እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ጋብቻናሙና
የጋብቻ መፈጠር
እግዚአብሔር ጋብቻን ያበጀው ለሰው ዘር ክንውንና መለምለም ነው፤ ምንም እንኳን በዓለም ክፍሎች ጋብቻ እያሽቆለቆለ መሆኑ ባይካድም እግዚአብሔር ግን አሁንም ለራሱ ህዝብ ያቀደው መልካም ሀሳብ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ጋብቻን መፈናፈኛ የሌለው ያለፈበት ተቋም ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ እጅግ ከልክ ያለፈ የፍቅር ዓለም ስሜት ስላደረጉት ተስፋ አስቆራጭነቱ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ እንደ እግዚአብሔር ሀሳብ የሆነ ጋብቻ ግን የህይወት ዘመን ጥምረት፣ የጋራ መሰጠት፣ ኢየሱስ ለሙሽሪት ቤተ-ክርስቲያን ያለውን ዓይነት የፍቅር መገዛት የሚታይበት ነው መሆን ያለበት፡፡ እንዲሁም ጋብቻ ልንንከባከበው የሚገባ ነገር ነው፡፡
የመጀመሪያው ጋብቻ የተፈፀመው በአዳምና ሔዋን መካከል በኤደን ገነት በዘመን መባቻ ነበር፡፡ አዳም ከአፈር ነው የተፈጠረው፤ ሔዋን ወደ እርሱ ከመምጣቷ በፊት እግዚአብሔር አዳምን ምድርን እንዲንከባከብና እንዲጠብቃት አዞት ነበር፡፡ ከዚያም ሔዋን ከአዳም ተፈጠረች፡፡ (ምናልባትም አዳምን መሰረታዊ ሞዴል- መነሻ ማሳያ ልንለው እንችላለን፤ ሔዋንን ግን እጅግ ተሻሽሎና ከፍ ብሎ የመጣ ስሪት ልንል እንችላለን!) አንድ ነገር ማስተዋል የሚገባን ነገር ሰው ማለት ሰራተኛ ወይም ደግሞ አቅራቢ እንዲሁም ጠባቂ ማለትም በዙሪያው ላሉ ሁሉ መልካሙን ሁሉ የሚያይና የሚፈልግ መሆኑን ማስተዋል አለብን፡፡ የሰው ዘር በኃጢአት ከመውደቁ በፊት እግዚአብሔር እንድንሰራው የሰጠን ስራ አለ፤ መልካምም ብሎ ጠርቶታል፡፡
እግዚአብሔር አዳምን እንዲያቀርብና እንዲጠብቅ ተልዕኮ ከሰጠው በኋላ ለብቸኝነቱ ግድ እንደሚለው ድምፁን አሰማ፡፡ ይህ ብቻ ነበር እስካሁን ኃጢአት በሌላትና ፍፁም በሆነች ዓለም ላይ መልካም አይደለም የተባለው፡፡ ይሄ በእርግጠኝነት የጋብቻን እጅግ አስፈላጊነት ያሳያል፡፡ እርስ በእርስ እንፈላለጋለን፡፡
ሌላው የሚያስገርመው ደግሞ አዳም ወደ አግዚአብሔር ረዳት ፈልጎ አልቀረበም፤ ራሱ እግዚአብሔር ነው ለአዳም እንደሚያስፈልገው አውቆ ያዘጋጀለት፡፡ ምንም እንኳን አዳም በጣም የምታምር፣ ለም መናፈሻ፣ እጅግ ብዙ አዕዋፍና እንስሶች የነበሩት ቢሆንም አንድ የጎደለው ነገር ግን ነበር፡፡ ሀብትና ቁሳቁስ በቂዎቹ አልነበሩም፡፡ አዳም የምታግዘው ረዳት፤ ከእርሱ ጋር እኩል መነጋገርና መግባባት የምትችል ታስፈልገው ነበር፡፡ ከዚህ ብርታትን ልናገኝ እንችላለን፡፡ እግዚአብሔር ያውቀናል፤ እኛ ለእኛ ከምንሰራው በተሻለ ምን እንደሚያስፈልገን የሚያውቅ እንዲሁም ከሚባለው በላይ ሊያዘጋጅልን የሚችል ነው፡፡
ያላገባህ ከሆነና ለማግባት ፍላጎቱ ካለህ አግዚአብሔር እጮኛውን እንዲያስተዋውቅህ በየቀኑ ፀልይ፡፡ ጊዜ ወስደህም ጋብቻ ሰው የፈጠረው ባለመሆኑ አመስግን፡፡ በማህበረሰብ እንድናድግና እርስበርሳችን ጥልቅ የሆነ ግንኙነት እንዲኖረን የሚረዳን ከእግዚአብሔር የተሰጠን ስጦታ ነው፡፡ ጋብቻ ዕድሜ ጠገብ ተቋም ነው ነገር ግን ጊዜ ያለፈት ግን አይደለም፡፡ እኛ ለመያያዝና አቻችን ከሆነው ግን ደግሞ ከእኛ ከሚለየው ጋር ለመጣመር ፍላጎት እንዲኖረን ተደርገን የተፈጠርን ነን፡፡ ይኸውም በህይወት ዘመን ውሳኔ እግዚአብሔር እኛን ሊባርክ ካለው መልካም ሀሳብ አስደማሚው ነው፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ያገባህም/ሽም ሁን/ኚ ልታገባ/ቢ የምትፈልግ/ጊ ይህ የ3 ቀናት የንባብ ዕቅድ በህይወት/ሽ ዘመን ላለው የባልነት ወይም የሚስትነት መሰጠት የእግዚአብሔርን መልካም ዓላማ እንድታውቅ/ቂ ይረዳሃል/ሻል፡፡ የጥምረትን፣ መብዛት፣ የአዋጅን፣ የቅድስናንና የእርካታን ዓላማዎች በመፈለግ ኢየሱስ ለሙሽሪት ቤተ-ክርስቲያኑ ያለውን ፍቅር ማንፀባረቅን ተማር፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Kip' Chelashaw ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://christchurchke.org/