የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ጥርጣሬዎቻችንና ተስፋ መቁረጦችናሙና

ጥርጣሬዎቻችንና ተስፋ መቁረጦች

ቀን {{ቀን}} ከ5

እግዚአብሔርን ማመን እንችላለን

ምናልባት በህይወትህ በዚህ ሰዓት ላይ እግዚአብሔር ለምን በህይወትህ ላይ አንዳንድ አስጨናቂ ነገሮችን ታልፍበት ዘንድ እንደፈቀደ ሙሉ በሙሉ ላትረዳ ትችል ይሆናል፤ እንዲሁም ልክ መጥምቁ ዮሐንስ በእስር ቤት እንደ ገጠመው ዓይነት ተስፋ መቁረጥና መጠራጠርም ሊገጥምህ ይችላል፡፡

እንደዚያ ከሆነ ነማንኛውም ተስፋ በሰጠህ ነገሮች ሁሉ ላይ ምንም ያህል ሊያደርገው ጊዜ ቢወስድ ሊፈፅመው ግን ታማኝ መሆኑን ሊታወስ ይገባል፡፡ እግዚአብሔር በህይወትህ ላይ ምን እያደረገ እንዳለ በሚገባ ያውቃል፤ ምንም እንኳን አንተ አሁን ላይ በህይወትህ ምን እያደረገ እንዳለ እርግጠኛ ባትሆንም፡፡

እኔ በግሌ እጅግ ሀያሌ ጊዜያት ከእግዚአብሔር ጋር እየተጓዝኩኝ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ተስፋ ቆርጫለሁ፤ እውነት እግዚአብሔር ግን ፀሎቴን እየሰማኝ ነው? በእነዚህ ወይም በእነዚያ ችግሮች ወይም አስቸጋሪ ነገሮች ይረዳኛልን የሚሉ ጥርጣሬዎችን ተለማምጃለሁ፡፡ ግን ዘወትር ልክ ስለ እኔ በመስቀል ላይ የሰራውንና ትናንት ያደረገልኝን ስመለከት እምነቴ ይበረታል፤ እናም እኔ ፈፅሞ ልገምተው በማልችለው መንገድ ከተፍ ይላል፡፡ ምናልባት አንተም ከእግዚአብሔር በተጓዝክበት ጉዞህ ይህን መሰል ምስክርነት ሊኖርህ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ከስር ያለውን ዓለት እንድንመታ እንደሚፈልግ ተረድቻለሁ በዚህም እርሱ ራሱ ከስራ ያለው ዓለት መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ አንድ ነገር አስተውያለሁ እግዚአብሔር ጀርባችንን በግድግዳው ላይ ሲያደርግ ጀርባችን የተደገፈበት ግንብ ግን እርሱ መሆኑን።

የእግዚአብሔር ታማኝነት ያረጋገጠልን ደህንነትን ለመጀመሪያ ጊዜ በመስቀል ላይ እንድናሸንፍ ክርስቶስን ወደ ዓለም ለመላክ በብሉይ ኪዳን የገባውን ተስፋ ፈፅሞልን ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ልክ እንደተፈፀመው ተስፋ ቃል ሁሉ በአዲስ ኪዳንም ክርስቶስ ወደ ዓለም ተመልሶ ይመጣል የሚለውን በመፈፀም የእግዚአብሔር ታማኝነት ይረጋገጣል፡፡ በዚያ ዳግም ምፅዓት ክርስቶስ የእግዚአብሔርን ዓለምና የዘላለምን መንግስት ወደመታየት ይገልጣል፡፡ ያ ደግሞ ሀጢአት፣ መከራና በዚህ ዓለም ያሉ ችግሮች በሙሉ ሲያበቁ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የመጥምቁ ዮሐንስ ታሪክ በተስፋ መቁረጥና በጥርጣሬ ጊዜ በክርስቶስ በመስቀል ላይ በቋሚነት በተገለጠው የእግዚአብሔር ታማኝነት ላይ ስናተኩር በእኛ እየኖረ ያለው መንፈስ ቅዱስ በማናቸውም እያለፍናቸው ካሉ የልብ መሰበርና አስቸጋሪ ነገሮች ውስጥ ሊያወጣን እንደሚችል መታመናችንን እንድንቀጥል ያስችለናል፡፡

በአጭሩ በተስፋ መቁረጥ ውስጥና መጠራጠር ውስጥ ሆነን እንኳን ከእግዚአብሔር የማይናወጥ መታመን የተነሳ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ላይ መታመን እንችላለን፤

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 4

ስለዚህ እቅድ

ጥርጣሬዎቻችንና ተስፋ መቁረጦች

ይህ የአምስት ቀን የንባብ ዕቅድ በኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ በኩል የተገለጠውን በጥርጣሬዎቻችንና በተስፋ መቁረጦች ግዜያት ሁሉ የእግዚአብሔርን ታማኝነት እውነት እያሳየን ያበረታናል፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Returning to the Gospel - East Africa ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://returningtothegospel.com/

ተዛማጅ እቅዶች