እና የእግዚአብሔር መንግስት እየተሰበከች ስለመሆኗ ያዩትን እንዲነግሩት ላካቸው፡፡ እኚህን ተዓምራት በማመልከት ለዮሐንስ እና ለዮሐንስ ደቀ-መዛሙርት ሲጠበቅ የነበረው መሲህ እርሱ ስለመሆኑ ያስረግጥላቸው ነበር፤ ምክንያቱም እርሱ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ላይ እንዳለው መሲሁ የሚያደርጋቸውን ድንቆች በሙሉ ፈፅሟልና፡፡

ኢየሱስ ይህን እያለ ያለበት ምክንያት ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት እግዚአብሔር በነብያቱ በኩል ቃል የገባቸው ነገሮች አሁን እርሱ እያደረጋቸው ያሉት ነገሮችን መሆናቸውና እግዚአብሔር ታማኝ ስለመሆኑ ነው፡፡ ኢየሱስ እያለ ያለው እግዚአብሔር ታማኝ ስለሆነ በእርሱ በመሲሁ በኩል የተስፋ ቃሉን እንደሚፈፅምና መንግስቱን እንደሚመሰርት፤ ምንም ጊዜው ቢረዝም እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ቃል የገባውን እንደሚፈፅም ያስረግጣል፡፡

ይህንን ትኩረት ለማድረግ ኢየሱስ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ሲናገር የዮሐንስን ታላቅነት ለሚያውቁት በእግዚአብሔር ምንግስት ከሁሉ ታናሽ የሆነ እንደሚበልጠው ያውጃል፡፡ ኢየሱስ ይህንን ማለቱ ዮሐንስ በብሉይ ኪዳን ያለውን ተስፋ ቃል መጠበቅ ብቻ ሲሆን ነገር ግን ልባቸውን ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ በሰራው ስራ ላይ የሚያደርጉቱ በእግዚአብሔር መንግስት ህይወት ተሳታፊዎች ይሆናሉ፡፡

ነገሩ በእስር ቤት ሳያበቃ በፊት መጥምቁ ዮሐንስ ስለ ክርስቶስ ይህን ብሎ ነበር “እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባኛል፡፡" ዮሐንስ ይህንን መሰረታዊ የእምነትና የትህትና መረዳት መያዙ በዚህ ምዕራፍ አንድ ነገር እንድንደመድም ያግዘናል ይኸውም ኢየሱስ ስለ መንግስቱ ተስፋ ቃል መፈፀም እግዚአብሔር የታመነ መሆኑን ዮሐንስ ተረድቶ እንዲበረታና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት እርግጠኛ እንዲሆንና ይህቺን ዓለም በሰላም መተዉና የእርሱ አገልግሎት ከንቱ አለመሆኑን እንዲረዳም ነው፡፡

ዮሐንስ ኢየሱስ ወደ መስቀል ከመሄዱ በፊት ነበር የመተው፡፡ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን መሲሁን ወደ ዓለም ልኮ ስለ ኃጢአታችን እንዲሞት ተስፋ የገባውን ኢየሱስአግዚአብሔር ፈፅሞ ታማኝነቱን እንደሚጠብቅ ያመለከተውን እውነት ለማየት ዮሐንስ አልታደለም ነበር፡፡ ስለዚህ ዮሐንስ ኢየሱስ እርሱ መሲህ እንደሆነ ማንም ጥርጥር ውስጥ ቢገባ ምን ያህል ርቀት ተጎዞ በሚገባ ለመመለስ እንደሚሄድ ለማየት አልታደለም፡፡

ከዮሐንስ በተለየ አንተና እኔ ግን በክርስቶስ የመስቀል ላይ ሥራ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ታማኝነት ማወቅ ብቻ ሳይሆን እርሱ በመስቀል ላይ በሰራልን ስራ ስናምን በእግዚአብሔር መንግስት ተሳታፊዎች በመሆን እውነተኛ የመስቀሉ ስራ ተጠቃሚዎች ነን፡፡

ስለዚህ ሶስተኛውን ጭብጥ ታማኝነትን እንዲህ ብለን መቋጨት እንችላለን፤ ከምናልፍባቸው ከባድ ነገሮች ተስፋ መቁረጥና ጥርጣሬ ስንለማመድ በወንጌል ስለ እኛ የታወጀውና በክርስቶስ በመስቀሉ ላይ የተገለጠው ይህ የታመነውየእግዚአብሔር ታማኝነት ለእኛ ያለውን ፍቅርና ተግባር ያሳየናል፡፡ በዚህ እንዲያሳልፈን ልንታመንበት እንችላለን፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 3ቀን 5

ስለዚህ እቅድ

ጥርጣሬዎቻችንና ተስፋ መቁረጦች

ይህ የአምስት ቀን የንባብ ዕቅድ በኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ በኩል የተገለጠውን በጥርጣሬዎቻችንና በተስፋ መቁረጦች ግዜያት ሁሉ የእግዚአብሔርን ታማኝነት እውነት እያሳየን ያበረታናል፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Returning to the Gospel - East Africa ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://returningtothegospel.com/

ተዛማጅ እቅዶች